>

ወለጋ በኦሮሞ ከመወረሩ በፊት የአማራ አጽመ ርስት ነበር፤ ዛሬ ግን አማራው "አገርህ አይደለም!" ተብሎ  እንደ ደገዛ ይጨፈጨፍበታል!!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ወለጋ በኦሮሞ ከመወረሩ በፊት የአማራ አጽመ ርስት ነበር፤ ዛሬ ግን አማራው “አገርህ አይደለም!” ተብሎ  እንደ ደገዛ ይጨፈጨፍበታል!!!!

አቻምየለህ ታምሩ

በኦሮሞ ከተወረረ በኋላ ስሙ ወደ ወለጋ የተቀየረው የጥንቱ የኢትዮጵያ ክፍል የሆነው ቢዛሞ ክፍለ ሀገር በኦሮሞ ከመወረሩ በፊት ባለቤቶች እነ ማን እንደነበሩ ካጠኑ “የታሪክ ጸሐፊዎች” መካከል ግንባር ቀደምቶቹ የኦሮሞ ብሔርተኞች ናቸው። አቶ ይልማ ደሬሳ፣ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ፕሮፈሰር ተሰማ ተዓ፣ ፕሮፈሰር ሕዝቅኤል ጊቢሳ፣ ወዘተ… ኦሮሞ ወለጋን ከመውረሩ በፊት የቢዛሞ ባለርስት ሆነው ይኖሩ ስለነበሩ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገዶች ማንነት ከጻፉት የኦሮሞ ብሔርተኞች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
የወለጋው ንጉሥ የሞቲ በከሬ ጎዳና 4ኛ ትውልድ የሆኑት የብላታ ደሬሳ አመንቴ በከሬ ልጅ እና የሞቲ ሞሮዳ በኬሬ የወንድም የልጅ ልጅ የሆኑት አቶ ይልማ ደሬሳ በ1959 ዓ.ም. “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን” በሚል ርዕስ ባሳተሙት የታሪክ መጽሐፍ ገጽ 17 ላይ የዛሬው ወለጋ በኦሮሞ ከመወረሩ በፊት ስሙ ማን ይባል እንደነበርና ባለ ርስቶቹም እነ ማን እንደነበሩ እንደሚከተለው ጽፈዋል፤
“ከአዋሽና ከጊቢ ወንዞች መካከል የሚገኘው አገር በጠቅላላው የዳሞት ግዛት ይባል ነበር። በዚሁ ክፍለ ሀገር በዐባይ ወንዝ በስተደቡብ ዛሬ ሆሮ ጉዱሩና ጂማ ራሬ በሚባሉት ወረዳዎች እስከ ጨሊያ ድረስ የጋፋት ወገን የሆኑ ጎሳዎች ይኖሩበት ነበር። ከጋፋቶቹ በስተደቡብ እስከ ጊቤ ወንዝ ድረስ በግዛቱ ላይ የሰፈሩት እናርያ ወይም ዲና የሚባሉ ጎሳዎች ነበሩ። ከ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የመጫ ጎሳ የሆኑት ጋ*ች አዋሽን ተሻግረው ከወንዙ በስተ ምዕራብ ያለውን አገር በወረራ እስከ ያዙበት ጊዜ ድረስ የእናርያ ጎሳ የሠፈረበት አገር ከጋፋቶች ጋር ይዋሰን ነበር።
ከዳሞት ግዛት በስተ ምዕራብ ዛሬ የወለጋ ጠቅላይ ግዛት የሆነው አገር የቢዛሞ አውራጃ ይባል ነበር። ይህንም አውራጃ በ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን የመጫ ጎሳ የሆኑ ጋ*ች ገብተው እስከ ያዙበት ጊዜ ድረስ ባገሩ ላይ ይኖርበት የነበረው ሕዝብ የዲና ጎሳ የተባለው የእናርያ ነገድ ነበር።”
ይህ የአቶ ይልማ ደሬሳ ጥናት የሚያሳየው የዛሬው ወለጋ በኦሮሞ ከመወረሩና ስሙ ከቢዛሞ ወደ ወለጋ ከመቀየሩ በፊት ይኖሩበት የነበሩ የክፍለ ሀገሩ ባለቤቶች የጋፋት አማራ ሰዎችና የእያርያ ነገድ አባላት እንደነበሩ ነው።
በአቶ ይልማ ጥናት የእናርያ ነገድ የተባሉት እነማን እንደሆኑና ዝርያቸው ከየት እንደሆን ለማወቅ ታዋቂው የኦሮሞ ታሪክ አጥኚ ጀርመናዊው ፕሮፈሰር በርካምበር እ.ኤ.አ. በ1973 ዓ.ም. “The correlation of Oral Tradition and Historical Records in Southern Ethiopia” በሚል የጻፈውንና በጆርናል ኦፍ ኢትዮጵያን ስተዲስ ያሳተመውን ጥናት መመልከት ይቻላል። ፕሮፈሰር በርካምበር በዚህ ጥናቱ ገጽ 17 ላይ ስለ እናርያ ሰዎች ማንነት እንዲህ ሲል ጽፏል፤
“The Ennariya, a Semitic-speaking element from Hate Amhara cluster, are said to have inhabited the area [between the Omo and the upper Bilate rivers] before the establishing of the Kambata tribes disappeared from there without leaving remarkable traces.”
ይህ የፕሮፈሰር በርካምበር ጥናት የእናርያ ሰዎች የሴሜቲክ ቋንቋ ተናገሪ የሆኑ “የአቴ አማራ” ክላስተር መሆናቸውን ይነግረናል። አቶ ምስጋናው በላቸው የጨቦ ሕዝብ የጉራጌ ሕዝብ መሆኑን በገለጡበት “የጨቦ ኡዳደ የሱስ ሕዝብ አጭር ታሪክና ባሕል” መጽሐፋቸው ገጽ 50 ላይ ፕሮፈሰር በርካምበር “Hate Amhara” ሲል የጠራቸውን ሰዎች “አፍቴ አማራ” በመባል የሚታወቁትን ሰዎች ነው።
እንግዲህ! ፕሮፈሰር በርካምበር የእናርያ ነገድ የሴሜቲክ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ የአማራ ሰዎች ናቸው ያሉትን ወስደን አቶ ይልማ ዴሬሳ ኦሮሞ ወለጋን ከመውረሩ በፊት ይኖሩ የነበሩትን ጥንታዊ ዜጎች የእናርያ ነገድ የሆኑ ሰዎች ያሉትን ስናጤን ከኦሮሞ ወረራ በፊት ቢዛሞ በነበረውና ከወረራው በኋላ ወለጋ ተብሎ ስሙ ወደተቀየረው ምድር ኦሮሞ በወራሪነት ከመግባቱ በፊት አገሩ የአማራ አጽመ ርስት እንደነበር ከሁለቱ የታሪክ ምንጮች መገንዘብ እንችላለን።
ከአቶ ይልማ ደሬሳ ቀጥሎ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ወለጋ የአማራ አጽመ ርስት እንደነበር በዶክትሬት ጥናታቸው ካሳወቁን የኦሮሞ ብሔርተኞች መካከል ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ  ተከታዩ ናቸው። የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም. በጀርመን አገር በፍራንክፈርት ከተማ ለሚገኘው ዮኸሃን ዎልፍጋንግ ዩኒቨርሲቲ “History of the Sayyoo Oromoo of Southwestern Wallaga, Ethiopia: From about 1730 to 1886” በሚል ርዕስ ባቀረቡት የዶክትሬት ጥናታቸው ገጽ 76 ላይ ኦሮሞ ወለጋን ከመውረሩ በፊት አማራ ወለጋ ውስጥ ይኖር የነበረ ነባር ነገድ እንደሆነ ለጀርመኖቹ ባቀረቡት በዚሁ የዶክትሬት ማሟያ ጥናታቸው  ውስጥ “Pre-Oromoo Peoples of Wallaga” የሚል ርዕስ በሰጡት ሶስተኛው ምዕራፋቸው ላይ አረጋግጠዋል።
ከኦሮሞ ወረራ በፊት ወለጋ አጽመ ርስቱ የነበረው አማራ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ በኦሮሞ አባገዳዎች ገርባ ተደርጎና መሬቱን በጉልበት ተቀምቶ በኦሮሞ እንዲዋጥ ከተደረገ በኋላ በስሙ  ላይ ቅጥያ ተጨምሮለት ዛሬ ላይ መጠሪያው “አማራ ካንቺ” ሆኖ አሁንም ድረስ በአማራ ጎሳነት እየታወቀ እዚያው ወለጋ ውስጥ ከአንፊሎ በስተሰሜን ምስራቅ እንዲሁም ከገላና ሐለኩ በስተሰሜን በሚገኝ አካባቢ ብቻ ተወስኖ እንደሚኖር ዶክተር ነጋሶ ከዛሬ 37 ዓመታት በፊት ባቀረቡት የዶክትሬት ጥናታቸው ጨምረው ነግረውናል።
ይቀጥላል…
Filed in: Amharic