>

ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሶማሊያ ያዘመተችው በአሜሪካ “ጫና “መሆኑ ተጋለጠ [ታምሩ ገዳ]

Tamru Geda articleኢትዮጵያ እኤአ 2006 ለመጀመሪያ ጊዜ ጦሯን ወደ ጎረቤት ሶማሊያ በማሰገባት በወቅቱ ሞቋዶሾን ያስተዳድሩ የነበሩት የ እስላማዊ ፍርድ ቤ/ትን እንደተዋጋ የተደረገው በአሜሪካ “ጫና እና ማግባባት” እንደነበር በአሜሪካ አገር ከላስ ቪጋስ ከተማ የሚሰራጨው የሕብር ራዲዮ ዘገበ።

በዲፕሎማቲክ እና ሚስጥራዊ ሰንዶች ዙሪያ የሚያውጠነጥነው (ዊክ ሊክ ) ድሕረ ገጽ መረጃውን በዚህ ሳምንት ውስጥ ይፋ ማደረጉን የጠቀስው የእሁድ ጥቅምት 18 2015 አኤአ ምሽት የህብር ራዲዮ ዜና ዘገባ “ምንም እንኳን የእስላማዊ ፍርድ ቤ/ቱ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የነበርው እና ጸረ አትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም በኢትዮጵያ ገዢዎች በኩል እስላማዊ ፍርድ ቤቱን ለመዋጋት ችልተኝነት ነበር። “ ይላል የ ዊክሊክ መረጃ።ይሁን እና የእስላማዊው ፍ/ቤ/ት አደገኛነት ያሰጋት አሜሪካ በተለይ ደግሞ የቀድሞዋ በውጪ ጉ/ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ሁለተኛ ሰው የነበሩት ጂኔዳይ ፍሬዘር” ጫና እና ጉትጎታ” የተነሳ የቀደሞው ጠ/ሚ/ር መለሰ ዜናዊ “ጦራቸውን ወደ ሶማሊያ ከመላክ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም” ይላል ይሄው ሚስጥራዊው ዘገባ።
ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ከቡድኑ ጋር መዋጋት “አስፈላጊ አይደልም “ የሚል አቋም ነበራት ያለው መረጃው ጦርነቱ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በቅድሚያ አቅለለው እንደጠበቁት እና እንደገመቱት አልንበረም፣ እስላማዊው ፍርድ ቤ/ቱ ወደ የደፈጣ ተዋጊነት በመሸጋገሩ ፣ ቡድኑ በሚቀብራቸው ፈንጂዎች ፣ ኢትዮጵያን ሁሌም እንደ ታሪካዊ ጠላት የሚቆጥሯት የሰማሊያ የጦር ኣበጋዞቿ እስላማዊ ፍርድ ቤቱን በመቀላቀላቸው የተነሳ በኢትዮጵያ በኩል በርካታ ወታደሮች መሰዋት ለመሆን ተገደዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ጦርን ከ ኣሳቱ ወስጥ የከተተችው አሜሪካ በጊዜው የራሱዋን ጦርን በ ኣፍጋኒስታን እና በኢራቅ መሬት በማሰማራቷ ሶስተኛ ክንፍ ጦርነት በ አፍሪካ ቀንድ (ሶማሊያ ውስጥ) መክፈት ስላልፈለገች ኢትዮጵያን ለደንበር ተሻጋሪ ጦርነት(ፕሮክሲ ጦርነት ) ዳርጋታለች። የሶማሊይው ጦርነት ውሰብሰብነት ተሰፋ ያስቀረጣት እና ያሰከፋት ኢትዮጵያ ጦሯን አኤአ በ2009 ከሶማሊኣ ነቅሎ እንዲ ወጣ አድርጋለች። ይላል ሚስጥራዊው ሰንድ(ዊክ ሊንክን ) ዋቢ ያደረገው የሕብር ራዲዮ ዘገባ ።

ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ አጋጣሚዎች እና መደርኮች ላይ “ጦርነቱ በአሜሪካ ጉትጎታ አና የአሜሪካን ፍላጎትን ለሟሟት ሲባል ነው የተካሄደው ”ተበለው ሲጠየቁ “በጭራሽ በራሳችን ወጪ እና በራሳችን እቅድ እና ፕላን ነው ሶማሊያ የገባነው።” በማለት ሲያሰተባብሉ እንደነበር አይረሳም። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት አክራሪው አልሽባብን ለመፋለም በሚል ምክንያት በ ሺዎች የሚቆጠር ሰራዊቷን
ሶማሊያ ውስጥ አሰማርታ ትገኛለች።

Filed in: Amharic