>
4:11 pm - Wednesday January 23, 8441

በ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሠጠ መግለጫ

ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የጀመርነው የጋራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን የመጀመሪያ ዙር ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲሸጋገር ከሁሉ በማስቀደም የአንደኛው ዙር ዕቅዳችን ተግባራት ክንዋኔ ከዓላማችን ጎን ቆማችሁ በተለያየ መንገድ ለደገፋችሁን በአገር ቤትና በውጪ አገር ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን፣ በአንጻሩ ዕቅዳችን ከዳር እንዳይደርስ ህገመንግስታዊ መብታችንን በመጨፍለቅ ጉዞኣችንን ለማደናቀፍ የተቻላችሁን ህገወጥ የቢሮክራሲ መሰናክልና ለኢትዮጵያዊ ሠላማዊ ዜጋ ቀርቶ ለጠላት የማይገባ ኃይል በመጠቀም የመብት አፈና ለፈጸማችሁ የመንግሥት አካላት ሁሉ ወደ ኅሊናችሁ እንድትመለሱ ጥሪ በማቅረብ ነው፡፡ በተጨማሪ ለሁሉም ወገን የያዝነው ትግል የአገርና የህዝብ፣ተጠቃሚውም ሁላችንም/ሁሉም ዜጎች/ና የሁላችንም የጋራ አገራችን፣ለጉዞኣችን የመረጥነው መንገድ ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣መጓጓዣችን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም በማረጋገጥ ነው፡፡
ትብብራችን የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር፣በእኛ በኩል ከፊት ቆመን ትግሉን ለመምራት ያለንን ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ለዚህም የገባነውን ቃል በማደስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ‹‹በየትም የዓለማችን ክፍል አምባገነንነት የህዝቦችን የተባበረ የዲሞክራሲ ጥያቄ በኃይል አፍኖ በጨቋኝነት የዘለቀበት ታሪክ አልተመዘገበም›› ማለታችንን በማስታወስ ነው፡፡
ይህ ዕቅድ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ እንደመሆኑ ዓላማችንም የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ሚናችንም የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ደጋግመን እንደገለጽነው ነጻነት በሌለበት ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው፡፡
በመሆኑም የዚህ ዙር ዓላማችንም ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የጀመርነውን እንቅስቃሴ አጠናክሮና አስፍቶ በመቀጠል ለነጻ ፣ፍትሃዊ፣ተኣማኒ፣አሳታፊ….በአጠቃላይም ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ለህዝብ ተደራሽ በመሆን በህዝብ (የተለያዩ የህዝብ ክፍሎችን፣ አደረጃጀቶችንና ዜጎችን በማካተት) የነቃ ተሳትፎ ተጽዕኖ በማሳረፍ በምርጫ ሂደቱና አተገባበሩ ላይ ያነሳናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ ማድረግና ከዚህ ጎን ለጎን በቀጣዩ ምርጫ (2007) ተቃውሞ ጎራው በአጠቃላይ የትብብሩ አባላት በተለይ ድምጽ እንዳይሻሙ /የመራጩ ህዝብ ድምጽ እንዳይከፋፈል/ የሚያስችል ስልት በመቀየስ ከመራጩ ህዝብ ማድረስ ነው፡፡
በዚህ ላይ በመመስረት ትብብሩ በዚህ ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት አካቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት ፤በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡
4. አስተባባሪ ኮሚቴው ተግባራቱን በጊዜ ሠለዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት አጽድቋል፡፡
እዚህ ላይ ይህን ዕቅድ ስናወጣ መንግሥት/ጠቅላይ ሚ/ሩ/ ከቅርብ ቀን በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥትን መገዳደር አይችሉም›› የሚል ኃሳብ ያዘለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ማድመጣችንን፤ይህ መልዕክት የማደናገሪያና ማደናበሪያ ፕሮፖጋንዳ ስልትም ይሁን የተቃዋሚዎችን ዓላማና የመኖር ትርጉም የመጨፍለቅ ግልጽ መልዕክት ቢሆን እኛ የተያያዝነው ህገመንግሥታዊ መብታችንና የዜግነት ክብራችንን የማስከበር ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በመሆኑ ማስፈራሪያውም ሆነ ማስጠንቀቂያው ህገመንግሥታዊ አይደለምና ህገወጥ ነው አይመለከተንም፤በሚል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በመጨረሻም ለተያያዝነው ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል፡-
1ኛ/ የጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በሠላማዊ ትግል አስገድደን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ራሱን እንዲያዘጋጅ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማቅረብ ከጎናችን እንድትቆሙ፣ በተለይ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ትብብሩ ለትግሉ ተገቢውን አቅም እንዲገነባ በጀቱን ለመሸፈን ወቅታዊ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታደርጉ፤
2ኛ/ በአገራችን የሚደረጉ ምርጫዎች ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑና ከማንኛውም ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ ለማስፈጸም በህገ መንግሥቱ ሥልጣኑ የተሠጣችሁ፣ ኃላፊነቱ የተጣለባችሁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚ ባለሥልጣናት ከገዢው ፓርቲ ወገኝተኝነት እንድትላቀቁና እንደ ተቋሙ መሪና ዜጋ ራሳችሁን ከትውልድ ባለዕዳነትና ከታሪክ ተጠያቂነትና ተወቃሽነት ነጻ እንድታወጡ፤
3ኛ/ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም የመግባቢ ሰነዱና የጥናቱ ሪፖርት ባለቤቶች የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚጠይቀውና የተያያዝነው ትግል ከፓርቲ መሪዎች የግል ፍላጎትና ከፓርቲ ጥቅም በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ለአገርና ህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ተቃዋሚ ጎራው ባለፉት ምርጫዎች ሁሉ በመከፋፈልና የህዝብን ድምጽ በመበታተን ሚናው ከምርጫ አጃቢነት ያላለፈ በመሆኑ ይህን ‹‹በቃ›› የማለት ወቅቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ስለሆነ ከ‹‹እናቴ መቀነት ጠለፈኝ›› ምክንያት ወጥታችሁ ለዚህ ዓላማ በጋራ ለመቆም ትብብሩን ያለቅድመ ሁኔታ እንዲቀላቀሉ፤
4ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት ከተያያዘው በአፈና ‹‹ለብቻ በመሮጥ›› አሸናፊ ነኝ በሚል ሥላጣን የማስጠበቅ ኢህገመንግሥታዊ አካሄድ ታርሞ የአገርና ህዝብ ጉዳይ ከሥልጣን ማስጠበቅ በላይና የኃይል እርምጃና አፈና ሥልጣን የማራዘም እንጂ የህዝብን የለውጥ ፍላጎትም ሆነ ለውጥን የማስቀረት አቅምና ኃይል የሌለው መሆኑን ከዓለም ታሪክና ከቅርብ ጊዜ የጎረቤት አገሮች ተሞክሮ እንዲማርና ራሱን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያዘጋጅ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ያለመስዋዕትነት ድል የለም፤ የጋራ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ታህሳስ 17/2007 ዓ.ም! አበባ!

በ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሠጠ መግለጫ፤

4.
አስተባባሪ ኮሚቴው ተግባራቱን በጊዜ ሠለዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት አጽድቋል፡፡

እዚህ ላይ ይህን ዕቅድ ስናወጣ መንግሥት/ጠቅላይ ሚ/ሩ/ ከቅርብ ቀን በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥትን መገዳደር አይችሉም›› የሚል ኃሳብ ያዘለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ማድመጣችንን፤ይህ መልዕክት የማደናገሪያና ማደናበሪያ ፕሮፖጋንዳ ስልትም ይሁን የተቃዋሚዎችን ዓላማና የመኖር ትርጉም የመጨፍለቅ ግልጽ መልዕክት ቢሆን እኛ የተያያዝነው ህገመንግሥታዊ መብታችንና የዜግነት ክብራችንን የማስከበር ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በመሆኑ ማስፈራሪያውም ሆነ ማስጠንቀቂያው ህገመንግሥታዊ አይደለምና ህገወጥ ነው አይመለከተንም፤በሚል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

በመጨረሻም ለተያያዝነው ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል፡-
1ኛ/ የጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በሠላማዊ ትግል አስገድደን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ራሱን እንዲያዘጋጅ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማቅረብ ከጎናችን እንድትቆሙ፣ በተለይ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ትብብሩ ለትግሉ ተገቢውን አቅም እንዲገነባ በጀቱን ለመሸፈን ወቅታዊ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታደርጉ፤
2ኛ/ በአገራችን የሚደረጉ ምርጫዎች ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑና ከማንኛውም ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ ለማስፈጸም በህገ መንግሥቱ ሥልጣኑ የተሠጣችሁ፣ ኃላፊነቱ የተጣለባችሁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚ ባለሥልጣናት ከገዢው ፓርቲ ወገኝተኝነት እንድትላቀቁና እንደ ተቋሙ መሪና ዜጋ ራሳችሁን ከትውልድ ባለዕዳነትና ከታሪክ ተጠያቂነትና ተወቃሽነት ነጻ እንድታወጡ፤
3ኛ/ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም የመግባቢ ሰነዱና የጥናቱ ሪፖርት ባለቤቶች የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚጠይቀውና የተያያዝነው ትግል ከፓርቲ መሪዎች የግል ፍላጎትና ከፓርቲ ጥቅም በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ለአገርና ህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ተቃዋሚ ጎራው ባለፉት ምርጫዎች ሁሉ በመከፋፈልና የህዝብን ድምጽ በመበታተን ሚናው ከምርጫ አጃቢነት ያላለፈ በመሆኑ ይህን ‹‹በቃ›› የማለት ወቅቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ስለሆነ ከ‹‹እናቴ መቀነት ጠለፈኝ›› ምክንያት ወጥታችሁ ለዚህ ዓላማ በጋራ ለመቆም ትብብሩን ያለቅድመ ሁኔታ እንዲቀላቀሉ፤
4ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት ከተያያዘው በአፈና ‹‹ለብቻ በመሮጥ›› አሸናፊ ነኝ በሚል ሥላጣን የማስጠበቅ ኢህገመንግሥታዊ አካሄድ ታርሞ የአገርና ህዝብ ጉዳይ ከሥልጣን ማስጠበቅ በላይና የኃይል እርምጃና አፈና ሥልጣን የማራዘም እንጂ የህዝብን የለውጥ ፍላጎትም ሆነ ለውጥን የማስቀረት አቅምና ኃይል የሌለው መሆኑን ከዓለም ታሪክና ከቅርብ ጊዜ የጎረቤት አገሮች ተሞክሮ እንዲማርና ራሱን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያዘጋጅ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ያለመስዋዕትነት ድል የለም፤ የጋራ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ታህሳስ 17/2007 ዓ.ም! አበባ!

Filed in: Amharic