>
5:13 pm - Wednesday April 19, 9972

አባይን የኦሮሞ ልጆች ልክ አስገቡት [ሙሉነህ ኢዮኤል]

MerfeQulef on sosial midia 18012016ከአዲስ አበባ ማስተር ክራይምና የተቀናጀ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የመሬት ቅርምት ጋር በተያያዘ ስሙ በክፉ የሚነሳበት እንደ አባይ ጸሃይ ያለ ሌላ ሰው የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ ሰው ስምና ግብር ላይገናኙ እንደሚችሉ ጥሩ ማሳያ ነው። ሁለት በጣም ትልቅ ፋይዳ ይላቸውን ነገሮች ይዞ የሚዞር ሰው ነው። አባይና ጸሃይን። አባይም አባይ፤ ጸሃይም ጸሃይ። ይህ ሰው ግን ባለፉት ሁለት አመታት ኦሮሚያ ውስጥ የፈሰስውን የደም ጎርፍ ባሰብን ቁጥር በጆሯችን የሚያቃጭል ስም። የሳጥናኤል ልጅ ነው። መቼም አንረሳውም።

ስለአባይ ሥልጣን

አባይ አማካሪ የሚባል ትግራይ ስሪት ባርኔጣ ጣል አድርጎ ሀይሌ የሚጋል ፈረስ ጋላቢ ነው። ምንም እንኳን ከመለስ ሞት በኋላ ሁላቸውም የተስማሙበትና ሁሉን ያስፈራ አንድ ሰው ከወያኔ መንደር ቢጠፋም እርስ በርሳቸው እየተጠባበቁ አመራር የሚሰጡ ሰዎች ግን አልታጡም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አባይ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ሰው ሆኗል። በሌላ አገላለጽ የህይለማርያም የቅርብ አለቃ ማለት ነው። እውነተኛው ጠቅላይ ምንስትር።

ጥቂት ቃላት ስለዳንኤል

አባይና ዳንኤል አጭር ቆይታ አድርገው ነበር። ዳንኤል እየተርበተበተ አንድ ጥያቄ ብቻ ጠየቀው። ዳንኤል ሃይለማርያምን ቢሆን የሚጠይቀው እንዲህ አይርበተበትም ነበር። አገሪቷን ከሚገዛው ሰውዬ ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ ሲሰማው የደነገጠ ይመስላል። ዳንኤልን ሳውቀው ማንንም የሚፈራ ሰው አልነበረም። በአንድ ወቅት እግዚአብሄር እንደሌለ ሊያስረዳን ፈልጎ ልንረዳለት ባለመቻላችን እንዴት እንደተናደደብን እስከዛሬ አስታውሳለሁ።

አባይና መልሱ

1ኛ የአባይን ስም በክፉ ያነሳ ሁሉ የትግራይን ህዝብ ይጠላል፤

አባይ የኔን ስም በክፉ የሚያንሱ ሁሉ የትግራይን ህዝብ የሚጠሉ ናቸው አለን። አባይ በዚህ አባባሉ “እኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ነን” እያለን ነው። እውነት አባይና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው? አባይ የኦሮሞን ህዝብ በጣም እንደሚጠላ በመቶዎች እያስገደለ፣ በሽዎች እያቆሰለና እያሳሰረ አረጋግጦልናል። በተጨማሪም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሃዘኑን ለመግለጽ ባለመሞከር ለፈሰሰው ደም ቅንጣት ሃዘን እንደሌለው አሳይቷል። ይህ ሁሉ የሚያሳየው አባይ ኦሮሞን እንደሚጠላ ነው። ስለዚህ አባይና የትግራይ ህዝብ አንድ ከሆኑ የትግራይ ህዝብም ኦሮሞን አጥብቆ ይጠላል ማለት ነው። እውነት የትግራይ ህዝብ ልክ እንደአባይ የኦሮሞን ህዝብ ይጠላል? ለዚህ ጥያቄ መልስ መመለስ ያለበት የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። መልሱን ከትግራይ ህዝብ እጠብቃለሁ።

2ኛ የአባይ ሽንፈት

አባይ ማስተር ክራይሙን የሚቃወም ልክ ይገባል ብሎ ነበር። ይህን ማለቱን የሚገልጽ የድምጽ ማስረጃ ኦኤምኤን አቅርቧል። ስለዚህ ጉዳይ ምን ትላለህ ሲባል አባይ የሰጠው መልስ እጅግ አስገራሚ ነው። “ከሳሾቼ ያቀረቡት ፓረግራፍ የኔ አይደለም” የሚል። ለማስረጃ የቀረበበት ድምጹ ሆኖ እያለ ጽሁፉ የኔ አይደለም ማለቱ ሰውዬው ከራሱ ድምጽ እየሸሸ እንደሆነ ነው። ድምጹ የኔ አይደለም ማለት አልቻለም። ይህ ማለት ደግሞ አባይ የራሱ ድምጽ አሳፍሮታል ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው አባይ ከራሱ ከድምጽ እየሸሸ እንደሆነ ነው። ይህ ማለት ደግሞ የመሸነፍ ምልክት ነው። ይህ ማለት ደግሞ አባይ ልክ ገባ ማለት ነው።

ቪዲዮውን ይመልከቱ

 

Filed in: Amharic