>
5:13 pm - Sunday April 19, 8505

በኖርዌይ የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ጊዜያዊ ግብረ ኃይል የተሰጠ የአቋም መግለጫ !!

DCESON - Oslo Norway       

የባዕዳን ወራሪዎች ለሃገራቸው ቀናኢ በሆኑ ጀግኖች አባቶቻችን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ነጻነታችንን የተቀዳጀንበት እንዲሁም ለጥቁር ህዝብ አርአያ የሆንበት 119 የአድዋ በዓል በሚከበርበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነቱ ተዋርዶና ተንቆ በጥቂት ዘረኛ ፋሽስቶች  እየደረሰበት ያለው ግፍና መከራ ውሎ እያደረ እየመረረና እየከረፋ መምጣቱ ከማንም ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አደለም፡፡

አንባገነኑ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ በሃገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ሰቆቃ ለመታገል ኢትዮጵያንና ህዝቧን አስተማማኝ መሰረት ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለቤት ለማድረግና ከዚህ በዘር ከተደራጀ የሃገርና የህዝብ ጠላት ነጻ ለማውጣት በውጪም ሆነ በውስጥም ውድ ህይወታቸውን ለመስዋእትነት ያቀረቡና ለማቅረብ የተዘጋጁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና ይህው ዘረኛዉ የወያኔ ሥርዓት ከወትሮው በረቀቀ መልኩ በሃገር ውስጥ የሚደረገውን የነጻነት ትግል ለማዳፈን ከማሰርና ከማሰቃየት በዘለለ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ደፋ ቀና የሚሉ አውራና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የህዝብ ፓርቲዎች ሌት ተቀን የሚዘምርለት የይስሙላ ምርጫ ከመድረሱ በፊት የሥርዓቱ ክንፍ በሆነው የወያኔ ምርጫ ቦርድ ተብዬው አማካኝነት በነጻነት የመደራጀት መብታቸውን በመግፈፍ እንደበታተናቸውና ምርጫው ከመካሄዱ ከወራት በፊት ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ራሱን ለመጫን ብቻውን እሮጦ ብቻውን የሚያሸንፍበትን ጥርጊያ መንገድ እያመቻቸ መሆኑ በገሃድ እየታየ ነው፡፡

በሕዝብ ና በሃገር ላይ እየደረሰ ያለውን መረን የለቀቀ የዘረኛውን ቡድን  እኩይ ተግባር  እምቢኝ በማለት በውስጥም ሆነ በውጪም የሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግልና በኢትዮጵያችን እውን እንዲሆን የምንፈልገውን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስብዓዊ መብቱ ተከብሮ በነጻነት የሚኖርባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባትና ዘረኛውን የወያኔ ሥርዓት ለማስወገድ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከዚህ ከፋፋይ የዘረኛ ሥርዓት ለማላቀቅ የሚደረገው ትግል ለጥቂት የህብረተሰብ ክፍል የሚተው ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እነድትቀጥል የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ማድረግ የሚችለውን በማድረግ ሃገራዊ ግዴታውን የሚወጣበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተደረሰበት ወቅት ነው፡፡

ስለሆነም በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የነጻነት ትግሉ የሚጠይቀውን ሃገራዊ ጥሪ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትየዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  በአፕሪል 18፣2015 በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ሕዝባዊ ሥብሰባና የነጻነት ትግሉን የሚያግዝ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም በሃገራችንና በሕዝቧ ላይ ቀን ከሌት የሚደርሰው ሰቆቃ የሚያሳስበው፣ በወገኖቻችን ላይ በተለይ እምቢኝ ለሃገሬ እምቢኝ ለሕዝቤ ባሉ ንጹሃን የህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰው ዘግናኝ ሰቆቃ እንደወገን የሚቆጨው፣ ከአያት ቅድመ አያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጡት የዕምነት ተቋማት እንዲሁም ማህበራዊ እሴቶቻችን  በዚሁ ዘረኛ ቡድን መደፈርና መዋረድ ያስቆጣው፣  ምስኪኑ የሃገራችን ገበሬ ከቤት ንብረቱ መፈናቀል ለህሊናው የከበደው ፣. . . . . . . . ይህንንና ይህንን የመሳሰለ በሃገርና በሕዝባችን ላይ የሚደርሱ ተነግረው የማያልቁ ሰቅጣጭ በደሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከነ ሥርዓቱ ለማስወገድ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በሚደረገው ሃገራዊ ጥሪ ላይ በመገኘት የበኩልን ያድርጉ!! ለሚደረገው የነጻነት ትግል አጋርነትዎን በተግባር ያስመስክሩ!!!!

ቀኑ፣ አፕሪል 18፣ 2015

ሰአት፣ 15፣00 እስከ 22፣00

ቦታ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር በቅርብ ቀን ይገለጻል

የፌስቡክ ኤቨንት ገጻችንን ይጎብኙ እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ እንደሚመጡ ያረጋግጡ በተጨማሪም ጓደኛዎትን በዚህ ሃገራዊ ጥሪ ላይ ይጋብዙ፣

https://www.facebook.com/events/445434435611079/

ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ደምና አጥንት መስዋዕትነት ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!

 የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!

 ከስላምታ ጋር !!

Filed in: Amharic