>

በቅርቡ ኣንድነት ፖርቲን የተቀላቀሉት ኣስራት ኣብርሃ ታሰሩ

ዛሬ መድረክ የተቃውሞ ሰልፍ ያድርግ አንጂ ኣባላቶቹና ኣመራሮቹ ሲታሰሩና ሲዋከቡ መዋላቸው ይታወቃል። በትላንትናው ዕለት በቡራዮ 12 የመድረክ ኣመራሮች ታስረዋል። በመሆኑም በቡራዮ የታሰሩትን የመድረክ ኣመራርን ለመጠየቅ ወደ ቡራዮ ያቀኑት ኣቶ ኣስራት ተመሳሳይ እጣ ደርሶባቸዋል።

በቅርቡ ኣንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፖርቲን የተቀላቀሉት የቀድሞው የኣረና ፓርቲ ኣመራርና ኣባል የነበሩት ኣቶ ኣስራት ኣብርሃ በሃገራችን የነቃ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ፖለቲከኞች ኣንዱ ሲሆን፣ ለኣድናቆትና ተደጋጋሚ ህትመት የበቃው ከ”ኣገር በስተጀርባ” መጽሓፍ ደራሲ መሆናቸው ይታወቃል።

Filed in: Amharic