>

ወሮበሎች በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሰርጎ መግባት?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

VOA 3ጥንታዊ የሮማ ሰዎች እራሳቸውን ከወሮበላ አደጋ ጣዮች ለመጠበቅ ሲሉ የከተሞቻቸውን በሮች እና ግንቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ይጠብቁ ነበር፡፡

የሮማ ሰዎች ወሮበላ አደጋ ጣዮች ምንም ዓይነት አደጋ ሳይጥሉ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ገና ከበሩ ጋ በመጠበቅ ዓላማዎቻቸውን ያከሽፉባቸው ነበር፡፡

በአሁ ጊዜ ደግሞ የዘመኑ የፕሬስ ነጻነት አደጋ ጣይ ወሮበሎች እ.ኤ.አ መስከረም 26 /2015 በዋሺንግተን ዲ.ሲ የሚገኘውን የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በድብቅ  ጭለማን ተገን አርገው ሰርጎ ገብተው ነበር ፡፡

የወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርሀን ፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተተኮሰው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን (ህዋሀት ) ስብስብ ሚኒስትር የሆነው ቴዎድሮስ አድኃኖም እና በአሜሪካ የዘ-ህዋሀት አምባሳደር ተብዬ ግብረ አበር የሆነው ግርማ ብሩ ጨለማን ተገን በማድረግ በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት የአሜሪካ ድምጽ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ዋሺንግተን ዲ.ሲ እንደ ጅብ በሌሊት ተስበው በመግባት ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ከሌሎች አገልግሎቶች የተመረጡ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር የሚስጥር ስብሰባ በማድረግ ቆሻሻ እና ዕኩይ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡ ድርጁቱን አርከሰዉታል

ድል ያደረጓቸውን የሮማ ሰዎችን ሕግ እና ደንቦችን በመጣስ ወንጀል ይፈጽሙ እንደነበሩት እንደ ጥንቶቹ ያልሰለጠኑ አደጋ ጣይ ወሮበሎች ሁሉ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ቴዎድሮስ አድኃኖም እና ግርማ ብሩ በተከበረው የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚስጥር ሰርገው በመግባት የተመረጡ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ሌሎች ዘጋቢዎችን እና የስራ ባልደረቦችን በመሰብሰብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ውስጥ እያራመዳቸው ስላሉት ፖሊሲዎች እና ስለሚሰጠው አመራር የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እንዴት መዘገብ እንዳለበት መመሪያ በመስጠት እና ዘገባዎቹን ከማቅረቡ በፊትም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ማሳወቅ እንዳለበት ዓይን ባወጣ መልኩ ያለምንም ሀፍረት የዴሞክራሲ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ጠበቃ ነኝ በምትለው ሀገር ውስጥ በመገኘት መመሪያሰጥተዋል፡፡

አንድ የውጭ ሀገር አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲ.ሲ ውስጥ በመገኘት እስካሁን ድረስ ተሞክሮ የማያውቀውን እንደዚህ ያለ የጋዜጠኝነትን ስነምግባር በሚያውክ እና ድርጊቱም እጅግ በጣም አሳፋሪ እና ባልተጠበቀ መልኩ የተካሄደ የፈሪዎች የመቅበዝበዝ ዕኩይ ምግባር ያልተጠበቀ ክስተት ነበር፡፡

ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት አደጋ ጣይ አፋኝ የወሮበሎች ስብስብ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ላይ ሲሰነዝር የቆየውን አፍራሽ ድርጊት ሁሉ በመቃወም ለቪኦኤ ተሟጋች ጠበቃ ሆኘ ቆይቻለሁ፡፡

ህዋሀት  ስብስብ መሪዎች በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የጋዜጠኝነት ነጻነት እና ተማዕኒነት ላይ ኋላቀር የሆነውን ያልሰለጠነ ጥቃቱን በመሰንዘር ከከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ የማይደፈረውን ምሽጌን አጠንክሬ በመያዝ ከፍተኛ የመከላከል ተጋድሎ ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡

ህዋሀት  በተለያዩ አጋጣሚዎች የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎትን በተደጋጋሚ እና ጭካኔን በተመላበት ሁኔታ የጥቃቱ ዒላማ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 አሁን በህይወት የሌለው የህዋሀት  መሪ የነበረው ጨካኙ እና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋዜጠኞች በሚያስተላልፉት ዘገባ በርካታ ወንጀሎችን ይፈጽማሉ በማለት በአምስት የአፍሪካ ቀንድ ዘጋቢ በሆኑት ጋዜጠኞች ላይ የውንጀላ ክስ አቅርቦ ነበር፡፡

ይህ ላልተጠበቀ እና አሳፋሪ የሆነው የመለስ ዜናዊ ድርጊት የቪኦኤ የብሮድ ካስት ገዥዎች/Broadcasting Board of Governors (BBG) አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ወያኔ በቪኦኤ ዘጋቢዎች ላይ እያቀረበው ያለው የውንጀላ ክስ መሰረተ ቢስ ነው በማለት በአንድ ድምጽ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው፡፡

በዚያን ጊዜ ቦርዱ ያስተላለፈው የውሳኔ አዋጅ እንዲህ የሚል ነበር፡

“እነዚህ የውንጀላ ክሶች የፕሬስ ነጻነትን ለመወንጀል የሚደረጉ ጫጫታዎች የተሞሉበት ተራ እና ባዶ የውንጀላ ቅጥፈት ከማለት ውጭ ሌላ የሚባል ነገር የለም፡፡ እኛ የጋዜጠኝነት ስነምግባራችንን እና የስራ ጥራታችንን በማጠናከር በጽናት እና ሊቀለበስ በማይችል መልኩ ለእውነተኛ ዘገባ እንቆማለን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለትክክለኛ፣ ለተመጣጠነ እና አጠቃላይ የሆነ መረጃ ያለምን ችግር ተደራሽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ላለፉት 24 ዓመታት የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ይህንን ድርጊት በሚገባ ተወጥቶታል፡፡ አሁንም በቀጣይነት ይህንን እውነተኛ የአዘጋገብ ድርጊቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡” የሚል ነበር፡፡

አድኃኖም እና ግበረ አበሩ ብሩ ጨለማን ተገን በማድረግ በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት የአሜሪካ ድምጽ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ዋሺንግተን ዲ.ሲ እንደ ጅብ በሌሊት ተስበው በመግባት ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ከሌሎች አገልግሎቶች የተመረጡ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር የሚስጥር ስብሰባ በማድረግ ቆሻሻ እና ዕኩይ ድርጊት መፈጸማቸውን አስመልክቶ የተዘጋጀ ዘገባ ካነበብኩ በኋላ በጣም ተናድጄ ነበር ፡፡

አድኃኖም እና ብሩ “በተቀደሰው የአሜሪካ የፕሬስ ነጻነት ማዕከል በሆነው አዳራሽ” ውስጥ በድብቅ ተስበው በመግባት   እንደ  ተኩላዎች የበግ ልብስ በመልበስ በግን ለመምሰል ከሚገኙት ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

እንደዚሁም ሁሉ የፕሬስ ነጻነት ጨለማ ልዑሎች ድብቅ በሆነ መልኩ ወደ አሜሪካ የፕሬስ ነጻነት የተቀደሰ ቦታ ውስጥ ተስበው በመግባት ለዓለም ህዝብ በመታዬት ቅዱሱን ቦታ አርክሰውታል ከማለት ጋር አንድ እና አንድ ነው፡፡ ያንን ቅዱስ ቦታ አርክሰውታል፡፡

የአድኃኖም ህዋሀት  በኢትዮጵያ ለሩብ ምዕት ዓመት ያህል በዘለቀ የኢትዮጵያን የፕሬስ እና መረጃ ስርዓት በጨለማ ብርድ ልብስ እፍን አድርጎ ጋርዶት ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ በህዋሀት  የጭቆና መዳፍ ስር በአፍሪካ በአስከፊ ሁኔታ የፕሬስ ነጻነት የሚደፈጠጥባት እና በደፍጣጭነቷበሁለተኛዋ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት!

እ.ኤ.አ በ2015 የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ እንዳወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የፕሬስ ምርመራ ከሚካሄድባቸው ሀገሮቸ መካከል በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2015 ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “ኢትዮጵያ፡ ሜዲያ እየሞተባት ያለች ሀገር“ በሚል ርዕስ እንዲህ የሚል ዘገባ አስነብቦ ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ስልታዊ በሆነ መልኩ በሀገሪቱ ነጻ ድምጾች ላይ አደጋ በመጣል፣ ሜዲያውን የመረጃ እና የትንታኔ ምንጭ አድርጎ ዋጋ በመስጠት ከማስተናገድ እና ከማጠናከር ይልቅ በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ እንዲሽመደመድ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡“

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 የዓለም የጋዜጠኞች መሪ የሙያ ድርጅት/world’s leading professional organization for journalists የተባለው ድርጅት “የኢትዮጵያ መንግስት በስራቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ ይፍታ” የሚል ተማጽዕኖ አቅርቦ ነበር፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ፍሪደም ሁውስ/Freedom House የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2015 ዘገባው እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፣ “ወደፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ለሚካሄደው ምርጫ በመፍራት በጋዜጠኞች እና በጦማሪያን ላይ ኃይልን የቀላቀለ እርምጃ በመውሰድ እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ ፕሬስ በአስደንጋጭ ሁኔታ ተሸመድምዶ ወድቋል“ በማለት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 30/2015 የአድኃኖም ህዋሀት አገዛዝ የኢትዮጵያ ወጣት ጋዜጠኛ የሆነውን ሕገመንግስቱን ጥሷል በማለት የሀሰት የሸፍጥ ውንጀላ በማቅረብ በእስር ቤት አስሮ እያማቀቀው የሚገኘውን ተመስገን ደሳለኝ ህክምና እንዳያገኝ እና ቤተሰቦቹም እንዳይጎበኙት እገዳ ጥሏል በማለት እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቷል፡

“ተመስገን በጀርባ ሕመም በመሰቃየት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለህመሙ ማስታገሻ የሚሆን ሕክምና እንዳያገኝ እና በቤተሰቦቹም እንዳይጎበኝ የክልከላ ዕግድ ተጥሎበታል፡፡ ቤተሰቦቹ መጎብኘት እንንዳይችሉ ዕገዳ ከመጣሉ በፊት በተገኘ አንድ የውስጥ መረጃ መሰረት የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የውስጥ ምንጭን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው ተመስገን በግራ ጆሮው በኩል የመስማት ችግር አጋጥሞታል፡፡ ባለፈው ሀምሌ ወር እንደጎበኘው እንደ አንድ ምንጭ ከሆነ ጋዜጠኛው ከፍተኛ የሆነ የጀርባ ህመም ችግር የገጠመው በመሆኑ መቀመጥም ሆነ መተኛት አይችልም“ ብሎ ነበር፡፡

.. መስከረም 26/2015 በኢትዮጵያ ያሉት በጥባጮቹ የፕሬስ ነጻነት አሳሪዎች “ከኢትዮጵም አልፈው ወደ አሜሪካ በመሄድ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም/ቪኦኤ ዋሺንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት በጨለማ በድብቅ ሰርገው በመግባት ከጥቂት የድርጅቱ የስራ ባልደረቦች ጋር ስብሰባ በማድረግ ከስልጣናቸው ውጭ የኢዲቶሪያል ስራ መመሪያ ሰጥተው ወጥተዋል፡፡“

አድኃኖም እና ብሩ ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በድብቅ ሰርገው በመግባት ከቪኦኤ የአማርኛው ድምጽ አገልግሎት ከጥቂት የተመረጡ የድርጅቱ የስራ ባልደረቦች እና ዘጋቢዎች ጋር ያደረጉት ስብሰባ የአድኃኖም ህዋሀት  ለሩብ ምዕት ዓመት ያህል በኤሌክትሮኒክ ለማፈን ሲያደርግ ከነበረው እኩይ ጥረት ጋር እኩል ነው፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ከአስር ዓመታት በላይ ሲያንቋሽሹት እና ስሙን ጥላሸት ሲቀቡት የቆዩትን ድርጅት በድብቅ ያውም በድቅድቅ ጨለማ ለመጎብኘት የመጡት ለምንድን ነው?

ለበርካታ ጊዚያት በአየር ሞገድ ላይ ብለውት ብለውት አልሳካላቸው ያለውን እዚሁ ከቢሮው ድረስ ሰተት ብለው በድብቅ በመግባት በይፋ የማፈን ሙከራቸውን ለማድረግ ነውን?

አንድ የሌላ ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና አንድ የውጭ ሀገር አምባሳደር የሆኑ ሰዎች በምን ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ነው በተከበረው የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎት መስጫ ዓለም አቀፋዊ  ተቋም ውስጥ በድብቅ እና በጨለማ በመግባት ከተመረጡ የድርጅቱ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር ሁለት ሰዓት የፈጀ የግል  ስብሰባ ለማድረግ የሚችሉት?

አንድ የሌላ ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና አምባሳደር የሆኑ ሰዎች በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ተቋም ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በድብቅ እና በጨለማ ሰርገው በመግባት ከተመረጡ የድርጅቱ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር ሚስጥራዊ ስብሰባ በማካሄድ የሚያተርፉት ውጤት በተጨባጭ ምን ሊሆን ይችላል?

የአድኃኖም ህዋሀት አገዛዝ ነጻ ጋዜጠኞችን በሚያገኝበት ወይም ደግሞ በሚጎበኝበት ጊዜ ዋናው እና ብቸኛው ዓላማው ነጻ ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅ፣ ለማስፈራራት፣ በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ከተቻለም በእስር ቤት አስግበቶ ለመቀፍደድ መሆኑ ጸሐይ የሞቀው እና ሀገር ያወቀው ጉዳይ ነው፡፡

አንድ የሌላ ሀገር አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆነ እና (የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን ለመውሰድ ሌት ቀን የሚቋምጥ) ሰው እንዲሁም በዓለም ላይ የሚገኙት ታላላቆቹ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በየጊዜው ዋና የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ነው እያሉ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን የሚያወጡበት አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለምንድን ነው ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በድብቅ እና በድቅድቅ ጨለማ በመሄድ በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በመገኘት ስብሰባ ሊያካሂድ የሚችለው?

እኮ ለምን? ለምን?

አድኃኖም እና ብሩ በሳምንቱ መጨረሻ በአንዱ ዕለት ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት ለግል ቢዝነስ ጉዳይ ወይም ደግሞ ቃለመጠይቅ ለማድረግ በእርግጠኝነት እንደሚመጡ ለመገመት ይቻላል፡፡

አድኃኖም እና ብሩ በድርጅቱ መደበኛ የስራ ሰዓት እና ይፋ በሆነ መልኩ ለምን ምክንያት እንደመጡ እና በመደበኛው የስራ ሰዓት መሆኑም ተመዝግቦ ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ለመምጣት ያልፈለጉበት ምክንያት ምንድን ነው?

ለአድኃኖም እና ለብሩ በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት በሚስጥር እና በጨለማ ስብሰባ የማድረጉ አስፈላጊነት ምክንያት ምንድን ነው?

አድኃኖም እና ብሩ የእነርሱ መንግስት ጠላቶች ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን እና ያልተጋበዙትን የቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ስም ዝርዝር ለመውሰድ ፈልገው ነው በድብቅ ከሜዲያ ተቋሙ በጨለማ የገቡት?

ለምንድን ነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና አምባሳደሩ በአንድ ወገን ሌሎች የተመረጡ ጥቂት የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ደግሞ በሌላ በኩል በመሆን ለሁለት ሰዓታት ያህል የፈጀው ስብሰባ በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት ያውም ማታ በሚስጥር የተካሄደው ድብቅ ስበሰባ በዜና ስርጭት እንዲተላለፍ ወይም እንዲዘገብ ያልተደረገው?

የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት በዋሺንግተን ዲሲ የሚደረጉትን ብዙም ጠቀሜታ የሌላቸውን ነገሮች ዜና እየሰራ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ሲዘግብ ይስተዋላል፡፡ ታዲያ የተቋሙ የተለመደው አሰራሩ እንደዚህ ከሆነ ለምድን ነው የአድኃኖም እና የብሩ ከተመረጡ የቪኦኤ  ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በሌሊት ለሁለት ሰዓታት የተካሄደው ሚስጥራዊ ስብሰባ ለሕዝብ ያልተገለጸው? ምናልባትም አንድ ሰው ዜናው ለሕዝብ እንዳይተላለፍ በማሰብ የደበቀው ነገር ሊኖር ይችል ይሆን?

በአድኃኖም እና ብሩ በአንድ ወገን እና በተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች በሌላ በኩል በመሆን በማታ በሚስጥር የተካሄደው የሁለት ሰዓታት ስብሰባ የቪኦኤን የእራሱን የጋዜጠኝነት መስፈርት እና ተሞክሮን ለአድማጭኦች ማቅረብ የድርጅቱን የጋዘጠኝነት ስነምግባር ሊያሟላ አይችልምን?

ለመሆኑ እንደዚህ ዓይነቱ አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ሚስጥራዊ የስብሰባ ክስተት በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት በሌሊት እንዲካሄድ መደረጉ ለቪኦኤ የጋዜጠኝነት ነጻነት እና ታማዕኒነት ምን ማለት ነው?

የአገዛዙ ሁለተኛ ሰው በሆነው ታላቅ ባለስልጣን (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር) እና በውጭ ሀገር በሚገኝ ታላቅ የዲፕሎማሲ ሰው (በዓለም ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላት ሀገር ውስጥ አምባሳደር ሆኖ በተቀመጠ ሰው) እና በተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረባዎች መካከል የተደረገው የጓዳ በር ስብሰባ እና ስምምነት ትይንት እንዴት አድርጎ ነው የኢትዮጵያ አድማጮች ስለቪኦኤ የጋዜጠኝነት ታማዕኒነት እና ነጻነት ያላቸውን ስሜት ሊጎዳ የሚችለው?

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን አጠቃላይ የሆኑ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና ሌሎችን ጉዳዮችን በሚመለከት ትክክለኛ፣ በእውነት ላይ የተመሰረተ እና ከአድልኦ ነጻ የሆኑ ዜናዎችን፣ ዘገባዎችን፣ መረጃዎችን እና ትንታኔዎች በሀገር ውስጥ ሌላ ምንም ነጻ የሆነ ሜዲያ የሌለ ስለሆነ የሚያገኙት በቪኦኤ ላይ ተመስርተው ነው፡፡

ለመሆኑ ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር መሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በሌሊት ለሁለት ሰዓታት ያህል (ስብሰባው ለምን እንደተካሄደ ሊገልጽ የሚችል ምንም ዓይነት የጽሁፍ መረጃ በእርግጠኝነት ባልተያዘበት ሁኔታ) አብረው ለመሳተፍ የወሰኑት የተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ምን ይሰማቸዋል?

እነዚህ የቪኦኤ ተሳታፊ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ወዲያውኑ ድርጊቱ እንደተፈጸመ፡ “ይህ በሳምንቱ መጨረሻ በጨለማ በሚስጥር ምንም ዓይነት ምዝገባ ሳይያዝ ለሁለት ሰዓታት ያህል ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር የተደረገው ስብሰባ በብዙሀን መገናኛ ቢተላለፍ እና በይፋ ቢዘገብ ኢትዮጵያውያን አድማጮች ዘንድ ምን ዓይነት ግንዛቤ ሊያዝ ይችላል?“ የሚል ጥያቄ አንስተው ነበርን?

የአድኃኖምን እና የብሩን ስብሰባ የተካፈሉ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች እንዲያው ስለጉዳዩ ትንሽም ነገር ቢሆንአስበው ነበርን;

ነው ወይስ ደግሞ በአንክሮ ማገናዘብ ባለመቻላቸው በእንዝህላልነት በውሳኔ አሰጣጣቸው ደካማነት ግዙፍ የሆነ የሙያዊ ስነምግባር ስህተት ፈጽመዋል?

ያም ሆነ ይህ እነዚህ በዚያ ድብቅ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ዘጋቢዎች እና የድርጅቱ የስራ ባልደረቦች የዓለም አቀፍ ዝናን በተጎናጸፈው በቪኦኤ የጋዜጠኝነት የሜዲያ ተቋም ውስጥ መቀጠል ሳይሆን በሌላ ለእነሱ ምግባር የሚመጥን ድርጅት ፈልገው እና አፈላልገው መቀጠር ይኖርባቸዋል፡፡

የፍላጎት ግጭት ጉዳይን እና ግጭቶችን ለማስወገድ ስለሚቻልበት ሁኔታ የቪኦኤ ጋዜጠኞች የጋዜጠኝነት ስነምግባር ሰነድ  ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ እንዲህ በማለት አስቀምጦታል፡

“ሰራተኞች ከምንም ዓይነት አድልኦ በጸዳ መልኩ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ የግል ድርጅትን ወይም ግለሰቦችን አያስተናግዱም፡፡ እናም ሰራተኞች አድልኦ ያለው የሚያስመስል ስራን ስዕል ሊያላብስ የሚችል ከሚሆኑ ነገሮች ወይም ደግሞ ሕጉን እና የስነምግበር ደንቡን ለመጣስ ከሚያስመስሉ ማናቸውም ነገሮች ሁሉ እራሳቸውን ማስወገድ አለባቸው፡፡“

የጋዜጠኞች የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር ከዚህም በተጨማሪ “ለአሜሪካ ድምጽ ታማኝ መሆን  ከእሴቶቻችን መካከል ዋናው ነው“ በማለት ግልጽ አድርጓል፡፡

ለዓለም አቀፍ ለአህጉራዊ እና ለአሜሪካ ዜናዎች እና መረጃዎች ምንጭ በመሆን ለቪኦኤ ተማዕኒነት ከመቆም ዓላማ አንጻር ሲገመገም ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር በመሆን የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት ያካሄዱት ሚስጥራዊ ስበስባ ምን ማለት ነው?

አድኃኖም ወይም ደግሞ ብሩ በአሜሪካ የቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት እንደዚህ ያለ ከምዝገባ ውጭ የሆነ እና በሚስጥር የተካሄደ ስብሰበ ከቪኦኤ ዘጋዎች እና የስራ ባልደረባዎች ጋር ካሁን በፊት  አካሂደው ያውቃሉን?

አድኃኖምን እና ብሩን ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት የጋበዙት ሰዎች ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያለ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የቆዬ ተሞክሮ እና ልምድ ከሌላቸው በስተቀር እንዴት ይኸ ነገር በአንድ ቅጽበታዊ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል?

አንደው ለነገሩ አድኃኖምን እና ብሩን ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት እንዲገቡ የጋበዙት የቪኦኤ ዘጋቢዎች/ሰራተኞች የስልክ እጀታቸውን በማንሳት እንዲህ በማለት ደውለው ነው?  “ይስሙ! ይስሙ! አድኃኖም፣ ብሩ ቅዳሜ ማታ ምንድን ታደርጋላችሁ? ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት የፒዛ እና የጃም ፓርቲ ማረግ ትፈለጋላችሁ “፡፡  (የቪኦኤን ስርጭት ታፍናላችሁ አላልኩም፡፡)

ለሚስጥራዊ ስብስባው የተመረጡት የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ወይም ደግሞ በሌላ ተመሳሳይ በሆነ ስራ ያሉ ሰዎች ለየትኛውም ምክንያት ይሁን ከትክክለኛው የሙያ ተልዕኮ ውጭ በመሄድ በዋሺንግትን ዲ.ሲ የሚገኘውን የዘ-ህዋሀትን  ኤምባሲ ጎብኝተው ያውቃሉን?

ማናቸውም የቪኦኤ ዘጋቢዎች ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ጋር ግላዊ ወይም ደግሞ የገንዘብ ግንኙነት አላቸውን?

ግርማ ብሩ ለእርሱ አገዛዝ በየጊዜው እየተከታተሉ ትዕዛዝ በመቀበል ዘገባ የሚያቀርቡለት የቪኦኤ የጋዜጠኞች እና የሰራተኞች የሚስጥር ካድሬዎችን አዘጋጅቷልን?

አድኃኖም እና ብሩ የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎት VOAን የዘ-ህዋሀት ብሮድ ካስት ኮርፖሬሽን (EBC) እንደሆነ አድርገው ያስባሉን?

የአድኃኖም ዘ-ህዋሀት አገዛዝ አባላት ሁልጊዜ EBCን በሚጎበኙበት ጊዜ ምን መዘገብ እንዳለበት እንደሚፈልጉ እና ምንስ መዘገብ እንደሌለበት በመጮህ ለአሻንጉሊት ጋዜጠኞቻቸው ትዕዛዝ ያዥጎደጉዳሉ፡፡ የአድኃኖም አገዛዝ በተደጋጋሚ ለዘጋቢዎቹ የተዛባ፣ በሸፍጥ የታጀበ እና አሳሳች የሆኑ ዜናዎችን እና መረጃዎችን ለህዝብ እዲያቀርቡ ትዕዛዝ ይሰጣሉ፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በድብቅ እና በጨለማ በመግባት ሌሎቹ የቪኦኤ የአማርኛው ድምጽ አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች የሚያቀርቧቸውን የአመጽ ቅስቀሳዎች ሲያነቡ ቆይተዋልን? ምናልባትም እነዚህን ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች በመለየት በማሳመን የዘ-ህዋሀትን መምሪያ መስመር እንዲከተሉ ለማድረግ ታስቦ ነውን?

ማናቸውም የቪኦኤ ዘጋቢዎች ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦች የቪኦኤን ትክክለኛ ዘገባ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ድብቅ ዘገባዎችን፣ የኢዲቶሪያል ስብሰባዎችን እና ሌሎችን እንቅስቃሴዎች ሁሉ ለግርማ ብሩ በሚስጥር ማደል ላይ ይገኛሉን?

እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 በአድኃኖም፣ በብሩ እና በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛወው አገልግሎት እና በተመረጡ ሌሎች ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች መካከል ለሁለት ሰዓታት ያህል በቆየው ስብሰባ ምን ምን ጉዳዮች ተነስተው ተዳሰሱ? ተወደሱ? ስምምነት ተደረሰባቸው? ያልትፃፈ አግብኦ ተደረሰባቸው?

እኮ ምን?

በዚያ ስብሰባ ላይ ይፋ ለሆነ ጉዳይ ዓላማ ተብሎ የተመዘገበ፣ ፅሁፍ  ወይም ደግሞ ቃለ ጉባኤ ነገር ተይዞ እና ተዘጋጅቶ ነበርን? የሌለ ከሆነስ ለምን ምክንያት ነው እንዲያዝ ያልተፈለገው?

አድሃኖምና ብሩ ስብሰባው ላይ ስለ ቭኦኤ ግምገማ አቅረበው ነበር? የቭኦኤ ጋዘጤ ች ገስጠዉስ ነበር?

ከስብሰባው በኋላ በአድኃኖም/ብሩ ስብሰባ ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተብሎ የተዘጋጀ ሰነድ ነበርን? ሰነድ ከሌለ አግብኦ ተደርሶ ነበር?

በአድኃኖም፣ በብሩ እና በተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ዘጋቢዎች በሌሊት በጨለማ የተካሄደውን የሚስጥር ስብሰባ የቪኦኤ አመራር በውል ተገንዝቦት ነበርን?

የቪኦኤ አመራር እንደዚህ ያለ ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረባዎች ጋር ብቻ ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት የሚስጥር ስብሰባ እንዲካሄድ አውቆት መካሄድ እንዲችል በይፋ ግልጽ  በሆነ መልኩ አጽድቆት ነበርን?

አድኃኖም እና ብሩ ለምንድን ነው ከተወሰኑ የተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባለደረቦች ጋር ብቻ የተሰበሰቡት?

ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በሌሊት በሚካሄደው ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ ሌሎች የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች መሳተፍ እንዲችሉ ይፋ በሆነ መልኩ ወይም ይፋ ባልሆነ መንገድ ግብዣ ተድርጎላቸወ ነበርን?ከሆነም የጋበዙት አነማንናቸው?

የአድኃኖም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በካድሬዎቹ አማካይነት ግብረ በላ ለሆድ አዳሪ የሆኑ ስብዕናየለሽ ሰው መሳይ በሸንጎዎችን እየመለመለ EBCን በህሊናየለሽ ስብስቦች በመሙላት ላይ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 አድኃኖም እና ብሩ በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚስጥር እና በሌሊት በመገኘት ሚስጥራዊ የምልመላ ተልዕኮ ሲያራምዱ ነበርን? ነው ወይስ ደግሞ በEBC እንዳሏቸው ካድሬዎች ሁሉ በቪኦኤም ለመመልመል እንዲችሉ የማደፋፈር ንግግር ሲያደርጉ ነበር?

አድኃኖም እና ብሩ በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በሌሊት የሁለት ሰዓታት የፈጅ ስብሰባ ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር በማካሄድ ምን ዓይነት የየግል  ትርፍ ማግኘት ችለዋል?

ከአንድ ድብቅ ከሆነ፣ በጨለማ ከተካሄደ፣ በሳምንቱ መጨረሻ በሆነ ዕለት የፕሬስ ምርመራ በማካሄድ በአስከፊነቱ ከዓለምበአራተኛ ደረጃ ላይ በምትገኝ ሀገር (በተመሳሳይ መልኩ ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከምትገኝ ሀገር)  ቁንጮባለስልጣን ተወካዮች እና ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦች ጋር በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤትውስጥ ሚስጥራዊ ስብሰባ በማካሄድ ምን አዎንታዊ (ምናልትም በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ እንኳ) ምን ቁም ነገር ነገር ይገኛልተብሎ ታስቦ ነው?

የተወሰኑ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ሌሎች ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር ያካሄዱት ሚስጥራዊ፣ በጨለማ እና በሳምንቱ መጨረሻ ያደረጉት ስብሰባ  የቪኦኤን የሙያ እና የስነምግባር መርሆን እና የዩናይትድ ስቴትስን የፌዴራል ሕጎችን ጥሷልን?

በአድኃኖም፣ በብሩ እና በተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና በሌሎች ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦችየተካሄዱ ሚስጥራዊ ዝርዝር ጉዳዮች፣

በአድኃኖም፣ በብሩ እና በተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች መካከል እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት በሌሊት በድብቅ ስለተካሄደው ሁለት ሰዓታትን የፈጀ አስደንጋጭ እና ህሊናን የሚረብሽ ስብሰባ ጉዳይ በማስመልከት በወጣቱ ኢትዮጵያዊ የምርመራ ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በሆነው በአበበ ገላው በማያሻማ መልኩ ግልጽ ተደርጓል፡፡ የምርመራ ውጤቱም በሚከተሉት ተከታታይ አንቀጾች እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

እንደ አበበ የምርመራ ዘገባ፡

እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 አድኃኖም እና ብሩ በ330 አቬኑ በዋሺንግተን ዲ.ሲ ከተማ በሚገኘው የቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ በድብቅ በመግባት ከጥቂት የድርጅቱ የስራ ባልደረቦች ጋር ስብሰባ በማድረግ ያልተፈቀደ እና ስልጣንነት የሌለው የኢዶቶሪያል ስብሰባና ግምገማ  ምርመራ አካሂደዋል፡፡

ድብቁ ስብሰባ የተካሄደው በአፍሪካ ቀንድ ዋና ከፍል በሚገኘው የኢዲቶሪያል የስብሰባ ከፍል ውስጥ ሲሆን ስብሰባው ለሁለት ሰዓታት ያህል የዘለቀ ነበር፡፡

ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር የተካሄደውን ድብቅ ስብሰባ በዋናነት ያደራጀው እና ያስተባበረው የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የዜና አገልግሎት ሰራተኛ የሆነው ሰለሞን አባተ ሲሆን ከእርሱ ጋር በመሆን በትረ ስልጣን የተባለው ከትግርኛ ድምጽ አገልግሎት እንዲሁም ሁለት ቴክኒሻኖችን ጨምሮ ሰባት አባላት ያሉት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦች ቡድንን የያዘ ነበር፡፡

የቅዳሜ ሌሊቱ የሚስጥር ስብሰባው ዋና ዓላማ በቪኦኤ ጋዜጠኞች እና በአድኃኖም አገዛዝ መካከል ትብብር እና መተማመን እንዲፈጠር ከሚል ፍላጎት የመነጨ ነበር፡፡

በስብሰባው ላይ አድኃኖም እና ብሩ በኢትዮጵያ የሚሰራጩት የቪኦኤ ስርጭት ዘገባዎች ድምጸት እና ይዘታቸው ፍጹም በሆነ መልኩ እንዲለወጡ ለማድረግ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ በስውር ማስፈራራት እና ማሸማቀቅን በተላበሰ መልኩ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኗቸውን ሲያሳርፉ ተስተውለዋል፡፡

አድኃኖም እየተካሄደ ስለነበረው ስብሰባ ምንም ዓይነት ቃለ ጉባኤ እንዳይያዝ ወይም ደግሞ ምዝገባ እንዳይደረግ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

አድኃኖም ምንም ዓይነት ቃለጉባኤ በማይያዝበት እና ምዘገባም በማይደረግበት በዚያ የሚስጥር ስብሰባ ላይ ለቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ወሳኝ የሆኑ ትችቶች ለሚያቀርቡት እና የአመጽ ተግባራትን ለሚያካሂዱት ግንቦት ሰባትን ጨምሮ የስርጭት መድረክ መስጠት መንግስትን ከማወክ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ወቀሳውን በመግለጽ በምሬት አቅርቧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቪኦኤ አሉታዊ ትረካዎችን በማቅረብ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው በማለት ትችቱን አቅርቧል፡፡

አድኃኖም በስብሰባው ላይ ለተገኙት የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ዲስኩር ማሰማቱን ቀጥሎ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ሌሎች ዘጋቢዎች እና  የሜዲያ ሰራተኞች ሁሉ አሉታዊ ትረካ እና ሀሳቦችን ለአየር ፍጆታ ከማቅረብ ይልቅ በአዎንታዊ ልማቶች ላይ ትኩረት በማድረግ መዘገብ አለባቸው በማለት ሙሉ የትዕዛዝ ሰጭነት ድምጸቱን በይፋ አስቀምጧል፡፡

አድኃኖም ዘ-ህዋሀት በየጊዜው ከቪኦኤ ውስጣዊ የስራ እንቅስቃሴዎች ዘገባ እንደሚደርሰው ፍንጭ በመስጠት ዲስኩሩን አሰምቷል፡፡

አድኃኖም የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች እራሳቸውን እንዲመረምሩ እና ወደ ህሊናቸው እንዲመለሱ ምክር (ትዛዝ) ሰጥቷል፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ስለወያኔ አገዛዝ እና ስለሚያከናውናቸው ተግባራት የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች አዎንታዊ ትረካ እና አስተየያቶችን የሚዘግቡ ከሆነ አስፈላገውን ድጋፍ እና እርዳታ እንደሚያደርጉ ዝግጁ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

አድኃኖም ጋዜጠኞቹ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ እውነታውን እራሳቸው በዓይናቸው ማየት እንዲችሉ ግብዣ አቅርቧል፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ለቪኦኤ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሩን በርገድ አድርጎ ምንጊዜም ይጠብቃችኋል በማለት ዲስኩራቸውን አሰምተዋል፡፡

ቪኦኤ እና አኔ፣

ባለፉት አስር ዓመታት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዘ-ህዋሀት በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ላይ ሲያካሄደው የቆየውን ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ጥላሸት መቀባት እና ግልጽ የሆነ ጣልቃገብነት አላካሄደም ብለው የሚከራከሩ እራሴን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ አላምንም፡፡

አሁን በህይወት በሌለው እና ቁንጮ አምባገነነን በነበረው የዘ-ህዋሀት መሪ መለስ ዜዘናዊ በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ የማሸማቀቅ፣ የማስፈራራት እና ጣልቃ የመግባት አካሄዶቹን በሚመለከት ቪኦኤን ለመከላከል በርካታ ትችቶችን ስጽፍ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 4/2015 ከኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ጋር በተያያዘ መልኩ የተወሰኑ አባላትን ያካተተ ኢትዮጵዊ ቡድን በአንድ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጋዜጠኛ ላይ ተሰንዝሮ የነበረውን ጥቃት በጥብቅ  መቃወም ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

በፕሬስ ነጻነት ድንቁርናቸው እና የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢ ጋዜጠኛን ባስፈራሩት እና በማሸማቀቅ ወንጀለል በሰሩት ላይ እንዲሁም በጋዜጠኛው ሙያ ላይ ጣልቃ በገቡት ሰዎች ላይ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

አድልኦ የሚሳዩ ቢሆንም፣ ታማዕኒነት የሌላቸው ወይም ደግሞ የሙያ ስነምግባር ቢኖርባቸውም እንኳ ማንም ቢሆን በቪኦኤ ጋዜጠኞች ላይ ጣልቃ የመግባት መብት እንደሌለው አውጀ ነበር፡፡

በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ዘንድ ፍትሀዊ ያልሆነ ወይም ደግሞ አድልኦ የሚታይበት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የዘ-ህዋሀት አገዛዝን ከመቃወም ይልቅ በቪኦኤ ህግ እና ደንብ መሰረት ቅሬታን ማቅረብ እንደሚቻል ለኢትዮ-አሜሪካውያን ወገኖቼ ተማጽዕኖዬን አቀርባለሁ፡፡

ለሴቷ ዳክዬ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለወንዱ ዳክዬም ጥሩ ነው ይላሉ አሜሪካኖች ሲተርቱ  ፡፡

አድኃኖም እና ብሩ በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘገባ ወይም በዘጋቢ ጋዜጠኞች ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነ ቅሬታቸውን ስርዓቱን እና የዕዝ ሰንሰለቱን ተከትለው ለዩናይትድ ስቴተስ የመንግስት መምሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡

የተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎችን እና የስራ ባልደረቦችን ብቻ ለይቶ በመጋበዝ በአንድ የሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት በሆነ በሌሊት ሚስጥራዊ ስብሰባን በማካሄዱ ምክንያት በመበሳጨት የቪኦኤን ዋና መስሪያ ቤት የመውረር መብት የላቸውም!

እስቲ ይህንን ጉዳይ ፍጹም በሆነ መልኩ ግልጽ ላድርግ፡ አድኃኖም እና ብሩ በስቱዲዮ ቃለመጠይቅ ለመስጠት ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ቢመጡ በእኔ በኩል ፍጹም ችግር የለብኝም፡፡

ከቪኦኤ ዘጋዎች ጋር የመነጋገር እና ሀሳባቸውን የመግለጽ መብት አላቸው፡፡

“የምንንቃቸው ሰዎች ሀሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት እንዲኖራቸው እምነት የሌለን ከሆነ እንዲያውም በእራሱ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ መብት ላይ ምንም ዓይነት እምነት የለንም” ከሚለው የፕሮፌሰር ኖዓም ቾሚስኪ ምልከታ ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡

ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ ሁኔታ ላይ በምንመጣበት ጊዜ ቀደም ሲል ስናውቃቸው የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ለመናገር መብቶቻቸው ትልቅ ዋጋ በመስጠት ሀሳቦቻቸውን በነጻነት መግለጽ እንዲችሉ ለማድረግ ጥብቅና መቆም አለብኝ፡፡

በነጻነት ከመግለጽ አንጻር የእኔ ፍልስፍና እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡ የተሻለው ሀሳብ አሸናፊ ይሁን! አሸናፊዉን ሀዝብይዳኘው

የእኔን ለዚህ መርህ ያለኝን ቁርጠኝነት እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘ-ህዋሀት መሪ  መለስ ዜናዊ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ያደርግ የነበረውን ንግግር ያለምንም ጣልቃገብነት እና ማቋረጥ መቀጠል አለበት በማለት ሽንጤን ገትሬ በመከራከር አሳይቸው የነበረው ጥሩ ትግል ለዚህ ጉዳይ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች 90 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ ታፍኖ ባለበት ሁኔታ የመለስ ዜናውን መብት አንዴት ትጠብቃለህ ብለው ይዛአኑ ብዙ ሰዎች ነበሩ ፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ቃለመጠይቅ ለመስጠት ወይም ደግሞ ይፋ ውይይት ለማድርግ ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ለመሄድ የሚፈልጉ ከሆነ ለእነርሱ ብርታቱን ይስጣቸው፡፡

የእኔ ችግር ይኸ የሚስጥር ስብሰባ፣ የሌሊት ስብሰባ፣ ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር የሚደረገው ስብሰባ፣ የማይቀዳ እና የማይዘግብ ስብሰባ፣ ምንም ዓይነት የተፈቀደ ስልጣን ሳይኖር የሚካሄድ ስብሰባ፣ ምንም ዓይነት ምዝገባ ሳይደረግ የሚካሄድ ስብሰባ፣ ምንም ዓይነት ቃለ ጉባኤ ወይም ጽሁፍ የሌለው ስብሰባ እና በሚስጥር እጅ በመጨባበጥ ብቻ እራስን ነቅንቆ እና በዓይን ጠቅሶ የሚጠናቀቅ ስብሰባን ከማካሄድ ላይ ነው፡፡

የነጻ ፕሬስ ህልዮት እንደ ጠባቂ ውሻ መታየት አለበት ፡፡

የጠባቂን ውሻ ተመሳስሎ ከነጻው ፕሬስ ጋር ስጠቀም እንደ አዳኝ ውሻ በጥንቃቄ በማነፍነፍ የመንግስትን ዕኩይ ምግባር፣ በሙስና መዘፈቅ፣ ቅሌት እና ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ ያለአግባብ መጠቀምን ፈልፍሎ በማውጣት ማጋለጥ ማለቴ ነው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ የቪኦ ጋዜጠኞች በስልጣን ላይ ያሉትን በመመርመር ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የመሆን መብትን ያጎናጽፋል፡፡ ፕሬሱ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ፈልፍሎ በማውጣት ግልጽ በማድረግ እና የማህበረሰቡን አስተሳሰብ በመለወጥ የእራሱን ጠባቂ ውሻ መጠቀም ይኖርበታል፡፡

የፕሬስ ጠባቂ ውሾች አልጋ ላይ በመተኛት ወይም ደግሞ በቦርድ ክፍል ውስጥ ከፕሬስ ቀበኛ ተኩላዎች ጋር በሚስጥር ስብሰባ በማካሄድ የሚያገኙት የንግድ ትርፍ ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡

በእርግጥ በክፍል 4 ስራ የቪኦኤ የአድማጮች የጋዜጠኝነት መብቶች አዋጅ በትክክል ያስቀመጠው ይህንኑ ጉዳይ ነው፡፡

የቪኦኤ ጋዜጠኞች የመጀመሪያው ታማኝነታቸው ለአድማጮቻቸው ሲሆን አድማጮችም እራሳቸውን ከመደበቅ ነጻ መሆን መቻል አለባቸው፡፡

የቪኦኤ ጋዘዜጠኛ ዋና ስራ የተደበቁትን ነገሮች ፈልፍሎ ማውጣት እንጅ በአልጋ ላይ በምቾት ተጋድመው የሚዋሹትን ውሸት በመደበቅ መዘገብ አይደለም፡፡

ለአድኃኖም፣ ለብሩ እና ለተመረጡ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አግልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች እንዲሁም ለሌሎች ዘጋቢዎች እና ሰራተኞች በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በድብቅ በመሄድ የፌዴራል ሕጉን እና የቪኦኤን የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር በመጣስ ሚስጥራዊ የሆኑ የባለስልጣኖችን እና ባልስልጣን ያልሆኑትን የግል ትርፍ ማሳደድ ብቻ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢ ጋዜጠኛ ላይ የተፈጸመው ማሸማቀቅ እና በአካል ላይ ጉዳት ለማድረስ በተደረገው ሙከራ፣ በአድኃኖም እና ብሩ ከቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የተመረጡ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር በሌሊት ባደረጉት ስብሰባ እንዲሁም በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ላይ በሚደረግ ሁከት መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት አላየሁም፡፡

አድኃኖም እና ብሩ በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በጨለማ በመገኘት ያደረጉት ድርጊት እና ባለፈው ሀምሌ በቪኦኤ ጋዜጠኛ ላይ ከኋይት ሀውስ ቅጥር ግቢ ውጭ የተደረገው የአመጽ ድርጊት ሁለቱም የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እነርሱ በሚፈለጉት አኳኋን እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉ ጠቃሚ የሆኑ የወሮበላነት ድርጊቶች ናቸው፡፡

ለበርካታ ዓመታት ለቪኦ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጥብቅና በመቆም ላደረግሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ሁሉ ኩራት ይሰማኛል፡፡

ለቪኦኤ ጥብቅና የምቆምበት ምክንያት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝን በመቃወም ከተቃዋሚዎች ጎን በመቆማቸው ምክንያት አይደለም፡፡ ቪኦኤ በወያኔ ላይ ተጻራሪ ሆኖ በመቆሙ ምክንያትም አይለደም የምቃወመው፡፡

ምንጊዜም ቪኦኤ በአደጋ ላይ በወደቀ በእንዳንዷ ጊዜ ሁሉ ጥብቅና እቆምለታለሁ ምክንያቱም አብዛኞቹ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ስራዎቻቸውን ሙያዊ ስነምግባርን በተላበሰ መልኩ አክብረው በታዕማኒነት የሚሰሩ ትንታጎች በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡

እውነት ለመናገር በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ልስማማባቸው የማልችልባቸው በርካታ ዘገባዎች አሉ፡፡

የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እንደ ዘጋቢ በእኔ በጣም ወገናዊነት በሆነው አይነት አዘጋገብ መሄድ እንደሌለበት እገነዘባለሁ፡፡

የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ሙያዊ የሆነ ስራቸውን ሙያዊ ደረጃቸውን ጠብቀው በመስራታቸው ትችት አቅርቤባቸው አላውቅም፡፡

እኔ በጣም ወገናዊ የሆንኩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ላመንኩበት ነገር በምንም ዓይነት መልኩ ግንባሬን የማላጥፍ ብሆንም ቅሉ ስራቸውን በታማኝነት ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ታላቅ ክብር አለኝ፡፡

የቪኦኤ የጋዜጠኝነት ስነምግባር ዘጋቢዎች ከፍተኛ በሆነ መልኩ ከጋዜጠኝነት ሙያ ስነምግባር እና ተማዕኒነት ጋር ጥብቅ ቁርኝ በመፍጠር ታማኝነትን በማሳደግ የአሜሪካንን ድምጽ ውጤታማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ሙያቸውን የጋዜጠኝነት ስነምግባር በሚፈቅደው መሰረት አክብረው የሚሰሩ እስከሆኑ ድረስ በምንም ዓይነት መልኩ ትችት አቅርቤባቸው አላውቅም፡፡

ሆኖም ግን የቪኦኤ ጋዜጠኞች የእራሳቸውን የጋዜጠኝነት ስነምግባር አክብረው እየሰሩ በሚገኙበት ጊዜ ሌሎች ትችት ሲያቀርቡባቸው እና ሲያሸማቅቋቸው በማይበት ጊዜ ጥብቅና እቆምላቸዋሁ፡፡

እንግዲህ እ.ኤ.አ በሀምሌ 2011 አሁን በህይወት የሌለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በቁጣ ገንፍሎ የጭቃ ጅራፉን ሲያጮህ ይደረግሁት ይህንኑ ነበር፡፡

መለስ በይፋ እና ስብዕናቸውን በማንቋሸሽ የቪኦኤን ቦርድ አመራሮች በማስፈራራት የቪኦኤን ድምጽ የአማርኛው አገልግሎትን ስርጭት ለማፈን ሙከራ ባደረገበት ጊዜ ሽንጤን ገትሬ ተከራክሪያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛ አገልግሎቱን አደገኛ ቅስቀሳ አካሂዶ የዘር ፍጅት የእልቂት እሳት እንዲለኮስ ካደረገው ሀገሪቱን ካወደመው ከሩዋንዳው ሬዲዮ ሚሌ ጋር እኩል አድርጎ አቀርቦት ነበር፡፡ ይህንኑ በማስመልከት መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ከበርካታ ዓመታት አንጻር ስንመለከተው እንደቆየነው ሁሉ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዝቅተኛ የሆኑ የጋዜጠኝነት መሰፍርቶችን በማያሟላ መልኩ በሩዋንዳ እንደነበረው እንደ ሬዲዮ ሚሌ ያሉ አስከፊ ተሞክሮዎችን እንዳለ በመቅዳት በአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ድርጊት ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ እምነት ይዘናል“ ብሎ ነበር፡፡

መለስ ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ የሚሰራጨው የአሜሪካ ድምጽ ስርጭት ሽፋን እንዳያገኝ በሚል ዕኩይ ምግባር እንዲታፈን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የቪኦኤን ስርጭት ማፈኑን ያለምንም ሀፍረት አፉን ሞልቶ በተናገረበት ጊዜ እኔ ጠንካራ በሆነ መልኩ ለቪኦኤ ጥብቅና በመቆም ተከራክሪያለሁ፡፡ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ዛሬ ይህንን የምታውቁ ለመሆኑ የማውቀው ነገር የለኝም፣ ሆኖም ግን የአሜሪካ ድምጽ ቪኦኤ በዩኤስ አሜሪካ ሕግ እንዲሰራጭ አይፈቀድለትም፡፡ ይልቁንም በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሳይሆን ወደ ሌሎች ሀገሮች እንዲሰራጭ ይፈቀድለታል መክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ያንጸባርቃልና፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት በግልጽ ሊታወቅ በሚችል ምክንያት በተለይም ከድሮው አገዛዝ ጋር ግንኙነት ካላቸው ሰዎች ጋር የተቆራኝ የጥቃት በሽታ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዩናይትድ ቴትስ ፖሊሲ አንድ ገጽ በመውሰድ ቪኦኤ ለኢትዮጵያ መልካም አይደለም ማለት እንችላለን“ በማለት አምባገነናዊ ዲስኩሩን አጠቃሏል፡፡

ለአበበ ገላው የምርመራ ዘገባ ውጤት የቪኦኤ ምላሽ፣

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም ቅሉ ቪኦኤ በአበበ ገላው ለቀረቡት የክስ  እውነታዎች ምላሽ መስጠቱን ተቃሟል፡፡ የአበበ ገላው የምርመራ ዘገባ ጥቂት የአመራር እና የወንጀል ባህሪነት ያላቸውን ጉዳዮች አንስቷል፡፡

አበበ ገላው ላቀረበው ዘገባ የቪኦኤ የስራ አመራር ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

የምርመራ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ እና የክትትል የኢሜይል የጽሁፍ መልዕክት ቢያደርግም ቪኦኤ ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠት በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ለአድኃኖም/ብሩ የሌሊት ድብቅ ስብሰባ ማብራሪያ ምላሽ አልሰጥም ብሏል  ፡፡

ቪኦኤ አስተያየት ሳይሰጥ የአበበን ዘገባ ማስተባበል አይችልም፡፡

የአድኃኖም/ብሩ የሌሊት ድብቅ ስብሰባ ከቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ጋር፣

አድኃኖም እና ብሩ እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 ድብቅ በሆነ መልኩ በሌሊት ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደራባዎች ጋር ስብሰባ በማካሄዳቸው የፌዴራል መንግስቱን ሕግ ጥሰዋልን?

የተመረጡት የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ከአድኃኖም/ብሩ ጋር በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት በሌሊት በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ስብሰባ በማካሄዳቸው የፌዴራል መንግስቱን ሕግ እና የቪኦኤን የጋዜጠኝነት የስነምግባር ሕግ ጥሰዋልን?

በተለይም በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋበዎች እና የስራ ባልደረቦች እና በአድኃኖም/ብሩ የሌሊት ሚስጥራዊ ስብሰባ በመካሄዱ ምክንያት በ22 U.S.C. 6202 (c) የተደነገገውን ሕግ ይጥሳልን?

በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች እና በአድኃኖም እና በብሩ መካከል በተካሄደው ሚስጥራዊ የሌሊት ስብሰባ የቪኦኤን የጋዜጠኝነት ስነምግባር እና ተሞክሮዎችን  (11 – 023 እና 11 – 024) ይጥሳልን?

በቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር ያደረጉት የሌሊቱ ሚስጥራዊ ስብሰባ የኤክሴኪዩቲቭ ብራንች ሰብፓርት ኢ/Executive Branch Subpart E (በ 5 C.F.R Part 2635 የተደነገገውን እና በ76 FR 38547 (እ.ኤ.አ ሀምሌ 1፣ 2011) እንደተሻሻለው)) እና የሌሎችን የፌዴራል ሕጎችን የሰራተኞች የሙያ ስነምግባርን ያካትታልን?

የቪኦኤ ቻርተር እና አሰተዳደራዊ ሕጉ፣

የቪኦኤ የአሰራር ሂደት እና ተግባራት በመንግስት ሕግ 94-350 ክፍል 206 (በ22 U.S.C 6202 እንደተሻሻለው) ግልጽ በሆነ መልኩ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

22 U.S.C 62020 (c) 10 ዋና ዋና መርሆዎችን በማካተት እንዲህ የሚል ትዕዛዝን በግልጽ ያስቀምጣል፡

…የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስርጭት ሰራተኞች በሁሉም ስራዎቻቸው ለትክክለኛ እና ነባራዊ ለሆኑ ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት አለባቸው፡፡ ለዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ወግነው መናገር የለባቸውም፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስርጭት ሰራተኞች ከግል የሜዲያ ተቋማት በተለዬ መልኩ ለእነርሱ ተብሎ ለሰራተኞቻቸው የተሻሉ ነገሮችን ከዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ባለስልጣኖች ወይም ደግሞ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት የተለዬ ድጋፍ ወይም እርዳታ ሊቀበሉ አይችሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቪኦኤ ባለሙያዎች የድርጅታቸውን ታማዕኒነት በጥንቃቄ በመጠበቅ በስርጭቶቻቸው ያልተመጣጠነ ዘገባን ወይም ደግሞ አድሎአዊነት ያላቸው ስርጭቶችን በማስወገድ ለከፍተኛ ልቅና ለመስራት ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካ ድምጽ ዓለም በግጭት ውጥረት ውስጥ ወድቃ ባለችበት እና ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ፍጻሜ በኋላ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተልዕኮውን መወጣት ይኖርበታል፡፡ ትክክለኛ፣ የተመጣጠነ እና የተሟላ መረጃ ለዓለም ሕዝብ ማድረስ እና በተለይም ደግሞ ብሄራዊ ጥቅምን ባካተተ መልኩ ትክክለኛ መረጃዎች  በማሰራጨት በዴሞክራሴ እና በነጻነት ለሚያምኑ ዜጎች ሁሉ የትኩረታቸው እና የተስፋቸው ምንጭ ነው፡፡

የኤክሴኪዩቲቭ ብራንች ሰብፓርት ኢ/Executive Branch Subpart E (በ 5 C.F.R Part 2635 የተደነገገውን እና በ76 FR 38547 (እ.ኤ.አ ሀምሌ 1፣ 2011) እንደተሻሻለው)) የፌዴራል ሰራተኞች ስራዎቻቸውን ከአድልኦ በጸዳ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ የተለዩ ሕጎችን ያጎናጽፋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ሰራተኞች ከአድልኦ ነጻ የመሆን ጉዳይ ከጥያቄ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ጉዳዮችን በማንሳት መሰረት ሊሆን ይችላል፡፡

የቪኦኤ የጋዜጠኝነት ስነምግባር እና ተሞክሮዎች (የጋዜጠኝነት ሕግ)

የቪኦኤ ጋዜጠኞች ሕግ በቪኦኤ ዘጋቢዎች እና ሰራተኞች ላይ በርካታ ግዴታዎችን ይጥላል፡፡

ሕጉ እንዲህ በማለት በግልጽ ይደነግጋል፡

ቪኦኤ የተለዬ ፍላጎት ላላቸው ቡድኖች የውጭም ይሁኑ የሀገር ውስጥ የስርጭት መድረኩን በመጠቀም ለእራሳቸው ሀሳቦች ማራመጃ ለማድረግ ለሚጥሩት ሁሉ የተለዬ ትኩረት በመስጠት የሚያደርጉትን ጥረት ሁሉ ያስወግዳል፡፡ ይህ በሁሉም ፕሮግራሞች እና ክፍሎች ላይ ሀሳብን ወይም ደግሞ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠትን ጨምሮ፣ በደብዳቤዎች ላይ መወያየትን፣ የአድማጮች አስተያየትን ወይም ደግሞ የስልክ ጥሪዎችን ሁሉ በማካተት ተገባራዊ ይደረጋል…

…የቪኦኤ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ዜናዎችን እና የፊቸር ፕሮግራሞችን የሚሰሩ ሰራተኞች ሁሉ ወገንተኝነትን ከሚያራምዱ ማናቸውም ድርጊቶች ሁሉ እራሳቸውን ማስወገድ አለባቸው…

…ከእነዚህ የጋዜጠኝነት ስነምግባሮች እና መርሆዎች በተጨማሪ የቪኦኤ ሰራተኞች በስራ እና ከስራ ውጭ በሁለቱም በኩል የሚገኙት ሰራተኞች የአሜሪካንን ማህበረሰብ ድምጽ የሚያንጸባርቁ ይሆናሉ፡፡

እነዚህ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ከሆነው የጋዜጠኝነት የስነ ምግባር ሙያ እና ታማዕኒነት ጋር ሙሉ በሙሉ ይቆራኛሉ፡፡ የቡድን ስራን ለማራመድ፣ ለመልካም ነገር መስራትን፣ የሲቪል ዲስኩሮችን ለማሰማት  እና በስራ ቦታቸው ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በዓለም ላይ የቪኦኤ ድምጽ ታማዕኒነት ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የውጭ ተልዕኮ ድንጋጌ (22 U.S.C. 4301-4316) የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ እና ብሄራዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ የውጭ ተልዕኮ ተግባራቱን ይቆጣጠራል፡፡

አድኃኖም እና ብሩ ከተመረጡ የቪኦኤ ሰራተኞች ጋር ያልተፈቀደን ሚስጥራዊ ስብሰባ በማካሄዳቸው ማናቸውንም የፌዴራል መንግስቱን ሕጎች ጥሰዋልን?

የተመረጡት የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በመሰብሰብ ከአድኃኖም እና ከብሩ ጋር ባልተገለጹ ጉዳዮች ላይ በሌሊት ውይይት በማድረጋቸው ማንኛውንም የፌዴራል መንግስቱን ሕጎች ጥሰዋልን?

እ.ኤ.አ የ1978 የዋና ተቆጣጣሪ/Inspector General Act (OIG) ድንጋጌ ፣ የ1980 የውጭ አገልግሎት ድንጋጌ እና የ1998 የውጭ ጉዳይ ማሻሻያ እና እንደገና የማዋቀር ድንጋጌን በሚመለከት የመንግስት መምሪያን እና የስርጭት ቦርድ ገዥን/Broadcasting Board of Governors አጠቃላይ በሆነ መልኩ የመመልከቱን ኃላፊነት ለOIG ተሰጥቷል፡፡

22 U.S.C ክፍል 3929 (b) የቪኦኤን የስርጭት ቦርድ አመራር፣ የዓለም አቀፍ የስርጭት ቢሮን አስተዳደራዊ ተግባራት እና የውጭ አገልግሎት እና ሌሎችን በመንግስት መምሪያ ስር የሚንቀሳቀሱትን የስራ ክፍሎች የአሰራር ሂደት ሁሉ ስልታዊ በሆነ መልኩ እንዲከታተለው እና እንዲገመግም የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ለጠቅላላ ምርመራ/Inspector General ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

የOIG የመንግስት መምሪያ የምርመራ ቢሮ የወንጀል፣ የሲቪል እና አስተዳደራዊ የሆነ የስነምግባር ጉድለቶችን እና ከBBG ፕሮግራሞች አሰራሮች ውሱን የሆኑ ውንጀላዎች፣ ዘገባዎች ወይም ደግሞ ሌሎች ህጎች ወይም ደንቦች መጣሳቸውን የሚገልጹ ነገሮች ላይ ምርመራ ያካሂዳል፡፡

የአድኃኖም/ብሩ ሚስጥራዊ ስብሰባ ከOIG የመንግስት መምሪያ የምርመራ ክልል ውስጥ ነውን?  

ማነው የሚያንቀላፋው ቭኦኤ ዉስጥ? 

ቪኦኤ ወደ አራት ደርዘን የሚጠጉ ቋንቋዎችን ያሰራጫል፡፡

እ.ኤ.አ በ1942 ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ቪኦኤ አንድ ነገር በመስራቱ ወይም ባለመስራቱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጩ ዓለም ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡

የጠቅላይነት ባህሪን በተላበሱ አገዛዞች ዘንድ ቪኦኤ በሰባት አስርት ዓመታት ታሪኩ ውስጥ የአሜሪካ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ነው የሚል ጫጫታ የበዛበት ትችት ይቀርብበታል፡፡

ቪኦኤ እና ዘጋቢዎቹ በአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ዘንድ የህዝባዊ ወያኔ ወሮበላ የዘራፊዎች ቡድን ስብስብን ጨምሮ ማቆሚያ የሌለው የማሸማቀቅ እና የማስፈራራት ዕኩይ ምግባር ቀጥሎ ይገኛል፡፡

በቪኦኤ አዘጋገብ ላይ የሚሰጥ ትችት ለቪኦኤ አዲስ ነገር አይደለም፡፡

ፍጹም አዲስ የሆነው እና ያልተጠበቀው ነገር ቢኖር የአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ተስፋቸውን ማጠናከራቸው እና የተከበረውን የቪኦኤ ቅዱስ የሜዲያ ቦታ ደፍረው በመግባት ወረራ ማካሄዳቸው እና ከቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር ስብሰባ በመቀመጥ ያለምንም የሕግ ተጠያቂነት የቪኦኤ ጋዜጠኞች ይህን ዘግቡ ያንን አትንኩ እየተባሉ ትዕዛዝ እና መመሪያ መሰጠት የመጀመሩ ጉዳይ ነው፡፡

ቀጣዩ ነገር ምንድን ነው?

የአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ከቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር በጨለማ የሚስጥር ስብሰባ በአፍሪካ አምባገነኖች የሚወደዱ ወይም የማይወደዱ ጉዳዮችን በመለየት ይህንን ዘግቡ፣ ያንን እንዳትዘግቡ በማለት በሰጡት መመሪያ እና ትዓዛዝ ትርፍ አግኝተውበታልን?

ቪኦኤን ለመምታት ከተፈለገ የተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎችን እና የስራ ባልደረቦችን ለይቶ ማውጣት እና እነዚህ ጋዜጠኛ ተብዬዎች ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚስጥር ዘልቀው እንዲገቡ እንዲጋብዟቸው በማድረግ እነርሱ የሚፈልጉትን ይህንን ዘግቡ፣ ያንን እንዳትዘግቡ ለማለት ይቻላል ተብሎ ታስቦ ነውን?

ነው ወይስ ደግሞ የቪኦኤ ዘጋቢዎችን እና የስራ ባልደረቦችን ከአዲስ አበባ ማስወገድ ካልተቻለ እዚሁ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ዋሺንግተን ዲ.ሲ በመምጣት ከምንጩ ማድረቅ ይቻላል ተብሎ ታስቦ ነው?

አድኃኖም እና ብሩ ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት በጨለማ በመግባት ሚስጥራዊ ስብሰባ ማካሄዳቸው መጥፎ አጋጣሚን ከመፍጠር ያለፈ የሚፈይድላቸው አንዳችም ነገር የለም፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ሕግ ቪኦኤ ከማንኛውም የውጭ መንግስት ተጽዕኖ ነጻ መሆን እንዳለበት ብቻ አይደለም ግልጽ በሆነ መልኩ የሚደነግገው፡፡ ሆኖም ግን ከእራሱ ከዩኤስ መንግስትም ነጻ እንዲሆን በግልጽ ደንግጓል፡፡ ያ ነው እንግዲህ የቪኦኤ ቦርድ እና የስርጭት ክፍሎቹ በአንድነት በመንግስት መምሪያ ስር በጅምላ እንዳይተዳደሩ የሚለው ድንጋጌ በዋናነነት እንዲወጣ የተደረገበት ምክንያት፡፡ ለዚህም ነው በመንግስት መምሪያ እና በBBG ጋዜጠኞች መካከል የጋዜጠኝነትን ታማዕኒነት ለማረጋገጥ ሲባል በመካከላቸው የእሳት ግድግዳ ታንጾ የሚገኘው፡፡

አድኃኖም እና ብሩ እ.ኤ.አ መስከረም 26/2015 በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት፣ በጨለማ እና በሚስጥር ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ዘልቀው በመግባት ከብዙ ዘመናት በፊት በአሜሪካ ኮንግረስ የተገነባውን የእሳት ግንብ (firewall) እንዴት አፍርሰው ለመግባት ቻሉ?

አድኃኖም፣ ብሩ እና የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂዎች ካልሆኑ በስተቀር የአፍሪካ አምባገነን ወሮበላ ዘራፊዎች አንደጎርፍ ወደ ቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ወደ ዋሺንግተን በመምጣት የቪኦኤ ጋዜጠኞችን እና ዘጋቢዎችን እጃቸውን እንዲሰጡ ከማስፈራራት እና ከማሸማቀቅ ወደኋላ እንደማይሉ ግልጽ ነው ፡፡

ፍጹም፣ ፍጹም መፈቀድ የለበትም!

በአድኃኖም፣ በብሩ እና በተወሰኑ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች መካከል በተደረገው ሚስጥራዊ ስብሰባ በጣም አዝኛለሁ፡፡

በቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የፕሬስ ነጻነትን በመደፍጠጥ እና በፕሬስ ምርመራ በዓለም በአራተኛነት ደረጃ ላይ የሚገኝ አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣኖች መካከል ሚስጥራዊ ስብሰባ የመደረጉን ጽንሰ ሀሳብ በእራሱ ስሰማ የሆድ ቁርጠት ይሆንብኛል፡፡

እንደዚህ ዓይነቱ የቀልድ ስብሰባ ቪኦኤ ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት በፕሬስ ነጻነት ሕግ የተቋቋመበትን መሰረታዊ መርሆዎች የሚያደበዝዝ እና የሚያጠፋ ዕኩይ ድርጊት መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

ስለ አሜሪካ ድምጽ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ አደርጋለሁ ማለት የሚያሳፍረ ኝ ጉዳይ አይደለም፡፡

በበርካታ ህጸጾች ምክንያት ፍጹም ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡

ከቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የፕሮግራም ቅድሚያ አሰጣጥ ሀኔታ ጋር አልስማማም፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ያሉ የኢትዮጵያ አድማጮች ሁልጊዜ በየምሽቱ ለአንድ ሰዓት በሚተላለፈው የአየር ሰዓት ስርጭት በአሜሪካ ስለሚካሄዱ የስፖርት ክስተቶችን ከማቅረብ ይልቅ ዜናዎችን፣ መረጃዎችን እና በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረጉ ስላሉ ነገሮች ትንታኔዎችን እያቀረቡ ማሰማት የህብረተሰቡን የፖለቲካ እና የዕውቀት ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የተሻለ ጠቀሜታን ይሰጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሆኖም ግን  ቪኦኤ በአሜሪካ ስለባህል እና ሌሎች ክስተቶች በቂ መረጃ መስጠት እንዳለበት ሕጉ ይጠይቃል፡፡

በእርግጥ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ስለዩኤስ አሜሪካ ባህል እና ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ አድማጮች በማቅረብ ታላቅ የሆነ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ብዙሀን ዜናዎችን፣ ሀሳቦችን፣ እና ትንታኔዎችን ለኢትዮጵያውያን አድማጮቹ በማቅረብ መልካም ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በቪኦኤ ላይ ማስፈራራት፣ ማሸማቀቅ እና በአምባገነኖች እና በወሮበሎች በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ቪኦኤን በሙስና ጠልፎ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ ድምጼን ከፍ አድርጌ በመጮህ ላለፉት በርካታ ዓመታት ስሟገት ቆይቻለሁ፣ አሁንም በተጠናከረ መልኩ የምቀጥልበት ይሆናል፡፡

በአድኃኖም/ብሩ ዕኩይ ምግባር አንባቢዎቼ እንዲበሳጩ እና የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎትን እንዲያወግዙ ፍላጎት የለኝም፡፡

ከተቀናቃኞቼ ጋር ስምምነት ለማድረግ እንኳ ፍትሀዊ ጨዋታ መጫወት አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

አድኃኖም እና ብሩ በሳምንቱ መጨረሻ ዕለት፣ በሚስጥር እና በድቅድቅ ጨለማ፣ ከተመረጡ የቪኦኤ ዘጋቢዎች እና የስራ ባልደረቦች ጋር ለሁለት ሰዓታት የፈጀ ስብሰባ ለምን እንዳደረጉ አሳማኝ የሆነ ምክንያት ላገኝለት አልችልም፡፡

ምናልባትም እኔ እንደማስበው አንድ ድብቅ ነገር አለ?  ያንን ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡

ይህንን ጽሁፍ እያዘጋጀሁ ባለሁበት ጊዜ የትም የት ይሁኑ አሜሪካ ለቀሪው ዓለም የነጻ ፕሬስ ነጻነት ተምሳሌት ቀንዲል ሆና ዓለምን እየመራች ባለችበት ሁኔታ በቪኦኤ ዋና መስሪያ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ፣ በሳምንቱ የመጨረሻ ዕለት፣ በሚስጥር እና እዚያ ግቢ ውስጥ መግባታቸው እንዳይታወቅ የእጅ አሻራቸው እና የእግር ዱካቸው ሊለይ በማይችልበት መልኩ ተዘጋጅተው ህገወጥ ስብሰባ ያደረጉት የቪኦኤ ድምጽ ኋላቀር የፕሬስ ነጻነት ቀበኞች ይኸ ዕኩይ ድርጊታቸው ለዘላለሙ መጥፋት አለበት የሚል ፍጹም የሆነ አመክንዮ አለኝ፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 30 ቀን 2008 .

Filed in: Amharic