>

የኢትዮጵያ የ “ዲፕሎማቶች ቁንጮ” መሳለቅያ ቅጥፈት [ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም]

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነ ሰው ስለዲፕሎማሲ ጥበብ እና ሳይንስ ምንድን ሊያውቅ ይችላል? ወይም ደግሞ እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለው ልዩነት ምን ያውቃል? ወይም ደግሞ የለየለት ቅጥፈትን አምኖ በመቀበል እና ቅጥፈትን በማውገዝ መካከል ያለውን ልዩነት ምን ያውቃል? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ያለምክንያት አላነሰዋቸሁም፡፡

Ayte Tedros Adhanomቴዎድሮስ አድኃኖም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር new፡፡ ይፋ በሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሕይወት ታሪክ አድኃኖም “ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላው የወባ ትንኝ ተመራማሪ” መሆኑን ተገልጿል፡፡ አድኃኖም ከለንደን የጤና አጠባበቅ እና ትሮፒካል ህክምና ትምህርት ቤት/London School of Hygiene & Tropical Medicine የሰው ልጅ ሰውነት በሽታዎችን በመቋቋም ችሎታዎች/immunology ላይ ጥናት በሚያደርገው የተላላፊ በሽታዎች የህክምና ሙያ ላይ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ለንደን ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ2000 በህብረተሰብ ጤና/community health የዶክትሪት ዲግሪ ተቀብለዋል እየተባለ ይነገርለታል ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አድርገው ሾመው፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ አድኃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነ ተሾመ፡፡ የወባ ትንኝ ተመራማሪ በአንድ ጊዜ ባንድ ሌሊት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በማግስቱ ጀንበር ሳይጠልቅ የሀገሪቱ ታላቅ የተባለውን የዲፕሎማትነት የስልጣን ቦታ መቆጣጠር የሚቻልበት የፖለቲካ ሂደት ሌላ የትም ሀገር ሳይሆን አች በወሮበላ ተቀሰፋ የተያዘቸው የውሸቷ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው!

ውሸት በተንሰራፋባት ሀገር የቴዎድሮስ አድኃኖም በ14 ዓመት ልጃገረድ መታለል፣

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት አውስትራሊያዊት የሆነች እና ከየት ቦታ እንደመጣች የማትታወቅ የ14 ዓመት ልጃገረድ ከአድኃኖም ግን በመቀመጥ ቃለ መጠይቅ በማካሄድ እና በአውስትራሊያ አሸናፊ ሆና በሽልማት ያገኘችውን 20 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ አገልግሎት እንዲውል የለገሰች መሆኑን በገለጸችበት በዚያ የመድረክ ላይ ተውኔት አድኃኖም ዋና የገጸ ባህሪነት ድርሻን ይዘው ተውኔቱን ዋና ተጭዋች ነበር፡፡ አንድያው ለነገሩ ማንም የመታዘብ ቺሎታ ያለው ሰው እንደዚህ ያለ በህጻን ልጅ የሚደረግ የሃያ ሚልዮን ዶላር ትረካ አውነት ብሎ ያምናል፡፡ በእርግጥ ባለፈው ህዳር worldnewsdailyreport.com የተሰኘ የቀልደኛ ድረ ገጽ አስርቱ ትዕዛዛት የተጻፉበት ጽላት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ኃላፊዎች የተሰረቀ መሆኑን በመግለጽ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች አስደንግጦና አሸብሮ ነበር።

በስደት ላይ የሚገኘው እና ሙሰኝነትን፣ አጭበርባሪነትን፣ የሀሰት ዲግሪዎችን እና በህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ የሚጠቀሙትን በማጋለጥ ታዋቂ የሆነው ወጣቱ የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው እ.ኤ.አ መጋቢት 2/2015 አድኃኖም በአንዲት የትምህርት ቤት ልጅ የተታለሉ መሆናቸውን ምርመራ በማድረግ አንድ ዘገባ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ [ማስታወሻ፡ በአድኃኖም የቅሌት ተውኔት ውስጥ የተሳተፈችውን የትምህርት ቤት ልጅ ሆን ብዬ ስሟን ይፋ ማድረግ አልፈልግም ምክንያቱም የልጅቷ ስም በመገናኛ ብዙሀን እንዲወጣ፣ እንድትወገዝ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲፈጸምባት አልፈልግም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የ14 ዓመት የሆነች ልጅ ሙሉ በሙሉ በእራሷ ስብዕና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ዝርዝር የማጭበርበር ድርጊት በማውጣት ታታልላለች የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከዚህ በኋላ ይህችን ልጅ ወጣቷ ወይዘሪት ወይም ደግሞ ልጅቷ እያልኩ እጠራታለሁ ምክንያቱም እርሷ እራሷ በአድኃኖም እና በግብረ አበሮቹ አማካይነት ለርካሽ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እንድትዋሽ የተደረገች የማጨበርበሩ ሰለባ ናትና ፡፡]

ከአድኃኖም ጋር ሲካሄድ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ወጣቷ እንዲህ ብላ ነበር፣ “በውድድር አሸናፊ ሆኘ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በሽልማት አግኝቸ ነበር፡፡ እናም አሁን እዚህ የተገኘሁት ከኢትዮጵያ እና ከአውስትራሊያ መንግስታት ጋር በመሆን በሀገሬ የግንባታ ፕሮጀክት ለመጀመር ነው፡፡“ ቀሪውን የልጅቷን ትረካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆነው ሰው እንዲህ በማለት ተናግሮላታል፡

“መታወቅ ያለበት አንድ ዋና ነገር ልጅቷ በአውስትራሊያ በሚገኙ ክለቦች ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የምትገኝ ልጅ ናት፡፡ እርሷ ከምትመራቸው ክለቦች ውስጥ አንደኛው የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጥበቃ ክለብ ነው፡፡ በዚያ ክለብ ውስጥ እርሷ እና ሌሎች የክለቡ አባላት ሌሎችን ሰዎች እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ሀሳብ ይለዋወጣሉ፣ ውይይትም ያካሂዳሉ፡፡ እርሷ ያነሳቸው ዋነኛው ሀሳብ ሌሎቹ ትምህርት የማግኘት ዕድል እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከማሰቡ ላይ ነው፡፡ በአውስትራሊያ ያሉ ህዝቦች ይህንን በሚሰሙበት ጊዜ ይህንን ሀሳቧን የደገፉ ሰዎች ገንዘብ አሰባስበው 20 ሚሊዮን ዶላር ለእርሷ ሰጧት፡፡ ይህ ድርጊት የተፈጸመው እ.ኤ.አ በ2014 ነው፡፡ ለጉብኝት ወደ ትውልድ ሀገሯ በመጣች ጊዜ ከእራሷ አንደበት እንደሰማችሁት በሽልማት ባገኘችው በ20 ሚሊዮን ዶላር በሀረር በጋራሙለታ አካባቢ ትምህርት ቤት ለመገንባት እንደምትፈልግ ሀሳቧን ገልጻለች፡፡ እንግዲህ ኃላፊነቱ ካላቸው ባለስልጣኖች ጋር በመተባበር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስራውን ትጀምራለች፡፡”

አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አንዲትን የ20 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ የሆነች ልጅ እንዴት አድርጎ ሊያውቅ እና ሊያገኛት ቻለ? ለዚህ ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዲህ የሚል ገለጻ ሰጥቷል፡

ወጣቷ ልጅ በመጣች ጊዜ ስለእርሷ ማንነት የሚገልጹትን ሰነዶች ተመለከትን፡፡ ልጅቷ ወደ እኛ ቢሮ የመጣችው በቤተሰቦቿ አማካይነት ነው፡፡ የተከበሩት የእኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለልጅቷ ጉዳይ አወቁ እናም ይኸ ጉዳይ ለሌሎች ወጣቶችም መልካም አርዓያ ስለሆነ ልጅቷን ማበረታታት እና ስለዚህ ጉዳይ መናገር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሚኒስትሩ ጠንካራ በሆነ መልኩ ልጅቷን አበረታትተዋታል፡፡ ስለሆነም ልጅቷ ወደ እርሳቸው እንድትመጣ ጥሪ በማድረግ አነጋግረዋታል፡፡ መንግስት ማድረግ ያለበትን አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ለማድረግ እና ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ልጅቷ የምትፈልገውን እርዳታ ሁሉ እንደሚያደርግላት አረጋግጠውላታል፡፡

ይኸ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ዋናው ችግር ገንዘቡ ፍጹም የሌለ እና ያልተገኘ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ልጅቷ እንደዚህ ያለ ሽልማት በፍጹም አልተቀበለችም፡፡ ይህ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ሸፍጥ ነው፡፡ አንድ የተከበረ ሚኒስትር የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ልጅ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ከአውስትራሊያ 20 ሚሊዮን የእርዳታ ዶላር በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ ትጓዛለች ብሎ ማመን አንደ ማሞ ቂሎ አይነት ተረት ይመስላል ወይም ህዝብን አንዴ ሞኝ ከማየት የመጣ ይመስላል።

ይህንን አባባል በሌላ መልኩ ለማስቀመጥ የ20 ሚሊዮን ሽልማት ተብየው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ 11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዘገብኩ (በነገራችን ላይ ይህ አሀዝ የለየለት ሀሰት፣ ተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ መሆኑን ከጥርጣሬ በላይ በማስረጃ አስደግፌ ያረጋገጥኩት ጉዳይ መሆኑን ልብ ይሏል) ከሚለው ማጭበርበሪያ ጋር አንድ አይነት እና ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለቱም ማጨበርበሮች በነባራዊ እውነታ ላይ የሌሉትን እንዳሉ አድርገው የሚያቀርቡ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ የሆኑ የሸፍጥ አካሄዶች ናቸውና፡፡

የአበበ ገላው የምርመራ ዘገባ በአሰራር ስልት የአድኃኖምን የ20 ሚሊዮን አጠያያቂ ሽልማት ውድቅ አድርጎታል፡፡ አበበ የ20 ሚሊዮን ሽልማት በትምህርት ቤታችሁ ለምትማር ልጅ ሰጥታችኋል ወይ በማለት ልጅቷ ለምትማርበት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የስልክ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፣ “ይኸ እንቆቅልሽ የሆነ ነገር ነው፣ ትምህርት ቤታችን እንደዚህ ያለ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሰጥቶም፣ ውድድር አድርጎም አያውቅ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ልጅቷ ለ20 ሚሊዮን ዶላር የሚያበቃ እውቀትም የላትም፡፡“ አበበ በአውስትራሊያ በሜልቦርን የገንዘብ ማሰባሰቡን የማስተባበር ስራ አከናውኗል ከተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ ጋርም ግንኙነት አድርጓል፡፡ ኮሌጁ እንዲህ በማለት የማስተባበያ ቃሉን ሰጥቷል፣ “እንደዚህ ባለ አስገራሚ ጉዳይ ላይ መሳተፍ ይቅርና ኮሌጁ እራሱን የሚያንቀሳቅሰው 12 ሚሊዮን ዶላር በሆነው አመታዊ በጀቱ ነው፡፡“ በአውስትራሊያ የሮታሪ ዓለም አቀፍ ማናጀር የሆኑት ይህ ድርጀት ሽልማት ለመስጠቱ በአበበ ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሁሉም ቅርንጫፎች በበጀት ዓመቱ ውስጥ 5.6 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ብቻ መሰብሰባቸውን እና በምንም ዓይነት መልኩ እንደዚህ ላለች የ14 ዓመት የትምህርት ቤት ልጅ 20 ሚሊዮን ዶላር መሸለምም ሆነ መስጠት አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ነገር መሆኑን ግልጽ አድርገው ተናግረዋል፡፡

የአውስትራሊያ መንግስት ስለ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ለኢትዮጵያ መንግስት ለትምህርት ተብሎ የተሰጠ ገንዘብ እንደሌለ ግልጽ አድርጓል፡፡ እንግዲህ ነገሮች ሁሉ እንደዚህ የሚሆኑ ከሆነ የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት ከየት መጣ?

እንደ አበበ ገለጻ ከሆነ ወጣቷ ልጅ ከአድኃኖም ጋር በካሜራ ተቀርጻ ለቴሌቪዥን የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመቅረቧ ከሰዓታት በፊት በአድኃኖም እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡድን እና በአማካሪዎች አማካይነት ውሸት እንድትናገር በመቅረጽ በቴሌቪዥን እንዲቀርብ እንዲደረግ የማግባባት ስራ ተደርጎላታል የሚል ግምት አለ፡፡ የተባለው ገንዘብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጭቆና አገዛዝ ተቀናቃኝ የሆነ ተቃዋሚ በሚንቀሳቀስበት በምስራቅ ኢትዮጵያ በጋራ ሙለታ አካባቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ ይውላል መባሉ ለህዝብ ግንኙነት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል እንደሆነ ዘግቧል፡፡ እንደ አበበ አስተያየት ከሆነ ሚኒስትሩ [አድኃኖም]፣ በተወልደ ሙሉጌታ የሚመራው የህዝብ ግንኙነት ቡድናቸው፣ በአውስትራሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ባለስልጣኖች የኦሮሚያን ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ መሀመድን ጨምሮ በዚህ አደገኛ የሆነ ቀውስን ሊያመጣ በሚችል የሸፍጥ ዕኩይ ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

አበበ አንድ ጊዜ ታሪኩን ይፋ ማድረግ ከጀመረ በኋላ አድኃኖም ይህንን ድርጊት ለማስተባበል እ.ኤ.አ መጋቢት 7/2015 የማህበራዊ ድረ ገጻቸውን በመጠቀም በለቀቁት ጽሁፍ እርሳቸው በይፋ የዋሹትን ውሸት ልጅቷ አሳስታኝ ነው በማለት ውንጀላውን ሙሉ በሙሉ በልጅቷ ላይ ደፍድፈውታል፡፡ የአድኃኖም የማህበራዊ ድረ ገጽ ገለጻ በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ ስለሆነ በጣም የሚያሸማቅቅ እና አሳፋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ያቀረቡት አመክንዮ ውጤቱ እርባና የለውም በሚል ህግ ወይም መርህ ላይ በተመሰረተ የመጽሐፍ ምሳሌ እንዲህ በማለት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ አድኃኖም በአጠቃላይ ልጆች ትናንሽ ልጆችን ጨምሮ ጨዋዎች ናቸው የሚል አመክንዮ ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፡፡ ልጆች ይዋሻሉ፡፡ ልጆች የሚዋሹት ግን ከመጥፎ ድርጊት አስተሳሰብ በመነሳት ለክፋት ሳይሆን ከተራ ስህተት ነው፡፡ የልጆች የተሳሳቱ ውሸቶች ጨዋነት ያላቸው ውሸቶች ናቸው፡፡ ልጆችን አምናቸዋለሁ፣ ምክንያቱም የልጆች ውሸቶች ጨዋነትን የተላበሱ ውሸቶች ናቸው፡፡ እነርሱን ለማመን እመርጣለሁ፡፡ የልጆችን ጨዋነት የተሞላባቸውን ውሸቶች ማመን ስህተት ከሆነ ያንን ስህተት መፈጸምን እመርጣለሁ ብለዋል፡፡

አድኃኖም በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንዲህ የሚል የበከተ እና የበሰበሰ ሆኖም ግን በእርሳቸው አባባል ቅዱስነትን በተላበሰ መልኩ ለመጻፍ ሞክረዋል፡
“እንደምታውቁት ወጣቷ ልጅ ታዳጊ ልጅ ናት፡፡ ልጆች ምንም ዓይነት መጥፎ ነገርን የማይቀላቅሉ ጨዋዎች ናቸው በሚለው አባባል ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር ትስማማላችሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ልጆች ስህተቶችን የሚሰሩ ከሆነ እነዚህ ስህተቶቻቸው ከመጥፎ ነገሮች የሚመነጩ ሳይሆን ከተራ ስህተቶች የሚመሰረቱ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች የሚነግሩኝን ነገር ሁሉ ለማመን እመርጣለሁ፡፡ ልጆችን ማመን ጥፋት ከሆነ ያንን ስህተት መስራቱን እመርጣለሁ፡፡ ስለሆነም አሁንም ቢሆን ይህችን ወጣት ልጅ ማመን እመርጣለሁ፡፡ ተገቢነት ያልሆኑ ነገሮችን በመጻፍ የልጅቷን ስሜት መጉዳት የለብንም፡፡ የእርሷ የፕሮጀክት ዕቅድ የተቀደሰ ነው፡፡ የእርሷ ፕሮጀክት ስኬታማ እንደሚሆን ጠንካራ የሆነ እምነት አለኝ፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ ይህችን ወጣት ልጅ ማበረታታት እና መደገፍ መቻል ነው፡፡

በእርግጥ የ20 ሚሊዮን ዶላር የሚባል ምንም ዓይነት ፕሮጅክት የለም፡፡ ሁሉም ነገር እውነት ሳይሆን ሸፍጥ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያደርግ እንደቆየው የ11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት የቅጥፈት የህዝብ ግንኙነት የፕሮፓጋንዳ ስራ ሲካሄድ እንደቆየው ሁሉ ነው፡፡ አድኃኖም በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንኳ ይኸ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በተባለው በአንዲት የትምህርት ቤት ልጅ ፍጹም በሆነ መልኩ ተታልያለሁ፣ ተሞኝቻለሁ ወይም ደግሞ ተጭበርብሪያለሁ በማለት ለማመን የሞራል ድፍረቱ አልነበረዉም (በእርግጥ ይህንን መድረክ ላይ ተውኔት እራsu ያቀነባበሩት ካልሆነ በስተቀር)፡፡ ምናልባትም በዚህ ጉዳይ ላይ ልንደነቅ አንችልም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት አስርት ዓመታት ሀገሪቱ በየዓመቱ በአማካይ በ11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ስታስመዘግብ ቆይታለች ያለውን ተራ ወሸት፣ ቅጠፈት እና የቁጥር ጨዋታ ለመሆኑ እውቅና በመስጠት እንዲያምን እስከ አሁንም ድረስ ተስፋ ሳልቆርጥ በመጠበቅ ላይ እገኛለሁ፡፡

ወይ ጉድ! ወይ ጉድ!

ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አባባል ከህጻን ላይ ከረሜላ ነጥቆ እንደመውሰድ የቀለለ ተግባር ነው፡፡ አንድን የዲፕሎማሲ ቁንጮ የሆነን ታላቅ ባለስልጣን እና በቀጣይነትም የጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ባለስልጣን አንዲት ህጻን የ20 ሚሊዮን ዶላር የሚከፋፈል ከረሜላ አለ በማለት የማታለል ወንጀል ተፈጽምበታለች ተብሎ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ በፍጹም ሊሆን የሚችል ጉዳይ አይደለም! በጣም አስፈሪ የሆነው እውነታ ግን አድኃኖም በ14 ዓመት ልጅ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ታሪክ ትረካ በማቅረብ የሚታለል ከሆነ አስቸጋሪው እና ትልቁ ነገር ይህ ባለስልጣን ቀንድ ያለው ነገረኛ፣ ካገጩ ላይ ጺሙን ያንጨበረረ መሰሪ፣ ቀጣፊ ምላስ ያለው፣ ተናግሮ ማሳመን የሚችል አንደበተ ርትኡ የሆነ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እምነተ ቢስ እና አጭበርባሪ የሆነ ሰው፣ ሁለት ምላስ ያለው፣ ሆን ብሎ ጓደኝነትን ክዶ የሚያጭበረብር፣ አንድን ነገር በማስመሰል የሚደብቅ፣ ጭልፊት የሆነ አታላይ የዲፕሎማሲ ሰው በሚያጋጥመው ጊዜ ምን ሊያደርግ ነው? እንዲያው ሁሉም ነገር በአንክሮ ሲታይ አሳዛኝ እና የሀገሪቱን መጥፎ ዕጣ ፈንታ በጉልህ የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ወኔን አጠንክሮ ቀበቶን ጠበቅ በማድረግ ትግሉን ማጧጧፍ የእያንዳንዱ ዜጋ በተለይም ተማርን ለሚለው ወገን ታላቅ ኃላፊነት ነው፡፡ የትግሉን ቀጣይነት እንዲህ በሚሉ የተቋጠሩ የግጥም ስንኞች ስንቅነት እድንይዘው ጀባ ልበላችሁ፡፡

በክቦቹ ዙሪያ እሩጡ ዘምሩ፣
ጽጌረዳ ያዙ ማንንም ሳትፈሩ፡፡
በኪስ ሙሉ አበባ በመያዝ እሩጡ፣
ከጫፍ እስከ ጫፉ ሳትበጣበጡ፡፡

ያ መጣ ብላችሁ ሀሳብ ሳይገባችሁ፣
ያ ሄደ ብላችሁ ጭንቀት ሳይዛችሁ፣
ሁላችሁም ለድል ለስኬት ብላችሁ፣
ጉዞውን ፈጽሙት ወገን እባካችሁ፡፡

ሩጫው በርትቶ ድካሙ ሳይዘው፣
እስትንፋስ ሳያጥረው ነጭ ላብ ሳይወርደው፣
ጉልበቱ በመራድ ሳይዛነፍ ወኔው፣
ሸሚዙን አውልቆ ሳይዝ በትከሻው፣
ትግሉን አጧጡፉት ለመልካም ፍጻሜው፡፡

የአድሃኖም ጋር የሚሰሩ የዲፕሎማሲ ሰዎች አሱን ለማታለል አጃቸዉን አየፈተጉ ለሀጭቻቸዉን አያንጠባጠቡ ከልጅ ከረሜላ አንደመወስድ ያህል አየጠበቁ ነው።

የኢትዮጵያ ቁንጮ የዲፕሎማሲ ሰው የሆነዉን አድኃኖም እንደዚህ ያለ ምንም ዓይነት ማገናዘብ የማይል የዋህ፣ በቀላሉ የሚታለሉ ወይም ደግሞ ብልህነት ያነሳቸው እና ነገሮችን ሰፋ አድርጎ የመመልከት ችሎታ የሌለው በመሆን አንዲት ልጅ ከቢሯቸው ድረስ ሰተት ብላ በመሄድ የ20 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ልገሳ በመስጠት ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚል የተዛባ እና እውነትነት የሌለው ትረካ በማቅረብ ልታታልለው ትችላለች? አድኃኖም እንዴት እንደዚህ በቀላሉ ሊታለል ቻለ? የሀገር የዲፕሎማሲ ሰው መሆን ማለት ስለሀገር ሲባል በመሰረታዊ ጭብጡ ውሸትን እውነት አድርጎ የማቅረብ ሙያዊ ክህሎት መሆኑን እንዴት ማወቅ ተሳነው? ዲፕሎማሲ ለስልታዊ እና ዘለቄታዊ ጥቅም ሲባል እውነቱን ያለመናገር ክህሎት መሆኑን አልተገነዘቡምን? በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ይህንን ጉዳይ ወደ ኋላ እመልሰዋለሁ፡፡ ውሸት በሚነገርባት በኢትዮጵያ ላይ ውሸት መዋሸት የኑሮ ስልት ነው፡፡

በእርግጥ አድኃኖም በእውነታው እና ባቀረቧቸው የክርክር አመክንዮዎች በእጥፍ ስህተት የሰራ ሰው ነው ፡ ህጻናት እንደ ማስመሰያ ጸጉር/ዊግ አይዋሹም፡፡ (ይህ ማለት ወጣቷ ልጅ በምንም ዓይነት መንገድ በዚህ የቅሌት ዕኩይ ተግባር ላይ ትዋሻለች ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህንን የመሰለውን የማታለል ድርጊት መፈጻም እንድትችል የተቀነባበረ እና እንድትፈጽመው ስልጠና የተሰጣት ለመሆኑ ፍንጭ ሊሰጡ የሚችሉ ነገሮች ተንጸባርቀዋል፡፡)

ውሸትን ከእውነት ለመለየት ለምንሰራ ሰዎች ቢያንስ ከህግ ምርመራ ሁኔታዎች አንጻር ልጆች እንደ እርካሾቹ የቻይና ሰዓቶች የሚዋሹ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እድሚያቸው ከሶስት ዓመታት በታች የሆኑ ህጻናት እውነትን ከውሸት ለመለየት አይችሉም፡፡ እስከ ሰባት ዓመታት ድረስ ጥቂት ልጆች በእውነታ እና በማገናዘብ ኃይል መካከል ያለውን ልዩነት የመገንዘብ ይችላል፡፡ ጥቂት የሆኑ ነጭ ውሸቶችን መዋሸት ይጀምራሉ፡፡ በ10 ዓመታቸው እውነትን መናገር እና ውሸትን መናገር ምን ማለት እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ እናም ውሸት በሚዋሹበት ጊዜ ፒኖክዮ እንደሚባለው እውነተኛውን ተናግሮ እንደ እውነተኛ ልጅ ለመሆን እንደሚሞክረው አሻንጉሊት የእንጨት ተክል ናቸው፡፡ በ10 ዓመታቸው በእርግጠኝነት ሲዋሹ እና እውነታውን ለጥጠው ሲናገሩ እንዲሁም ለስለስ ያሉ ውሸቶችን እና ግማሽ የሆኑ እውነቶችን የመፈብረክ ችሎታን ያዳብራሉ፡፡ እንደዚሁም እውነትን አሳምሮ እና አጣፍጦ ከመናገርም በላይ በዝርዝር የቀረቡ እውነታዎችን እና ረዣዥም ትረካዎችንም ማቅረብ ይችላሉ፡፡

በ10 ዓመታቸው ልጆች ሙሉ ለሙሉ በሚዋሹበት ጊዜ ብቻ አይደለም የሚያውቁት እናም የ20 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር በወጣቷ ልጅ ተፈጽሟል የሚለው ሁኔታ እ.ኤ.አ በ1979 የቀረበውን ተንቀሳቃሽ ህይወት አልባ አስቂኝ ፍጡር በዚህች ውሸት በሚነገርባት ምድር ላይ በመኖር ቶሎ ቶሎ የሚተነፍሰውን የውኃ ተርብ አስታወሰኝ፡፡ በዚያ የህይወት አልባ የምስል እንቅስቃሴ ላይ የሚተውነው ተርብ ሳንዲ የምትባለውን ትንሿን ልጃገረድ በኃይል አስገድዶ ወደ የውሸት ዓለም ወደሆነችው ምድር ላይ በመውሰድ ፒኖክዮ ከሚባለው ታዋቂ ተክል እና እንደ በሬ ወለደ ከሚለው ልጅ ዘንድ በመውሰድ እንድትገናኝ በማድረግ እንዲህ የሚል ቃለ ምልልስ ያደርጋሉ፡

ሳንዲ፡ ፑፍ፣ ተመልከት!
ፑፍ፡ እስከ አሀን ድረስ ማንም አይቷት የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ቀለም ያላት ላም ናት፡፡
ሳንዲ፡ እንደዚሁም ቀይ ቀለም ያለው ዝሆን
ፑፍ፡ ጥቂቶች ሁልጊዜ ያያሉ
ሳንዲ፡ ያ ማን ነው?
ፑፍ፡ ኪልሮይ፡፡ ሁልጊዜ እዚያ ነበር እናም የትም አልነበረም፡፡
ፑፍ፡ እኔ የውኃ ተርቡ የትምህርት ቤት የቤት ስራየን ምሳ አድርጌ መብላት እንደምችል ማሰብ አዲስ ነገር አይደለምን? በእርግጥም ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማያውቅ አዲስ ነገር ነው፡፡ ውሸት ነገር ነበር፡፡ ቅሌት ነገር ነው፣ ትክክለኛ እና ታማዕኒነት ያለው መልስ መስጠት ያለመቻል ነበር፡፡ ኦ፣ ይኸ ነገር ሳንዲ በምትባል በትንሿ ልጃገረድ የተነገረ ቀላል የሆነ ውሸት ነበር፡፡
ሳንዲ፡ ፑፍ፣ ተመልከት!
ሳንዲ፡ የለም፣ እነዚህ ምዕናባዊ ውሸቶች ናቸው፡፡ እናም ጎጅ ያልሆኑ ምናባዊ ግንዛቤዎች ናቸው፣ እሺ፡፡ እናም ይኸ ነገር አስቂኝም ጭምር ነው፡፡
ለቴ እኔም ግማሽ የምናብ ግንዛቤ ነኝ፡፡

ወጣቷ ልጃገረድ ከአውስትራሊያ ውሸት ወደሚኖርባት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከአድኃኖም እና ከሸፍጡ ግብረ አበሮች ጋር የማታለል ድርጊት ጋር እንድትገኛኝ የተደረገች ይመስለኛል፡፡ ምንም በተጨባጭ የሌለውን እና ማንም ያላየውን ሽልማት 20 ሚሊዮን ዶላር ምዕናባዊ የሆነ ውሸት እንድትዋሽ ተነግሯታል፡፡ በ20 ሚሊዮን ዶላር የትምህርት ቤት ግንባታ የአስራአራት ዓመት ልጅ ታረጋለች ብሎ ማመን ቀይ ዝሆን አለ ብሎ ማመን ያህል ነው።

ሆኖም ግን በውኃ ተርቡ እንደተበላው የቤት ስራ ሁሉ 20 ሚሊዮኑ የአሸናፊነት የሽልማት ዶላር አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፣ ታላቅ ቅሌትም ነው፣ ቀጥተኛ እና እውነተኛ ያልሆነ መልስን በመስጠት እውነትን ለመቅበር የሚደረግ ደባ ነው፡፡ አድኃኖም እና ግብረ አበሮቹ ሽልማቱ ሙሉ በሙሉ ፈጠራ የነበረ መሆኑን አሳምረው ያውቁታል፡፡ ሆኖም ግን ወጣቷ ልጅ ስለዚህ ጉዳይ እንድትናገር አድርገዋል፡፡ አያውቁትም ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? እንዴት? አንዲት ትንሽ የሆነች ልጅ ከመንገድ ገብታ 20 ሚሊዮን ዶላር ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል ገንዘብ አለኝ በማለት የሀገሪቱ ቁንጮ ለሆነ የዲፕሎማሲ ሰው ስትናገር አንድ ምክንያታዊ የሆነ በዓለም ላይ የሚኖር ሰው ማድረግ ያለበት ምንድን ነው? ይህችን ህጻን ልጅ በቴሌቪዥን መስኮት እንድትቀርብ በማድረግ ህዝቡ ከእርሷ ለጋስነት ትምህርት እንዲወስድ መለፍለፍ ነው? ይህንን ፍጹም የተሳሳተ እና ምዕናባዊ የሆነ የገንዘብ ሽልማት ጉዳይ በማስመልከት ለአውስትራሊያ ኤምባሲ፣ ለአንደኛ ደረጃው ትምህርት ቤት፣ ለሮታሪ ክለብ እና ለባደን ፓወል ኮሌጅ በመደወል ለማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቢሮ ማድረግ የለበትም ? በአንድ በስደት ላይ ያለ ጋዜጠኛ ይህንን የመሰለ ቅሌት ጥቂት የሆኑ የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ ካጣራ እና ውሸት መሆኑን ካረጋገጠ የአድኃኖም ቢሮስ በተመሳሳይ መልኩ እንደዚህ ማድረግ ያልቻለው ለምንድን ነው? አንዲት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነች ህጻን ልጅ በመንገድ ሰተት ብላ በመሄድ አድኃኖምን ማታለል የምትችል መሆኑ ሲታይ ዝም ብሎ እንደ ተራ ነገር የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው እንዳቀረበው ዘገባ ይህ ጉዳይ ታላቅ የሆነ የውስጥ ተግባር ነው፡፡

አድኃኖም ምክንያታዊ ባልሆነ እና በተሳሳተ መልኩ በማህበራዊ ድረ ገጽ ያካሄደው ጫካውን የመደብደብ ከንቱ ጥረት በቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንዲሉ ከመሆን ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ ፈላስፋነትን የተላበሰ በሚመስል ሆኖም ግን በቅጥፈት በተላበሰ አንደበት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልጆች በስህተት ይዋሻሉ፡፡ የልጆች ውሸቶች ጎጅዎች አይደሉም፡፡ ወጣቷ ልጅ ስህተት አትሰራም ወይም ደግሞ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ልትዋሽ ካልሆነ በስተቀር ጎጅ ውሸት አትዋሽም፡፡ ቁንጮ በሆኑት የዲፕሎማት ሰው እና በግብረ አበሮቿ በተነገራት መሰረት ታላቅ የውሸት ትረካ ፈጽማለች፡፡ ውሸትን እንደ ጨዋነት አድርጎ አስመስሎ የሚያቀርበው እና ታዕማኒነትን ባጓደለ መልኩ ቅዱስ ሀሳብ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርበው የአድኃኖም እምነተቢስ የማህበራዊ ድረ ገጽ መልዕክት ጥረት የተንሻፈፈ እና የግንዛቤ አድማሳችንን የሚፈታተን ከንቱ ስሌት ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ዋልተር ስኮት “በመጀመሪያ ደረጃ መዋሸት ስንጀምር ምን ዓይነት ድር ነው እያደራን ያለነው” በማለት ተናግረው ነበር፡፡

አድኃኖም 20 ሚሊዮን ዶላር ስለተባለው የሀሰት የተጭበረበረ ገንዘብ ሁኔታ በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት ነገር ሊነግረን አልደፈረም፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር ከሌለ ሆን ብለው እራሱን ደንቆሮ አድርጎ ነውን? ሰውየው በገዥው አካል በብቸኝነት በተያዘው በህዝብ መገናኛ ብዙሀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ስላስተላለፉት ስለ20 ሚሊዮኑ ዶላር ቅጥፈት ኃላፊነቱን አልወሰደም፡፡ አድኃኖም እንደዚህ ባለ መልኩ ስለተፈጸመው ታላቅ ቅሌት ምርመራ እንዲደረግበትም እንኳ ትዕዛዝ አላስተላለፈም ፡፡ መግለጫዎችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ሁኔታውን ለማረም እና በብዙሀን መገናኛ እንዲተላለፍ ምንም ዓይነት ጥረት አላደረገም፡፡

የበለጠ አስደንጋጩ እውነታ ደግሞ ህጻኗን ልጅ በሰይጣን እና በጥልቅ ሰማያዊ ባህር መካከል ጥለው ምንም ዓይነት ኃላፊነት ያለመውሰዱ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ህጻን ልጅ በጓደኞቿ እና አታላዩዋ ልጅ፣ አሳዛኟ ወንጀለኛ እና አጭበርባሪዋ ልጅ እየተባለች በመጥፎነት ስትታወስ የምትኖር ስለመሆኗ አድኃኖም ጉዳዩ አይደለም፡፡ አድኃኖም ልጅቷን ከፈጣን አውቶብስ ስር በመጣል በጠቅላላ በ20 ሚሊዮን ዶላር ቅሌት ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ቸግር ሁሉ ሙሉ ኃላፊነቱን እንድትወስድ አድርገዋል፡፡ ልጅቷን ከመረጃ የትችት ማዕበል ውስጥ ጥለዋት ሄደዋል፡፡ እንደዚህ ያለ የጫካ ቅሌትን በማደራጃት እና በመምራት ለሰሩት ግፍ ይህችን ወጣት ልጅም ሆነ የኢትዮያን ህዝብ ይቅርታ አልጠየቀ ም፡፡ ወጣቷ ልጅ ጨዋነትን የተላበሰ እና ምንም ዓይነት ጉዳትን ሊያስከትል የማይችል ውሸት እንደዋሸች አድርጎ በመፈረጅ ይህንን ታላቅ ቅሌት እንደ ቀላል ነገር ለበስ ለበስ አድርጎ ለማለፍ ጥረት ተደርጓል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ሰዎችን ሆን ብሎ ለመጉዳት ዕኩይ ምግባር ለሚያራምድ ሰው፣ ቁንጮ ዲፕሎማት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ከመቅጽበት ለይስሙላ ተቀምጦ ያለውን ጠቅላይ ሚኒስትር በማስወገድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቢሮን ለመውሰድ ዙፋኑን እያሟሟቀ ላለ ባለስልጣን ምን ይባላል?

የሞራል ተቀባይነት በሌለው በአድኃኖም ባህሪ እጅጉን ደንግጫለሁ እናም አዝኛለሁ፡፡ ይህ የአድኃኖም ድርጊት ለኢትዮጵያ ህጻናት እና ለወጣቱ ትውልድ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድን ነው? ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ዓይነት ምሳሌነት ነው እያስቀመጡ ያሉት? ልጆች፣ እሺ ይሁን ይዋሹ ምክንያቱም በምትዋሽበት ጊዜ ስህተት እየሰራህ ነው፡፡ ውሸቶች ጨዋነትን የተላበሱ እስከሆኑ ድረስ ተገቢ ናቸው በማለት ለልጆች እየተናገሩ ነውን? የ20 ሚሊዮን ዶላር ጨዋ ውሸቶች የሞራል ዝቅጠት እና ስህተት የለባቸውም ምክንያቱም ልጆች መታመን አለባቸው በማለት እያስተማሩ ነውን? ለኢትዮጵያ ወጣቶች ምን ዓይነት አርዓያነትን ነው በማስተማር ላይ ያሉት? አድኃኖም የዚህን አዋራጅ ቅሌት ጉዳይ ከኢትዮጵያ ህጻናት ልጆች እና ወጣቶች አመለካከት አንጻር ተመልክቶታልን? ወጣቷ ልጅ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተምሳሌት ቀንዲል እንድትሆን አድኃኖም ጽኑ ፍላጎት አድሮበታል፡፡ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ጉዳይ ቅሌት መሆኑ በአደባባይ እየታየ እና በህዝብ ዘንድ እየታወቀ በአድኃኖም በኩል ወጣቷ ልጅ ምን ዓይነት የተምሳሌትነት ቀንዲል እንድትሆን ነው የተፈለገው? አድኃኖም የፈጠሩት የተምሳሌትነት ቀንዲል በአሁኑ ጊዜ የተዋረደ እና በቅሌት የተዘፈቀ አጭበርባሪነት ተብሎ የተወገዘ ስለመሆኑ ደንታ አላቸው እንዴ?

አድኃኖም ስለሞራል ስብዕና አመክንዮ ችሎታ አላቸውን? ልጆች እንደልጅነታቸው መዋሸታቸው ስህተት የለውም ብለን ብናምንም እንኳ እንደ አዋቂ ሰው መዋሸት ስህተት የሚሆነው ለምንድን ነው? በእርግጥ ውሸት እና ሸፍጥ በተንሰራፋበት ምድር መዋሸትም ፍጹም ተገቢ ነው የሚለው አባባል ትክክል ነው፡፡ ይቅርታ ሊደረግለት የማይችለው እና በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የሌለው ነገር ግን አሁን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የዲፕሎማሲ ሰው ከህዝብ ነቀፌታ፣ ከቅሌት እና ውግዘት እራሳቸውን ለመከላከል በማሰብ ውሸት ጨዋነትን የተላበሰ ስህተት ነው በማለት ጉንጭ አልፋ እና አመክንዮ የሌለው ክርክራቸውን የመቀጠላቸው ጉዳይ ነው፡፡ ካፈርኩ አይመልሰኝ መሆኑ ነው እንጅ በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ውሸት ውሸት እንጅ መቸውንም ጊዜ ቢሆን ውሸት ጨዋ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ባህላችንም አይደለም አድኃኖም ሊበርዝብን ካልሆነ በስተቀር፡፡ ስህተት በነጠረ እውነት እንጅ በእራሱ በስህተት አይታረምም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ጨዋ ውሸት ያው ውሸት እንጅ በፍጹም ጨዋነትን ሊላበስ አይችልም፡፡ ስለሆነም በሀገር ላይ እየተሰራ ያለው ደባ እና ሸፍጥ በምንም ዓይነት መልኩ ይቅርታ ሊደረግለት የማይገባ የሞራል ስብዕና ወንጀል ነው፡፡

የሞራል ሰብዕና መሪዎች ወጣቶች እንዲዋሹ በፍጹም አያደፋፍሩም ወይም ደግሞ ውሸትን ታላቅ ቅሌት እንጅ የደግ ነገር ተምሳሌት ነው ብለው አቃልለው አይመለከቱም፡፡ የሞራል ሰብዕና መሪዎች ወጣት ውሸታሞች ውሸትን እንዲፈበርኩ ትዕግስቱ የላቸውም ወይም ደግሞ ጨዋ ዋሾች በማለት ይቅርታ አያደርጉላቸውም፡፡ የሞራል ሰብዕና መሪዎች በስህተት ነው ውሸት የተነገረው ለሚለው ምንም ዓይነት ይቅርታ የላቸውም፡፡ አንድ ህጻን የቤት ስራውን ወይም ስራዋን ባለማከናወኑ/ኗ ምክንያት የቤት ስራውን ውሻው በላው በማለት መዋሸት የለበትም/የለባትም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድ መንግስታዊ የሆነ ተቋም በእርግጠኝነት ውሸት፣ ተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ መሆኑን አስረግጦ እያወቀ ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግበናል በማለት መዋሸት በምንም ዓይነት መልኩ ትክክል አይደለም፡፡ ልጆቻችን ሀቀኞች፣ የተከበሩ፣ ሞገስን የተላበሱ፣ ላመኑበት ዓላማ ጽኑዎች እና ግልጾች እንዲሁም ታማኞች እንዲሆኑ እነዚህን መሰረታዊ እሴቶች በቤት እና በትምህርት ቤቶች እንዲማሩ እናደርጋለን፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹ የሞራል ስብዕና እሴቶች በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምድር ውስጥ ቦታ የላቸውም፡፡

በተደጋጋሚ ስናገረው እንደቆየሁት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የሬክ/የጀርመን የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር የነበሩትን የጆሴፍ ጎቤልስን እንዲህ የሚለውን መርህ አበርትተው ይከተላሉ፣ “ታላቅ ውሸት ከዋሸህ እና ይህንኑ ውሸት ደግመህ ደጋግመህ ከፈጸምከው በመጨረሻው ጊዜ ህዝቦች ማመን ይጀምራሉ፡፡ ውሸቱ ተደጋግሞ የሚነገረው መንግስት በህዝቡ ላይ ከተነሳበት የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት እና/ወይም ወታደራዊ የውሸት ውጤቶች በህዝብ ከሚወሰዱ እርምጃዎች እራሱን ለመደበቅ ሲል ብቻ በዚያን ጊዜ የሚፈጽመው ድርጊት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መንግስት ያለውን ኃይል ሁሉ በመጠቀም ሰላማዊ አመጸኞችን ለመጨቆን፣ እውነት ዋና የውሸት ጠላት በመሆኗ እና ከዚህም በመነሳት እውነት ዋነኛ የመንግስት ቀንደኛ ጠላት ስለሆነች ውሸትን እንደ በቀቀን መድገም እና መደጋገም አስፈላጊው ነገር ነው፡፡“

አድኃኖም እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሆን ብሎ እንደ በቀቀን ደግሞ እና ደጋግሞ የመዋሸትን የጎቤልን ትምህርት ወደ ላቀ እና ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግረውታል፡፡ የ20 ሚሊዮን ዶላር ውሸትን በመፈብረክ ውርርድ ገብተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ውርርድ በጽናት በሚታገለው መርማሪ ጋዤጠኛ አበበ ገላው ሙያዊ ክህሎት ተራ ቅጥፈት ሆኖ በመገኘቱ ውርርዳቸውን አጥተዋል፡፡ ውርርዱን ማጣት ብቻም ሳይሆን በቅሌት ባህር ውስጥም ተዘፍቀው በመንቦጫረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ላለፉት አስርት ዓመታት ስለኢትዮጵያ ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዓመታዊ ዕድገት ታላቅ ቅጥፈትን ፈጽመዋል፣ ሆኖም ግን የለየለት ውሸት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተይዘዋል፡፡ ስለሆነም እነርሱ ሊቃወሙት የማይፈልጉት እንዲህ የሚል ስጦታ ልሰጣቸው እፈልጋለሁ፡ ስለባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ስለ 20 ሚሊዮን ሽልማት፣ ምርጫዎች የሚዋሹትን ታላቅ ውሸት የሚያቆሙ ከሆነ እና ሌሎች በየሳምንቱ አዳዲስ ተራኪ ቅጥፈቶችን ከመፈብረክ የሚታቀቡ ከሆነ እኔም እንደዚሁ በየሳምንቱ ሰኞ እውነታውን በማውጣት ስለእነርሱ ቅጥፈት የምዘግበውን አቆማለሁ!

የወያኔ የቅጥፈት ዲፕሎማሲ እና ዋና የዲፕሎማት ሰው፣

የአድኃኖምን ድፍረት የተቀላቀለበት የዲፕሎማሲ አካሄድ እስከ አሁን ድረስ ተከታትያለሁ፡፡ በቪዲዮ የተቀረጸውን እና ለህዝብ የቀረበውን ተመልክቻለሁ፡፡ እናም እሱም ያደረገዉን ንግግር በማነብበት ጊዜ ማመን ተስኖኝ እራሴን በመያዝ አግራሞቴን ገልጫለሁ፡፡ የሀሳብ ምጥቀት ዳህራቸው ቅርብነት አስደንጋጭ ነው፡፡ የሚያደርጓቸው ንግግሮች ምንም ዓይነት ጥቅም እና ፋይዳ የሌላቸው በመሆናቸው ጥራት ይጎድላቸዋል፣ እንደዚሁም ደግሞ የነገሮች ተያያዥነት የላቸውም፡፡ እጅግ በጣም ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ አሁን ጊዜ ያለፈባቸውን እና የቀሩትን ቃላት እና ሀረጎችን በመጠቀም አሁን በህይወት የሌሉትን አለቃቸውን ለመምሰል ይታትራሉ፡፡ ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲን በማወቅ በኩል በጣም አናሳ የሆነ ግንዛቤ አላቸው፡፡ አጅግ በጣም መሰረታዊ የሆኑ የዓለም አቀፍ ህጎች፣ ውሎች እና ስምምነቶች እውቀት ግንዛቤ እና መጠነኛ የሆነ ዕውቀት አንኳ ያላቸው ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አያሳዩም፡፡ ያቀረብኳቸውን ነጥቦች ተጨባጭ ለማድረግ አስረጅ ምሳሌዎችን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

1ኛ) የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC በኡሩ ኬንያታ እና በዊሊያም ሩቶ ላይ መስርቶት ከነበረው ክስ ጋር በተያያዘ መልኩ፣

የኬንያ ፕሬዚዳንት በሆኑት በኡሁሩ ኬንያታ እና በእርሳቸው ምክትል በሆኑት በዊሊያም ሩቶ ላይ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ መስርቶባቸው እ.ኤ.አ ለጥቅምት 2013 ተይዞ ለነበረው ቀጠሮ ቅድመ ዝግት ለማድረግ እና ክሱ እንዲቋረጥ ወይም እንዲራዘም ለማድረግ በማሰብ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ አድርጎት በነበረው ጉባኤ ላይ አድኃኖም ቀንደኛ አስተባባሪ በመሆን በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ካልተቋረጥ የአፍሪካ ሀገሮች በሙሉ የሮማን ስምምነትን በመርገጥ በጅምላ ጥለው እንዲወጡ ሲያስተባብር ነበር፡፡ በአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ በመገኘት አድኃኖም እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፡

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ኢላማ በማድረግ እራሱን ወደ ፖለቲካ መሳሪያነት አሸጋግሯል፡፡ ይህ ዓይነቱ ትክክል እና ፍትሀዊ ያልሆነ አያያዝ ፍጹም ተቀባይነት የለውም፣ እናም ለዚህ ነው በICC ላይ ያለንን ስጋት ስንገልጽ የቆየነው…የኬንያን ፕሬዚዳንት እና ምክትላቸው ህገ መንግስታዊ ግዴታዎችን እና ኃላፊነቶችን ለመወጣት እንዲችሉ የራሳቸውን ስብሰባ እንዲመርጡ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቀድላቸው ያቀረብነውን ጥያቄ አዎንታዊ ምልሽ አላገኘም…ኬንያን እና አህጉራችንን የሚበጠብጥ እንደዚህ ያለ የተጠርጣሪ/ሰለባ ዓይነት አቀራረብ አንፈልግም…የመንግስታት ርዕሰ ብሄሮች ሊከሰሱ አይችሉም እና ያለመከሰስ ከለላ አላቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሆኑ ውሳኔዎችን ይዘን መውጣት ይኖርብናል…ይኸ ጉዳይ በኬንያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ላይ ትልቅ የሆነ መዘዝ ሊያመጣ የሚችል ለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር አይደለም… ምናልባትም ይህ ጉዳይ በICC እንዴት መያዝ እንዳለበት ወደፊት አፍሪካ ከICC ጋር በሚኖራት ግኙነት ላይ ጠንከር ያለ እንደምታ ይኖረዋል… ICC በእንደዚህ ያለ ሁኔታ በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ የበላይነቱን እያሳዬ መኖር እዲቀጥል መፍቀድ የለብንም፡፡

በጉባኤው የመዝጊያ ስነስርዓት ንግግር ላይ አድኃኖም በባዶው የድል አድራጊነት መንፈስን በተላበሰ መልኩ ተኩፍሰው ታይቷል፡፡ በሮም ስምምነት መሰረት ሁሉንም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገሮች አሳድመው ከICC አባልነት በጅምላ እንዲወጡ ሊያደርጉት የነበረው ዕቅዳቸው ሙሉ በሙሉ ከሸፈበት፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጥሎ ነበር፡

ICC ዓለም አቀፍ የፍትህ አገልግሎቱን ለመስጠት ሲል የሚጠቀማቸውን የአድልኦ አሰራሮች ውድቅ አድርገናል፡፡ እንደዚሁም ICC በአፍሪካ በተመረጠ መልኩ በአድልኦ የሚፈጽማቸውን ተግባራት ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ የተሰማንን ቅሬታ ግልጽ አድርገናል፡፡ በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ርዕሰ ብሄር እና በምክትላቸው ላይ በተመሰረተው የICC ክስ በጣም የተጎዳንበት እውነታ መፈጠሩን እና ይህም ሁኔታ የኬንያን ሉዓላዊነት የተዳፈረ መሆኑን ያመላክታል…

የኬንያታን እና የሩቶን በICC ከመከሰስ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ አድኃኖም በሰጠው ትንታኔ ላይ የፍሬ ነገር ጭብጥ፣ የሕግ እና የአመክንዮ ግድፈት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ኢላማ በማድረግ እራሱን ወደ ፖለቲካ መሳሪያነት አሸጋግሯል የሚለው የአድኃኖም ፍረጃ ይህ ድርጊት እውነት ስለመሆኑ ቅንጣት ያህል ማስረጃ ማቅረብ አይችልም፡ ICC በአፍሪካ እና አፍሪካውያን ላይ የበላይነትን በማሳየት አድሎአዊ አሰራርን ያራምዳል ለሚለው ውንጀላ ተራ አሉባልታ ካልሆነ በስተቀር በተጨባጭ ምንም ዓይነት የቀረበ ማስረጃ የለም፡፡ ምንም!

አድኃኖም ተጨባጭነት ያለው እና በማስረጃ እና በሕግ በተደገፈ አሰራር ሳይሆን ማሸነፍ የፈለገው የICCን ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ነው፡፡ አድኃኖም በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ አስቀድመው ያለምንም ማስረጃ የእራሱን ሀሳብ በመጫን እና የእርሳቸውን ሀሳብ እንዲቀበሉ ጥረት በማድረግ የሌሎች ሰዎች ስሜቶች እንዲጎዱ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም በአድኃኖም እምነት መሰረት የነጮቹ የICC ዳኞች እና አቃብያነ ሕጎች የእነርሱን የዱሮውን የቅኝ አገዛዝ ስርዓት በICC አማካይነት በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ ለመጫን ጥረት እያደረገ ነው በማለት ሌሎችም በስሜታዊነት የእርሱን በማስረጃ ያልተደገፈ ውንጀላ በመከተል ተንጋግተው እንዲወጡ ለማድረግ ጥረት አድርግዋል፡፡ እውነታው ግልጥልጥ እና ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን በሚገዟት ሀገር በአሁኑ ጊዜ እየተገበሩት እንዳሉት ሁሉ ልምዳቸውን ከፍ በማድረግ በአፍሪካ በአሁጉር ደረጃ የዘር ካርድን ነቅሶ በማውጣት ነጮቹን የICC ሰዎች አሳፍረው እና አሸማቅቀው ለማባረር ያደረጉት የህጻን ዓይነት ጨዋታ እራስን ከትዝብት ላይ ከመጣል በስተቀር አንድም የፈየደው ነገር አልነበረም፣ ሊኖርም አይችልም፡፡

ዘረኝነትን አህጉር አቀፍ ለማድረግ ያደረጉት ያልተሳካ ሙከራ በአጫፋሪዎቻቸው ዘንድ ሊደገፍ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንም የሚያስብ አዕምሮ ባለው ሰው ዘንድ የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም፡፡ እውነታው ግን ICC እንደ እራሱ በጎጥ እና በመንደር የጠባብነት የዘር ስሜት የሚነዳ ሳይሆን በዘር፣ በመልክዓ ምድር እና በጾታ ህብረ ውህድ ያለው ለሰው ልጆች ሁሉ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ፍትህ በዓለም ላይ ሁሉ እንዲሰፍን የሚታገል ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ነው፡፡ በእርግጥ የእርሱ የይስሙላ አለቃ የሆነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ICC ዘር አዳኝ ነው በማለት በይፋ በአደባባይ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያ ንግግር እኔ በግሌ በጣም ነው ያፈርኩት እና ውርደት የተሰማኝ፡፡ ከድፍን 60 ዓመታት የነጻነት ህይወት በኋላ የአፍሪካ መሪዎች የዘር ካርድን እየመዘዙ ማውጣቱን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ምን ዓይነት የወረደ አሳፋሪ ድርጊት ነው!

እንደዚሁም ደግሞ ICC በማንኛውም የአፍሪካ ተጠርጣሪ ላይ አግባብነት የሌለው ድርጊት ለመፈጸሙ እና ፍትሀዊነት የጎደለው አሰራር ለመስራቱ ከመወንጀል በስተቀር ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ የአድኃኖም ድብቁ የክርክር ጭብጥ ግን ICC አፍሪካን እና አፍሪካውያንን በሰብአዊ መብት ወንጀሎች ይከሳቸዋል ምክንያቱም ጥቁር ስለሆኑ ነው የሚል አራምባ እና ቆቦ ሆኖ ይገኛል፡፡ የተከበሩ አድኃኖም ለመሆኑ አፍሪካውያን በዘር በICC ክስ ይመስረትባቸዋል ከተባለ በዘር ተከሰሱ እንዳይባሉ ንጹሀን ህዝቦችን ይፍጁ፣ ዕልቂት ይፍጠሩ፣ ያውድሙ እንደፈለጋቸው ይሁኑ እንዲባል ነው ፍላጎቱ? ወይስ ደግሞ ይህ የአምባገነንነት ሰይጣናዊ አስተሳሰብ የተጠናወተው የአፍሪካ ጥቁር ወሮበላ ዘራፊ በጠብመንጃ አፈሙዝ ስልጣንን እየጠቆጣጠረ እንደፈለገው በህዝቦች ላይ እልቂትን እየፈፀመ ሀብት እና ንብረታቸውን እየቀማ ባለበት ሁኔታ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ላጠፋው ጥፋት ተጠያቂ ይሁን መባሉ ለአፍሪካ ሲሆን እንዴት በዘር ነው ሊባል ይችላል?

ነጭ የቆዳ ቀለም ያለው ሰውም ቢሆን ሰብአዊ መብትን እስከደፈጠጠ ድረስ ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ ይኸ ነገር የዘር እና የቆዳ ጉዳይ አይደለም፡፡ በርካታ መብት ደፍጣጮች በአፍሪካ ውስጥ የመገኘታቸው ሁኔታ እውነት ነው፣ ስለዚህም በርካታዎቹ ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉም ቢባል ወንጀለኞች እስከሆኑ ድረስ የአፍሪካው አምባገነኖች በህግ መጠየቃቸው ከዘር ጋር የሚያገናኘው አንድም ነገር የለም፡፡ አድኃኖም ወይም ደግሞ በዚህች መከራዋ ባላለቀላት ሀገር መሰረትሁት እንዳሉት የዘር የፖለቲካ ዥዋዥዌ ጨዋታ ሁሉ እንደ ብሄር ብሄረሰቦች የይስሙላ በዓል አከባበር እንደምታደርጉት ሌሎች ወንጀል ያልሰሩትን አህጉሮች ሁሉ በመጨመር በኮታ ከአፍሪካ፣ ከአሜሪካ፣ ከኢስያ፣ ከአውሮፓ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከአውስትራሊያ….ይህን ያህል ሰብአዊ መብት ደፍጠጮች በICC ክስ ተመሰረተባቸው እንዲባል ይፈለጋል? የይስሙላ የመንደር እና የቀበሌ ኮታዎን እንደለመደው እዚሁ በመንደር እና በቀበሌዎ ያድርገው፡፡ እውነተኛውን ዓለም አቀፋዊ የፍትህ አካሉን ስም ማብጠልጠሉን እና ጥለሸት መቀባቱን ግን ፋይዳ አላስገኘለትምና፡፡

ቀደም ሲል እንደነበረው ቅኝ ገዥዎች ሁሉ የነጮቹ የICC ዳኞች እና ዓቃብያነ ሕጎች በፍርድ ቤት እያስቀረቡ የአፍሪካን መሪዎች ይገድላሉ፡፡ በእርግጥ ይህን አባባል ማራመድ የለየለት ድድብና ነው! ICC በአፍሪካ ላይ ሰብአዊ መብቶችን የደፈጠጡትን ወንጀለኞች ለሕግ በማቅረብ ፍትህን ይሰጣል፡፡ ከዚህ አንጻር ዊሊያም ሱቶን ለተባለ አንድ የአሜሪካ የታወቀ ባንክ ዘራፊ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው እንዲህ የሚለው መልስ ትዝ አለኝ፣ “አንተ ባንኮችን ሁልጊዜ የምትዘርፈው ለምንድን ነው?“ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ የሚል ቆምጫጫ መልስ ሰጠ፣ “ምክንያቱም ገንዘቡ የሚገኘው እዚያ መሆኑን ስለማውቅ ነው፡፡“ እንደዚሁም ሁሉ ICC የፍርድ ሂደቱን ቀጥሎ ያለው በአፍሪካ ተጠርጣሪዎች ላይ ነው ምክንያቱም አብዛኞቹ ተጥርጣሪ ወንጀለኞች የሚገኙት በአፍሪካ በመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ የሮም ስምምነት መሰረት ያደረገው እ.ኤ.አ ከ2002 ወዲህ ለተፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀሎች ብቻ ነው፡፡

አድኃኖም ስለICC ያላው የሕግ ሂደት ግንዛቤ ከእርሱ የፍትህ ስርዓት ጋር በጣም የሚመሳሰል መስሎ ታይቶታል፡፡ እንደ ወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሁሉ ለአባላት፣ ለተባባሪዎች እና ለደጋፊዎች አንድ ዓይነት ሕግ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን/ት ደግሞ ሌላ ሕግ እንደሚያወጡ ሁሉ አድኃኖም ለICCም በተመሳሳይ መልኩ እንደዚህ ያለ ሕግ መውጣት እንዳለበት ያምናል፡፡ ICC በሰብአዊ መብት ወንጀል ድፍጠጣ ለሚጠየቁ ተጥርጣሪዎች ሁለት ዓይነት ሕግ አያወጣም፡፡ ለሀገር መሪ ወንጀለኞች ለሌሎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ተብሎ የሚወጣ ሕግ የለም፡፡ በአድኃኖም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ዋናዎቹ የፓርቲው አባሎች ክስ ሊመሰረትባቸው የሚችሉት ከፓርቲያቸው ውጭ ለየት ያለ ሀሳብ ማሰብ ሲጀምሩ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ በሙስና ስም ክስ ይመሰረትባቸዋል፡፡ አንግዲህ ወያኔ በእንደዚህ ያለ የሕግ ሂደት ነው ገና ከጫካ ጀምሮ እስከ ወታደራዊው ደርግ ድረስ ሲካሄድ በነበረው የትጥቅ ትግል ዋና ዋና የሚባሉትን ወታደራዊ አዛዦቻቸውን በመግደል ስልጣናቸውን እያመቻቹ እዚህ የደረሱት፡፡

2ኛ) አድኃኖም ለአፍሪካ ህብረት ያቀረቡት የክርክር ጭብጥ የኡሁሩ እና ሩቶ ህገመንግስታዊ ግዴታዎቻቸውን እና ኃላፊነቶቻቸውን እየተወጡ ነው ወደ ICC የፍርድ ሂደት ችሎት መቅረብ ያለባቸው፣

አድኃኖም ኬንያታ እና ሩቶ በሰው ልጆች ላይ ስለፈጸሙት በጣም ከፍተኛ የዕልቂት ወንጀል፡ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የዘር ማጥፋት፣ እና የጦር ወንጀለኝነት ጉዳይ ከምንም አልቆጠረዉም፡፡ ይህ ድርጊት የሚያሳየው ገዳዮች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ እና ሌሎችም አሰቃቂ የሆኑ የሰው ልጅ መብቶችን የሚደፈጥጡ ወንጀለኞች እንደ ወንጀላቸው ሕጉ በሚፈቅደው ሳይሆን እነርሱን እንደተመቻቸው ወደ ICC ብቅ እያሉ የፍርድ ሂደታቸውን ጉዳይ ይከታተሉ ማለት አድኃኖም በሕጉ ላይ ምንም ዓይነት እውቀት እንደሌላቸው ከማሳየቱም በላይ ለሰው ልጅ ህይወት ምን ያህል የቀለለ አመለካከት እንዳላቸው በተጨባጭ ያመላክታል፡፡ ያ ቢደረግ ኖሮ ICC ማን ተብሎ ሊጠራ ነበር? ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Crimininals Court መባሉ ቀርቶ ዓለም አቀፉ የዝንጀሮዎች ፍርድ ቤት/International Kangaroo Court ነው ሊባል የሚችለው፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝን አቋም ለመቀየር እምነት አድሮብኛል፡፡ ይህም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምንም ዓይነት የፍትህ አካል ሳይጎበኛቸው በ10ሺዎች እና ከዚያ በላይ የሚቆጠሩ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ተጠርጣሪ ወገኖቻችንን የፍርድ ሂደት ተጠርጣሪዎቹ በሚመቻቸው መንገድ እያመቻቸ እየተዝናኑ የፍርድ ሂደታቸውን እንዲከታተሉ የሚያደርግ ከሆነ የማቀርበውን ተቃውሞ በሙሉ ውድቅ በማድረግ በነጻ እሰናበታለሁ፡፡

3ኛ) አድኃኖም ICC ይህንን ቀላል የሆኑ የተጠርጣሪ/ሰለባ አቀራረብን በማራመድ በኬንያ እና በአህጉራችን ብጥብጥ ሊያስነሳ የሚችለውን ነገር ህብረቱ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል… የሚል ተማጽዕኖ ለጉባኤው አባላት ማቅረባቸው፣

በእርግጥ ይኸ አባባል ፍየሌን ያስገኝልኛል፡! አድኃኖም በኬንያታ እና በሩቶ የተፈጸሙት ወንጀሎች ቀላሎች እና ብዙም እርባና የሌላቸው አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል፡፡ እነዚያ ተጠርጣሪዎች በአንቀጽ 25 (3) (a) ስር በዝርዝር በቀረቡት በሮም ስምምነት በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙ በአምስት ዓይነት ወንጀሎች ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡ ዝርዝር የህግ ጨብጦችም ሀ) ግድያ መፈጸም፡ በአንቀጽ 7 (1) (a) ስር የተጠቀሰው፣ ለ) ማጋዝ ወይም ደግሞ በግዳጅ ማፈናቀል፡ በአንቀጽ 7 (1) (d) ስር የተጠቀሰው፣ ሐ) አስገድዶ መድፈር፡ በአንቀጽ 7 (1) (g) ስር የተጠቀሰው፣ መ) ማሰቃየት፡ በአንቀጽ 7 (1) (h) ስር የተጠቀሰው፣ ሠ) ሌሎች ሰብአዊ ወንጀሎች፡ በአንቀጽ 7 (1) (k) ስር ተጠቅሶ የተጠቃለሉት ናቸው፡፡

ውንጀላዎቹ 155 ገጽ በያዘ ሰነድ በማስረጃ ተሟልተው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስክሮችን ቃል አካትተው በመያዝ የቀረቡ ሲሆን ለህሊና የሚሰቀጥጡ እና ዝርዝር ነበሩ፡፡ በ59 ቀናት ውስጥ ወደ 1,400 የሚሆኑ ሰዎች እንዲያልቁ የተደረጉ ሲሆን ሌሎች 600,000 የሚሆኑት ደግሞ ኬንያ አደገኛ በሆነ መልኩ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ወደሚመስል ደረጃ በተንሸራተተች ጊዜ ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ በህዝቦች ላይ የደረሰው እልቂት እና ውድመት አድኃኖም እንዳቀረቡት ቀላል የሚባል ነገር አልነበረም፡፡

ምናልባትም እንደዚህ ያሉት ዕልቂቶች እና ስቃዮች ለአድኃኖም ምንም ማለት ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም ለአድኃኖም እንደ እስታሊን ሁሉ የአንድ ሰው ሞት አሰቃቂ ነው፣ የ30 ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ግን የቁጥር ጉዳይ ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው የእርሱ አለቃ እ.ኤ.አ በ2005 በኢትዮጵያ የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ በእራሳቸው ስልጣን የጦር እና የደህንነት ኃይሉን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች እንዲገደሉ አድርጎ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት የሕግ ተጠያቂነት አልደረሰቤትም ነበር፡፡ ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎችን በመያዝ ኬንያታ እና ሩቶም የመለስን የህዝብ እልቂት በማየት እና ቢያንስ 182 ነፍሰ ገዳዮች እና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የግድያ ሙከራ አድራጊዎች በሕግ ሳይጠየቁ ምንም እንዳልሆኑ ግንዛቤ በመውሰድ ይህንን የፈሪዎች እና የደናቁርት ዕኩይ ድርጊት ከእነርሱ በመኮረጅ እነኬንያታ እና ሩቶ በኬንያ ህዝብ ላይ ፈጽመውታል የሚል የእራሴ እምነት አለኝ፡፡

4ኛ) በሀገር መሪዎች ላይ ምርመራ ማካሄድ እና በሕግ እንዲዳኙ ማድረግ ለኬንያ እና ለአፍሪካ በአጠቃላይ ውስብስብ የሆነ ችግርን ያስከትላል በማለት በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ክርክር ማቅረባቸው፣

አድኃኖም ይህንን የመሰል የክርክር ጭብጥ ማቅረቡ ፍጹም በሆነ መልኩ ትክክል ናቸው፡፡ ሟቹ መለስ እ.ኤ.አ በ2005 የተደረገውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ውዝግብ በርካታ ንጹሀን ዜጎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠቱ ምክንያት በICC ክስ ቢመሰረትበት እና ለሕግ ቢቀርቡ ኖሮ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ የተደረግውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ውዝግብ ሰበብ የኬንያ ህዘቦች እልቂት አይፈጸምም ነበር፡፡

ሆኖም ግን አድኃኖም የሮም ስምምነትን አጠቃላይ ሀሳብ ዘለውታል፡፡ ICC የተቋቋመው እያንዳንዱ ነፍሰ ገዳይ ዘራፊ ከቢሮው በምቹ ተሸከርካሪ ወንበር ተቀምጦ ነገ ደግሞ እነማንን ልግደል፣ ልድፈር፣ ላፈናቅል እያለ በሰው ልጆች ስቃይ ላይ ዳግም ስቃይ እየደገሰ ተዝናንቶ በተቀመጠበት ሁኔታ አይደለም የሕግ ጉዳዩ የሚታየው፡፡ ድርጅቱ ዓላማ አድርጎ የያዘው እጅግ በጣም ጨካኝ የሆኑ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለፍትህ በማቅረብ ለወንጀል ሰለባዎቹ ፍትህን ለመስጠት እና እንደዚሁም ሁሉ በእብሪት በመነሳሳት ወደፊትም በሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተመሳሳይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ለመማሪያ እንዲሆኑ ማስቻል ጭምር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ ውስጥ ያለምንም ተጠያቂነት በሰው ልጆች ላይ ወንጀል በሚፈጽሙ አምባገነኖች፣ የጦር ወንጀለኞች እና የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሚፈጽሙ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ላይ ICC ፍትህን የሚያጎናጽፍ እርምጃ የሚወስድ በመሆኑ በአፍሪካ መሪዎች፣ አምባገነኖች እና ጦረኞች ላይ አስፈሪ እና አስደንጋጭ ሁኔታ መፍጠሩ ከጥያቄ ሊገባ የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ ወንጀልን በሚፈጽሙ የአፍሪካ አምባገነኖች ላይ ICC ተገቢ የሆነውን እርምጃ የሚወስድ ከሆነ ይህንን እንደ ትምህርት በመውሰድ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት አምባገነኖች ከህግ አግባብ ውጭ የእራሳቸውን ዜጎች መብት ከመደፍጠጥ እንደዚሁም ሁሉ በጫካ ውስጥ ተደብቀው ያሉ ጦረኞች ከተደበቁበት ጫካ ውስጥ በመውጣት በዜጎች ላይ አሰቃቂ እና ጭካኔን የተሞለባት ዕልቂት ከመፈጸም ይታቀባሉ፡፡

አድኃኖም የሀገር መሪዎች በህግ መጠየቅ የለባቸውም ምክንያቱም እነርሱ የሕግ ተጠያቂ የሚሀኑ ከሆነ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ይጣሳል ይላሉ፡፡ እንደ ወንጀለኛ አቀራረብ ስነስርዓት ኡሁሩ እና ሩቶ በፈቃደኝነት ለICC ቀረቡ፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት የሉዓላዊነት ጥያቄ የለም፡፡ አድኃኖም ምን ለማለት ፈልጎ ነው!? እንደ እርሱ አባባል ሉዓላዊነት ማለት ሀገሪቱ፣ ድንበሯ እና ጠቅላላ ህዝቧ መሆናቸው ቀርቶ ሉዓላዊነት ማለት አንዱ ፈላጭ ቆራጭ የሀገር መሪ ተብዬው ነው፣ ስለዚህ እርሱ የሰብአዊ መብት ደፍጥጦ ለICC የፍትህ አካል የሚቀርብ ከሆነ ሉዓላዊነት ተደፈረ ነው ነው እያሉን ያሉት! ለማሰብ ቀርቶ ለመስማትም ያሳፍራል!

የአፍሪካ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ ወንጀልን ሲፈጽሙ፣ የጦር ወንጀል ሲፈጽሙ እና የዘር ማጥፋት ወንጀልን ሲፈጽሙ ምርመራ እና ለፍትሀ አካል ቀርበው እንዲዳኙ የማይደረገው ለምንድን ነው? አድኃኖም ለዚህ ጥያቄ ምንም ዓይነት መልስ የለዉም፣ ዝም ብሎ ምንም ዓይነት አመክንዮ ሳይኖር በደፈናው ያለምንም ማስረጃ በቀኖናዊነት የሚቀመጥ ካልሆነ በስተቀር ይህ ነው የሚሉት ምሁራዊ አንደበት የላቸውም፡፡ አድሃኃኖም ስለዚህ መሪዎቹ ያለመከሰሳቸው ትክክል ነው ብቻ ነው የሚለው ከዚህ ያለፈ የሚለው ነገር የለም፡፡

አድኃኖም ሆን ብሎ በድንቁርና በሰው ልጆች ላይ የተሻሉ እና መጥፎ የሰብአዊ መብት ወንጀሎችን፣ የጦር ወንጀለኞች እና የዘር ማጥፋት ወንጀለኞችን የሚፈጽሙ የሚባል ነገር የለም፡፡ እንደዚህ ያሉትን ሰብአዊ ወንጀሎች በሚፈጽሙ በአንድ የሀገር መሪ እና በአንድ የጦር ወንጀለኛ መካከል ምንም ዓይነት የሞራል እና የሕግ ልዩነት የለም፡፡ እንደ አድኃኖም ባለ የተንሻፈፈ እና አመክንዮየለሽ ሀሳብ ከሆነ ከአፍሪካ በቋፍ ላይ ካለ የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ወንጀል የሚፈጽም የሀገር መሪ ፍጹም ሊከሰስ አይችልም፡፡ ከፍተኛ የሆነ እልቂት እና ውድመት ፈጽመው ስልጣንን በኃይል የሚቆጣጠሩ አማጺ መሪዎች እና የጦር አበጋዞች ወይም ደግሞ ምርጫን አጭበርብረው ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በስልጣን ማማ ላይ ፊጥ የሚሉ ወንጀለኞች እንደ አድኃኖም ባለ ለእራስ አገልግሎት የቆመ እና አስደንጋጭ መርህ የሚከተል እቡይ ካልሆነ በስተቀር እንደ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ለህግ ይቀርባሉ፡፡

እነዚህ የአፍሪካ አምባገነኖች “ርዕሰ ብሄር እና የሀገር መሪ በቢሮ ውስጥ እስካሉ ድረስ በሕግ አይጠየቁም” ይላሉ፡፡ በእርግጥ በስልጣን ላይ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እንደ ሱዳኑ ኦማር አልባሽር ያሉት ስልጣናቸውን በመጠቀም ለበርካታ አስርት ዓመታት የሰብአዊ መብት እልቂትን እየፈጸሙ የሀገር መሪ በመሆናቸው ምክንያት በሕግ አግባብ የማይሞከሩ አይነኬ፣ ከማንኛውም ዓይነት ተጠያቂነት እና ከሕግ በላይ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአማጺ፣ ወታደራዊ እና የጦር አበጋዝ መሪዎች እነርሱ እራሳቸውን ብቻ ለዚያች ሀገር መድህን እና ጥሩ መሪዎች አድርገው በማቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ እና ከሕግ ፊት ያለመቅረብ መብት እንዳላቸው ከመጠየቅ ማን ያግዳቸዋል?

በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውን/ት ሠራተኞች ስቃይ፣

እ.ኤ.አ ሕዳር 2013 በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ፣ እና በሳውዲ አረቢያ አገዛዝ፣ በፖሊስ እና በተራው ህዝብ የውርደት ድርጊት ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት አድኃኖም በታዛዥነት እና እራስን ባዋረደ መልኩ በኢትዮጵያውያን ላይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ያካሄደውን አገዛዝ ተጻራሪ በሆነ መልኩ ይቅርታ ጠየቁ፡፡

ይኸ ድርጊት ሌላ ሳይሆን በሽታ ነበር፡፡ በወገኖቻችን ላይ ሲደረግ የነበረው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ አድኃኖም እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሳውዲ ባለስልጣኖች ህገ ወጥ የሆኑ ስደተኞችን መልሶ ወደ ሀገራቸው ለማጋዝ ያወጣውን ፖሊሲ እና ስላስተላለፉት ውሳኔ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር ትገልጻለች፡፡“ ይኸ ንግግር በዲፕሎማሲ ቋንቋ አሳዛኝ የሆነ ደንታቢስነት፣ ብቃየለሽነት እና ለተያዘው ቦታ ሊመጥን የማይችል እርባናየለሽነት ነው፡፡ አድኃኖም ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ በደረሰባቸው ህገወጥ አያያዝ ስሜታቸው የተጎዳ መሆኑን አምነው በመግለጽ ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር ይኸ ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ተናግረው ነበር፡፡ እርሳቸው እና መንግስታቸው ነገሮችን እንዴት ተቆጣጥረው እንዳለ ለማሳየት በሚመስል መልኩ አድኃኖም እንዲህ ብለው ነበር፣ “ወገኖቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እና ለመቀበል ዝግጅታችንን ሁሉ ያጠናቀቅን መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“

አንድ የእራሱን ዜጎች ሰብአዊ መብት በመርገጥ የሚያዋርድን ሌላ ሀገር ፖሊሲ እንዴት ነው ሊያከብር የሚችለው? አንድ ጤናማ አዕምሮ ያለው ሰው ዜጎቹ ለተደፈሩበት፣ ለተገደሉበት፣ አካለ ጎደሎ ለሆኑበት፣ለተሰቃዩበት እና በውጭ ሀገር እህት እና ወንድሞቻቸው ለተገደሉባቸው ዜጎቹ እንዴት “ተቀባይነት የለውም” የሚለውን ትርጉመቢስ እና እርባናየለሽ ቃል ምርጫው ያደርጋል? በሳውዲ አረቢያ ሲያልቁ የነበሩትን ወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ እና ግድያውን ለማስቆም አድኃኖም ለሳውዲ አረቢያ አምባሳደር መጮህ ነበረባቸው፡፡ እንዴት አንድ ወገኖቹ የግድያ ሰለባ ሲሆኑ እና ሰብአዊ መብታቸው ተደፍጥጦ እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ ግላዊ ጭንቀት እና ሀዘን ይሰማኛል ሊል ይችላል? አንድ ሰው እንዴት የዜጎቹ መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች በአምባገነኖች ሲጣሱ እና ሲደፈጠጡ እንዴት ምንም ነገር ባለማድረግ ቀዝቅዞ እና የሰብአዊነት ርህራሄ ሳይኖረው ዝም ብሎ ይመለከታል? እንዴት አንድ ሰው ዜጎቹ ስቃያቸውን እየተቀበሉ እያየ በመበሳጨት ዲፕሎማሲያዊ ቁጣውን እና ንዴቱን መግለጽ ይሳነዋል? በሺዎች ለሚቆጠሩ ስለእህቶቻችን እና ወንድሞቻችን በሞት እና በሽረት መካከል መኖር እየተነጋገርን ነው፡፡ ደህና ይኸ ነው እንግዲህ አሁን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ባለስልጣን እየሰራው ያለው ስራ!

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 የአድኃኖም አንዱ ደጋፊ በሆነው ዘራፊ የዲፕሎማት ከለላ አለው ተብሎ በዋሽንግተን ዲ.ሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥይት ስለተኮሰው እና ያልተጠበቀ የዲፕሎማሲያዊ ቀውስ እንዲከተል ስላደረገው ሁከት ፈጣሪ ስለነበረው እብሪተኛ መናገር እችላለሁ፡፡ በዋሽንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማቶች መዝገብ ላይ ተቀርጾ የሚገኘው ሰነድ እንደሚያሳየው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብሰብ ሌባ ዲፕሎማት ተብዬ ሰላማዊ አመጸኞችን ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማባረር በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥይት በመተኮስ ከዓለም የመጀመሪያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

አድኃኖም በዓለም ዋናዋ እና የመጀመሪያዋ የዲፕሎማት ማዕከል በሆነችው በዋሽንግተን ዲ.ሲ ያንን የመሰለ ወሮበላ ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲ ልምድ፣ ስልጠና ወይም ደግሞ እንደ ከደህንነት አታሸ ሙያ ጋር ምንም ዓይነት ክህሎት የሌለውን ተራ ማይም ልከው ነበር፡፡ ደህና እስከ አሁን ድረስ ስለወሮበላ ዲፕሎማሲ እና ስለዘራፊ ዲፕሎማት ብዙ ብለናል፡፡

በእውነት የብሩክሊንን ድልድይ እጅግ በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ ለሽያጭ ለማቅረብ ዕድሉን አግኝቻለሁ፡፡ የማዲሰን እስኩዌር ጋርደን ህንፃን እንደ ጉርሻ በተጨማሪነት አባሪ በማድረግ እሰጣለሁ፡፡

አድኃኖም ፍላጎት ሊኖረህ ይችላል ?

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም

Filed in: Amharic