>

የኮሚኒኬሽን ሚ/ሩ እቶ ጌታቸው ረዳ “ጨረቃ ላይ” ጥለውን ነጎዱ [ታምሩ ገዳ]

በርካታ ኢትዮጵያኖችን ለ ወከባ፣ ለ አሰራት እና በመጨረሻም ለሰደት የዳረጉት አወዛጋቢዎቹ የጸረ ሽብር እና የፕሬስ ህጎች በገዢው መንግስት በኩል እንከን የለሽ መሆናቸውን ቢነገረንም ዛሬም ድረስ ብዙዎችን ከአገዛዙ ጋር ሆድ እና ጀርባ አንዳደርጋቸው ይገኛል።ችግሩም በቅርቡም የፈታል ተብሎ አይጠበቅም።

Getachew Redaታዲያ ባለፈው እሁድ የጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፈለ ጊዜ (ዶቼ ቬሌ ) “ በአትዮጵያ ሃሳብን በነጻ የመግልጽ መብት፣የ ፕሬስ ህጉ እና በጸረ ሽብር ሕጉ ዙሪያ” አራት የተለያዩ እንግዶችን ለንትርክ (Cross Talk )ፕሮግራም ጋብዞ ነበር ። እንርሱም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት እቶ ጌታችው ረዳ ከሃሳይ፣ እውቁ የህግ መምህር እና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያቆብ ሃይለማሪያም፣ ታዋቂው የህግ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ እና ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ነበሩ። የእንግዶቹ ሰብጥርን ገና ከጅማሪው ሰሰማ ፕሮግራሙ አሰተማሪ እና ዘና የሚያደርግ ፕሮግራም አንደሚሆን ገምቼ ነበር ። በተለይ ደግሞ አንዳንድ ምእራባዊን የመንግስት ባለሰለጣናት ከሕዝብ ሰለሚሰነዘሩ ቅሬታዎች እና ትችቶች ከሚዲያ ፊት ቀርበው ምላሻቸው ምንም ይሁን ምን ሲሟገቱ ወይም ሰህተታቸውንም ሲያምኑ ሰሰማ “ይህ አይነቱ እድል እና መደረክን ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ ይሆን በነጻ የምናየው?” የሚል ጥያቄ ውሰጤን ሁሌም ስለ ሚኮረኩረኝ እና በእነርሱ የሰለጠነ የሚዲያ ባሕል ሰለ ምቀናም ጭምር ነበር።
ከ ንትርክ ፕሮግራሙ አዘጋጅ እና ጋዜጠኛዋ ከተወረወሩት በርካታ ጥያቄዋች መካከል “ከ አንድ አመት ተኩል እሰራት በሁዋላ ሰሞኑን በነጻ ሰለተለቀቁት(አንዱ በ20 ሺህ ብር ዋስ ነው የወጣው) የዞን 9 ጦማሪያኖች እና ጋዜጠኞች ከእስራት መፈታት ምን ትላላችሁ?፣,ምንስ ተሰማችሁ? ፣እነዚህ ለተለያዩ ችግሮች የተዳረጉት ወጣት ጦማሪዎች በፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ከተባሉ የሞራል ካሳ ሊከፈላቸው አይገባም ወይ?፣ገዢው መንግስትስ ወደፊት ከነጻው ፕሬስ ጋር አብሮ መሰራት ይችላል? …ወዘተ።” የሚሉ ይገኙበታል ። ከ ሚ/ር ጌታቸው በቀር ሶስቱም እንግዶች “የዞን 9 ጸሃፊዎቹ በእስር ቆይታቸው የተለያዩ ስቃዮች እንደ ደረሱባቸ ው፣ከጅማሪው ሊታሰሩ አንደማይገባ በፍትሕ እጦት መሰቃየት እና መጉላላት እንዳልነበረባቸው፣የሞራል ካሳ ጥያቄ የሚባለው ጉዳይ ደግሞ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደማያዋጣ እና ፌዝ መሆኑን ፣ ኢሕአዲግ በተፈጥሮው ዲሞክራሲያዊ መንግስት መሆን እንደማይችል ፣ጦማሪዎቹ የፖለቲካዊ ውሳኔ ሰለባዎች መሆናቸውን ፣ ወጣቶቹ በመለቀቃቸው ገዢው መንግስትን ማመሰገን አንደማይጠበቅባቸው “እና መሰል መልሶችን እንግዶቹ በተናጥል እና በዝርዝር አስረድተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ አቋም የነበረው ደግሞ በከፊል “አቃቢ ህግ እና ፖሊስ በቂ ማስረጃ ባለማቅርባቸው/ የቤት ስራቸውን ባለመሰራታቸው ፍ/ቤቱ ታሳሪዎቹን በነጻ አሰናብቷቸዋል፣ዶ/ር ያቆብ እና አቶ ተማም ወጣቶቹ በመፈታታቸው የተበሳጩ ይመሰላሉ፣ጉዳዮን ለፖለቲካ ሟሟቂያ ካለተጠቀምንበት በቀር ፣አንዳንዴ ፍ/ቤት ጥፋተኛ ያላቸው ሰዎች ከ20 አመት እሰራት በሁዋላ ነጻነታቸው የሚረጋገጥበት ሁኔታ ስለ ሚከሰት ታሳሪዎቹን እንኳን ደሰ ያላችሁ ነው ማለት ያለብን ።” በማለት በጦማሪያኖቹ እና በጋዜጠኞቹ ያላግባብ ከ አንድ አመት በላይ መታሰር በደረሰባቸው የአካላዊ እና የስነልቦናዊ ጉዳት ከ መቆጨት ለፍትህ ስርአቱ(ለዳኞቹ) ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ሞክረዋል። በነገርራችን ላይ እነዚህ ወጣቶች ከወራት በፊት “በሽብር ስራዎች ሰለመዘፈቃቸ በቂ መረጃ አለን”ተበሎ በጠ/ሚ/ሩ ሳይቀር ለአለም መገናኛ በዙሃናት ሳይቀር የታወጀባቸው ልጆች መሆናቸውን ማሰታወስ ግድ ይላል።
እየተሟሟቀ እና አጓጊ እየሆነ የሄደው ንትርኩ በተለይ ጠበቃ ተማም ከዚህ ቀደም ደንበኞቻቸው ማቆሚያ በሌለው የክስ ምክንያቶች እንዴት እንደተጉላሉባቸው በመግለጽ ላይ እያሉ ተራቸው እስኪ ደረስ ዝም ብለው ለመሰማት ፍቃደኛ ያለሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከ አስምት ጊዜያት በላይ “ተማም…!ተማም…! ተማም….!”በማለት ተናጋሪው አቶ ተማምን ለማቋረጥ እና የረሳቸውን አቋም ለመግለጽ ሲሞከሩ ተሰተውለዋል።ይህ አይነቱ የመደርክ አና ይማይክ ሺሚያ ደግሞ ብዙውን ጊዜ በእኛ አገር ባለሰልጣናት እና እንግዶች ዘንድ የተለመደ አይደለም ። በንትርርኮች ወይም ቃለ መልልሶች ላይ ያለመደማመጥ ችግር እንደ አረብ አገራት ግን በሰፋት የዘወተራል ። ክቡር ሚ/ሩ ከሰነዘሯቸው ግለሰባዊ ውንጀላዎች ለምሳሌ ያህል ባነሳ “ ለአንሰተኛ ጥብቅናቸው ካለሆነ በቀር አቶ ተማም ጥብቅና ለቆሙላቸው ከፍተኛ ፕሮፋይል ያላቸው ደንበኞቻቸው ጉዳይን አላሸነፉም ፣ዶ/ር ያቆብ ከዚህ በፊት መንግስትን በሃይል ለመጣል ሞክረው ያለተሳካለቸው ግለሰብ ናቸው ።”የሚሉ ይገኙበታል።

በንትርኩ ላይ “ከጥያቄው ጋር የማይዛመዱ ጉዳዮች ለማቅረብ እየተሞከረ ነው” የሚል ወቀሳ ያሰሙት አቶ ጌታቸው “ወደፊት ከተማም ጋር እንገናኝ ይሆናል ፣አሁን ሌላ ፕሮግራም አለኝ።” በማለት አገሪቱ በህይወት እስትንፋስ መሰጫ መሳሪያ (ላይፍ ሰፖርት ማሺን ) ወስጥ እንዳለች እና ቁልፉም በእርሳቸው እጅ ብቻ እንዳለ እስኪመሰል ድረስ ፣ምንም እንኳን በፕሮግራሙ እዘጋጅዋ “አቶ ጌታቸ ተሰናብተውን ሄደዋል “ብንባለም በእኔ እምነት ግን ሞቅ ብሎ የነበረው ንትርኩን “በበቃኝ”በማቋረጥ ፣ከማይክሮፎኑ ባሻገር ጆሯቸውን እና ልቦናቸውን ሰጥተው ሁሉንም እንግዶች እና ሃሳባቸውን አክብረው ፕሮግራሙን በጥሞና ይከታተሉ የነበሩ(እኔንም ጨምሮ) በርካታ አደማጮችን እና የነጻፕሬስ ወዳጆችን ጨረቃ ላይ ጥለውን እነደ ነጎዱ ሆኖ ነው የተሰማኝ።
እኔ የምለው “የህዝቡን ሙሉ ልብን በማግኘት ፣ ተቋዋሚዎችን በዝረራ በመጣል ምርጫውን 100%ያሸነፈ ፣ኢኮነሚውን በ ሁለት ዲጅት ያሳደገ፣ ተራራዎችን እሰከ ማንቀጥቀጥ ድረስ የቻለ ፓርቲ ሹም ” የሆኑት እኚህ አቶ ጌታቸው ረዳ የተሰጣቸው ትልቅ እድልን/መድረክን በመጠቀም ከ ፕሬስ እና ከጸረ አሸባሪው ሕጉ አኳያ ሊሟገቷቸው የቀረቡት ሶሰቱ እንግዶችን በመሞገት ለተሾሙበት የ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊነት ትልቅ ቦታ በብቃት መወጣት ሲገባቸው፣ድርጅታቸውን ሆነ መንግስታቸውን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ለማሸጋገር መጣጣሩን ትተው ንትርኩን በነገር ጀምረው ዶ/ር ያቆብንም “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ”በማለት እርሳቸውም (አቶ ጌታቸው) በቅጡ ሳይሰናበቱን መነጎዳቸው ሚኒስትሩ በመጀመሪያ አስተያየታቸው ላይ “ፖሊስ እና አቃቢ ሕግ በቂ ማስረጃ ባለማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዋችን በነጻ አሰናብቷል።” እንዳሉት ሁሉ በእለቱ የንትርክ ፕሮግራም ላይ ኢሕአዲግ ማሰረጃ ማቀረብ የተሳናቸው /ደካማ ፖሊሶች እና አቃቢ ህጎች የተነሰራፉበት ድርጅት ብቻ ሳይሆን በክፉ ቀን በሃሳብ አተካሮ ሸንጣቸውን ገትረው መሟገት የተሳናቸው ሚኒስተሮች የተበራከቱበት መንግስት መሆኑን ያሳያል ። ለማንኛውም አንዳንዴ ለመሪዎቻችን ቅን ልቦና ፣ብሩህ አይምሮ እና አንደበተ ርእቱነተን ብንመኝላቸው አይከፋም።

Filed in: Amharic