>
5:13 pm - Sunday April 19, 6167

ለሕዝቡም ለወንበሩም ክብር ጠፋ!  (ሙሉአለም ገብረመድህን)

ለሕዝቡም ለወንበሩም ክብር ጠፋ! 

ሙሉአለም ገብረመድህን

በቤተልሄም ጌታቸው ግጥም ወደ ጽሁፌ ልንደርደር?!?
…..የእግዜር ወምበር…
ሁሉም የሚመኙት
ጥቂቶች ያገኙት
በደም የጨቀየ
ፍርዱ የዘገየ
አጥንት ያረገፈ
እጣው ያልተጻፈ
ምን ቢጠበብበት የሰው ልጅ በልኩ
ምን ዙፋን ቢቀየር አልተዋበም መልኩ
 
     ለምኑ ውዶቼ
ከሚመኙት ይልቅ ስጦታው ይልቃል
በእጆቹ የሰራው የእግዜር ወምበር የታል?
                  
በአፍሪቃ ታሪክ በጉልህ የሚጠቀሰው ገናናው የጎንደር መንግሥት በሠርፀ ድንግል በ1553 ዓ.ም. ተጀምሮ በታሪክ ገጽ “ተፍጻሚተ-መንግሥት” በመባል በሚታወቁት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ በ1775 ዓ.ም. አበቃ። የከፍታው ዘመን ቁልቁል መወርወር ጀመረ።
ራስ ሚካኤል ሥሁል ነበር ዘመነ መሳፍንት ያስጀመረው። ዳግማዊ አፄ ኢዮአስን በሻሽ አሳንቆ የዘመነ መሳፍንትን በር ከፈተው። በስድስት ወራት ውስጥ ሁለት ንጉሥ ገደለ። ቀጥሎም ራስሚካኤል አማቹን (የሴት ልጁን ባል) ዳግማዊ አፄ ዮሐንስን በዳግማዊ አፄ ተክለሃይማኖት ተካው። ሌሎች በጉልበታቸው አፄውን ከሥልጣን አስወረዱት። ራስ ሚካኤል ግን የዋዛ መሰሪ አልነበረምና ኃይል አደርጅቶ መልሶ አፄ ተክለሃይማኖትን አነገሰ።
ከዛም ቆይቶ ራስ ጉግሣ ዘውዱ ላይ ተሰየመ። የእርሱ ዘመን ሲያልፍ ሌላው ተተካ። እያለ እያለ ራስ ማርዬ በሩ ላይ ለንግሥና ተረኛ ልሁን አለ። ራስ ማርዬ ራስ ዶሪ የሚባል ወንድም ነበረው።  በታሪክ ሁለቱ የሚታወቁት ጎንደር ቁጭ ብለው እርስ በእርሳቸው «አንዳችን እንንገስ እንዴ?» ተባብለው እንደተነጋገሩ ይነገራል። በመጨረሻም ሁለቱ እርስ በርስ ተጠያየቁ «ግን ንግሥናውን ማን ሰጠን እንላለን?» ብለው ሐሳቡን እንደተውት ይነገራል።
እዚህ ላይ አንድ ልብ ሊባል የሚገባው እውነት አለ። የኢትዮጵያ የዘውድ ገዥዎች፣ በአስተዳደር የአያያዝ ጉድለቶች ቢኖሩባቸውም ለዘውዱ ክብር ይሰጡ ነበር።  በዘመነ መሳፍንት ጊዜ መሳፍንቱ እንደልባቸው ቢሆኑም ዘውዱን ያከብሩት ነበር። ሕዝብ ፊት ዘውድ ጭኖ ለመቆም ቢያንስ የሚሰጡት ምክንያት  ይፈልጉ ነበር።
«ንግሥናውን ማን ሰጠን እንላለን?» የሚለው የመሳፍንቱ ጥያቄ ለዘውዱ ካላቸው ክብር ጋር ይያያዛል።
~
ዛሬ ኢትዮጵያ በግዛት ቅርፆም በአስተዳደራዊ ትርክትም ተቀይራለች። ያው የተቃርኖ ሕግ ነውና ተቀበለው! ግን ግን ዛሬም ድረስ ኃይል ያላቸው ዜጎች- (Empowered Citizens) የሚኖሩባት ሀገር አለመገንባታችን ብቻ አይደለም የሚገርመኝ፤ እኔን በይበልጥ የሚገርመኝ  ዛሬ ለተቀመጡበት ወንበር እንኳ ክብር የሌላቸው፣ ሕዝብን የዕዳ መያዥያ ያደረጉ የደም ግብር የለመዱ መሪዎች በየቦታው መሰየማቸው ነው።
ስለ ዘውዱ ክብር “ንግሥናውን ማን ሰጠን እንላለን?”  ብሎ  መጠየቅ ቢቀር፤ የሕዝብ ትግልን ጠልፎ የተገኘን ወንበር ሀገር ከምትፈርስ Benevolent dictatorship መሆን እንዴት ያቅታል? አሁንኮ ለወንበሩም ለሕዝቡም ነው ክብር የጠፋው!!
የዘውዱን ትውፊት አያውቁትም እንዳይባል ያኔ ቅድመና በሂደታዊ ዘመነ መሳፍንት ጊዜ ቤተ-መንግሥቱ ውስጥ  ነበሩ። ነው ወይስ ሰኝ ሞቲ bravado ነው?
‘ስቴት’ አልገባንም ወይ አልገባቸውም!!
የሆነ የተጋጨ  ባህልማ አለ!!
Filed in: Amharic