>

አነ ኣብርሃም ደስታን ጨምሮ ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ነፃ እንዲለቀቁ ወሰነ

ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ነፃ እንዲለቀቁ ወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Negere Ethiopia-zelalem Werqagegnewhu, Abrha Desta, Yeshiwas Assefa, Daneil Shibeshi,HAbtamu Ayalewዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡

በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡

Filed in: Amharic