>

በኢትዮጵያ ታሪክ ራሱን የደገመው የምዕራባውያን ቸልታ....!!!"   (አምባሳደር ሳሚያ,  በአል-ጄዚራ)

በኢትዮጵያ ታሪክ ራሱን የደገመው የምዕራባውያን ቸልታ….!!!”

 አምባሳደር ሳሚያ,  በአል-ጄዚራ

* …. “በማይካድራ ከ 600 በላይ አማራ ሲገደል ለምን አልጮኹም!!!,
አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በኳታር የኢትዮጵያ ኢምባሲ ይሰራሉ። አንጋፋዋ ዲፕሎማት በዛሬው ዕለት ከፍ ያለ አርቲክል በአልጄዚራ OPINION ላይ ተነባቢ አድርገዋል። አለማቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያን ጉዳይ ያሳየው ቀሰስተኛ አጋርነት መርሆችን ያላከበረ መሆኑን በገለፁበት ፅሑፋቸው
“የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በወያኔ ሃይሎች የተፈጸመበት የጭካኔ በአጭሩ የጦርነት አዋጅ ነበር” ብለዋል። “የአንድ ሉዓላዊ አገር የመከላከያ ኃይል የሕገ-መንግሥትና የሁሉም ህዝብ የመጨረሻው ዋስትና ሰጪ ነው። ስለዚህም ነው መሰል ጥቃቶችን ሁሉም አገራት ችላ ሊለው የማይችለው” ሲሉም አስገንዝበዋል።
ፎሬይን ፖሊሲ መጽሔት ባወጣው ዘገባ የ UNDP ሀላፊ አቺም ስቴይነር ለተመድ ዋና ጸሐፊ ያሰፈሩት “የህወሃት ጥቃት የትኛውም የዓለማችን ክፍል ቢሆን የጦርነት እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የማንኛውንም አገር መከላከያም ወታደራዊ ምላሽ እንዲሰጥ ያስገድደዋል” ብለው አስፍረዋል። ይሁንና ይህን ከፍተኛ ወንጀል ህወሃት በኢትዮጵያ ሲፈፀመው ተገቢ ትኩረት ሲሰጠው  አልተስተዋለም”
“የአለማቀፉ ማህበረሰብ ቸልታ ከ 86 ዓመታት በኋላ ታሪክ  ራሱን የደገመ ያስመስላል” ያሉት አምባሳደሯ 1935 መገባደጃ ላይ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ የኬሚካል ጋዝ ተጠቅሞ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ ወንዞችና የግጦሽ መሬቶች መርዛማ ዝናብ እንዲጋቱ ሲያደርግ ንጉስ ሃዬለ ስላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን ከዓለም መሪዎች ፊት አቤቱታቸውን ቢገልፁም ለይግባኙ ምላሽ አለመኖሩ ከአሁኑ የአለማቀፉ ማህበረሰብ አኳኋን ጋር ይመሳሰላል ብለዋል።
“የሱዳን ወታደሮች በኖቬምበር 2020 የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ሲጥሱ እንዲሁም በማይካድራ 600 በላይ የአማራ ተወላጆች ህይወት በህወሃት በተቀነባበረ ወንጀል ለእልቂት ሲዳረጉ  ሆኖም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቸልታ አልፎታል። ወንጀሉን ደፍረው ያወገዙት ጥቂቶች ናቸው” ያሉት አምባሳደሯ “አሁን አሁን በዓለም አቀፍ ተቋማት በተለይም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም.ቤት (UNSC) የአንድ ወገን ጥያቄን ማስተናገድ ቀላል እየሆነ የመጣ ይመስላል” ሲል አስምረውበታል።
     *                           *                            *
  ° የሚዲያ ዘመቻ ጉልበትና የዲፕሎማቶቻችን ሚና
አልጄዚራ ስለ ኢትዮጵያ አሉታዊ ዘገባ ለምን ይሰራል? የሚሉ ዜጎች ብዙ ናቸው። አገራዊ መቆርቆሩን ብቀበለውም አልጄዚራ የፈጠረውን እድል መጠቀም ከቻልን በሩ ክፍት የሆነ አሰራር ነው ያለው። ከኳታር የውጭ ፖሊሲ አንፃርም አልጄዚራ ፀረ ኢትዮጵያ የሚሆንበት የፖሊሲ ግዳጅ የለም ባይ ነኝ። መፍትሄው በአልጄዚራ መፃፍና መናገር ነው።
ከጅማሮው አንስቶ አልጀዚራ የምዕራቡ አለም አጀንዳ ላይ የተንጠለጠሉት CNN እና BBC ተወት የሚያደርጓቸውን ጉዳዮች በተተኳሪነት በማስተጋባት የአንድ ወገን የመረጃ ፍሰት ታሪክን አስቀርቷል የሚሉት በርካቶች ናቸው። ሽፋን ከተነፈጉ ሀገሮች የሚገኙ የታፈኑ ድምፆችን የዜና ዘገባዎችን በመዘገብ ላይ አተኩሯል። ዊሊያም ላፊ እና ዮማንስ ሲኢብ እንዳሉት የአልጀዚራ ውጤት በመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካና በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡  እያሳደረም ይገኛል” ነው ያሉት።
  ከአልጄዚራ የእንግሊዝኛው ዌብሳይት ተጠቃሚዎች ውስጥ 50 በመቶው ከአሜሪካ ናቸው። Fox news እና CNN በዘመናት የፈጠሩት 100 ሚሊዮን የቴቪ ተመልካቾችን አሃዝ አልጄዚራ በተመሰረተበት አመት ግማሹን ማሳካት ችሏል።
ድሮ ድሮ የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ በ CNN ጫና ስር መሆኑ “The CNN effect” የሚባል የልሂቃን ዘይቤ የተለመደ ነበር። አሁን ደግሞ “the AlJazeera Effect ”  እየተባለ ነው ያለው። የምዕራባዊያን የጂኦፖለቲካ ተቋማት በዚሁ ዙሪያ ከሰሯቸው ጥናቶች ጥቂቱን ብናወሳ “AlJazeera America’s biggest challenge:”  እና “AlJazeera: The Most-Feared News Network” የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል። ጥናቶቹ የአልጄዚራን ጉልበት ከኑክሌር ባለቤትነት ጋር ይመስሉታል። አትላንቲክ ካውንስል ፎሬን ፖሊሲ መፅሔት ፒው ሪሰርች ካውንስል ፎር ፎሬን ሪሌሽን ሎዊ ኢንስቲትዩት ወዘተ…ስለ ጣቢያው ተፅዕኖ ብዙ ብዙ ብለውለታል። የአሜሪካው የስለላ ተቋም CIA ‘አል-ጄዚራ ስለላ ፈፅሞብኛል፣ መረጃዎች በተደጋጋሚ ወስዶብኛል’ ሲል በአንድ ወቅት የመሰረተውን ክስ ስናስታውስ የጣቢያው ጉልበት እስከ ምን እንደሚደርስ ይገልጥልናል።
እናም፦ አል ጄዚራ የፈጠረውን ሜዳ አሟጠን እንጠቀምበት፣ ሳዑዲ ከአልጄዚራ በላይ ገንዘብ አውጥታ በከፈተቻቸው መሰል ቴሌቪዥኖች ለመመከት ሞክራለች። ይሁን እንጂ የጣቢያውን ስም እንኳ ታዋቂ ማድረግ እንኳ እንደከበዳት ትገኛለች። በዋናነት አልጄዚራን ጉልበተኛ ያደረገው ምን ይመስልሃል?  ጄዚራ እንደ ሳዑዲው ጣቢያ በጀለብያ የተጀቦኑ የኳታር ነገስታት መናኸሪያ አይደለም፣ የተቀረፀለትን አጀንዳ በአሳማኝ ምርምር ደግፍ ካልሆነ አያቀርብም፣ አብላጫ ዘገባው የታዳሚዎቹ ጉዳይ ሲሆን በዚህ መሃል የተመረጡ አጀንዳዎቹን ጣል ያደርጋል። አልጄዚራን አለማየት ከባድ የሚያደርጉ ምክንያቶች በርካታ ናቸው …ታዲያ ጣቢያ ለኛ ለኢትዮጵያ ሲል ይህን እሴቱን አይጥስልንም። ለኛ የሚበጀው በሜዳው መገኘት ነው።  በዛ ላይ እውነትም አለን። ውጋት ለሆኑብን ምዕራባዊያን ማርከሻ የሆነባቸውን የሚዲያ ተቋም  ብንጠቀምበት አትራፊ  እንሆናለን!

 

Filed in: Amharic