>

በዕውነተኛ ታሪክ ሠይጣን እና ሥልጣን       ሰላቢዎች ናቸው፤ከልብ ዕወቛቸው። (ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

በዕውነተኛ ታሪክ ሠይጣን እና ሥልጣን 
ሰላቢዎች ናቸው፤ከልብ ዕወቛቸው።
  ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

       ወደ ፈተና:- “ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።”ሉቃስ ም፬ቁ፯     
                                    ብልህ ፈረስ ያደርሳል እንጂ፣አይዋጋም። 
    ጠ/ምኒስቴሮች ዛሬም ድረስ የሚንቀለቀሉት  ለወቸገሉ  እንዲመቸው በቀደደላቸው የተንኮል መንገድ እየተግተለተሉ የሚጓዙ ስለሆነ እንጂ በዕውነት ፕሬዝርዳንቶች እጃቸውን አጣጥፈው የሚያስቀምጣቸው ኀላፊነት አይደለምወቸገል ዜናዊ ከዓባይ  ግድብ ግንባታ አስራ ኣራት ብሊዮን ብሩን እንደሰለቀጠው ከባለሙያዎች ሰማን።የቦንድ ዝርክርክ መዋጮም የተፈለገበት ሰበብ እና ምክን ያቱም ይሄንኑ ግርግር ለመፍጠር እንደነበረ ባለሙያዎቹ፣እኔን ጨምሮ በወቅቱ ሌባዎቹን ተቃውመን እንደነበረ በታሪክ ተመዝግቧል ።በተጻራሪው በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ያሉን ጠቅላይ ምኒስቴር  ሌብነትን የሚጸየፉ ኢትዮጵያዊነትን በልባቸው ፅላት ባደባባይ የሚጽፉ ናቸው፤ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን ሐቁ ይኼ ሆኖ ሳለ ዐቢይ ያስመስላል ይላሉ፣መስሎን ነበር።ዐይናችንን አናምነውም የሚሉት ምሁራን ፋሺስት ወያኔን ጨምሮ በየጢሻው ከነብረታቸው የቀሩት ፋሺሽቶች ፎቶ ኮፒ ናቸው ማነው የሚላቸው?…?….?      
  አዲስ የታሪክ ግልቢያ ከጀመርን ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፤ለዘመናት ያልነበረ እና ለመጀመሪያ ጊዜ   ስንት ጀግኖች ለሞቱለት ዲሞክራሲ እና ለሚገነባው ስርዓት ምስረታ እየተጣደፍን እንገኛለን፤ግንባር ቀደሙና አቅጣቻዎችን መሪ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነው።ሁሉም አለኝ በሚለው የሕሊና ፈረሱ እንደየ ችሎታው እና አቅሙ እንደፈቀደ፤የሽምጥም ሆነ የሶምሶማ አሊያም የወደደውን ዓይነት መርጦ   ግልቢያ ይጋልባል።                                                         
            እናም የዶ/ር ዐቢይ አህመድን የፈረስ ሥም የሚያውቅ ሰው የለም፤አስታውሳለሁ ይሁንልኝ ብሎ በስጦታ ፈረሶችን ከሕዝብ ሲበረከትለት ደጋግሜ በቴሌቪዥን መስኮት አይቻለሁ።እስኪ ከታሪክ ማሕደር የማን የፈረስ ሥም ምን ይባል እንደነበር እናስታውስ።
አፄ ቴዎድሮስ ን.ነ. ዘኢትዮጵያ ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣
ደጃዝማች ካሳ ምርጫ (አባ በዝብዝ)(ዮሐንስ ፬ኛ) 
ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ ን.ነ.ዘኢትዮጵያ(አባ ዳኘው)
ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ 
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ አባ ጠቅል 
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ኣባ ንዳው ቢባልስ
ፕሬዚደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አባ ነገታ ቢባልስ
ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ኣባ ቱርብ ቢባልስ
ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ ኣባ ቢሻን ቢባልስ
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሁንም ድረስ በስልጣናቸው ያሉ ናቸውይጠብቁን ይሰየምላቸዋል፤ “ቅመም”ቢባል አስተያየቴ ይያዝልኝ
       ያንን ዘመነ መሳፍንት በዘመናዊ መልክ ለማምጣት የሚቋምጡት ብዙዎች ናቸውከዕውነተኛ ታሪክ ሠይጣን እና ሥልጣንን ሰላቢዎች መሆናቸውን፤ከልብ አያውቛቸውእነዚህ ጎምዢዎች ደግሞ መሠረታዊ ፍላጎታቸው ሥልጣን ነውና መቼም ጊዜ ቢሆን ያቺን ዙፋን ባዶ መሆኗን ያየ የማይጎ ዥላት ሰው የለምየፈለገውን ያህል የሰው ደም ይፍሰስ ስልጣንን የሚፈልጓት እርሷን ለማግኘት ሕይወት አስገብረውም ቢሆን በክንዳቸው ስር ሊያደርት ሌት ተቀን ያልማሉ፤ለምን ቢባል የሕዝብ የሚያደርጋት ህግ የለምና ነው
ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ብቻ  የነበሩትን የዙፋን ተዋረድ ስንመለከት በሕዝብ ሥም የተፈጸሙት  የስልጣን ውንብድናዎች እንደሆኑ፤ቁልጭ እንደጡት ዐይን የጎረጡፍንትው እንደአረም የተለዩ ሆነው እናገኛቸዋለን።ስልጣን ዙፋኗንን የሕዝብ የሚያደርገው አንድ ዘዴ ብቻ ነው፤በሕግ የወጣ የሕዝብ ሥልጣን ብቻ የሚያዛት አንዲት አንቀጽ ያለው በሕዝብ የተረቀቀ ሕግ ማፅደቅ ብቻ ነው።
“ሕገ መንግሥት”በፍጹም አይደለም፤ስሙ እንኳን ይናገራል፣የመንግስት ሕግ ማለት ነው፣የሕዝብ ሕግ አይደለም።ይህ አባባል በቀትተኛ ትርጉሙ ብቻ ሳይሆን፣ሳይንሳዊ አተናተኑ የሚያሻማ ሆኖ አናገኘውም፤መንግሥት ተቀጣሪ የሆኑ ሹመኞች ነን ብለው የሚያምኑትን ሰዎች የያዘ መሆን አለበት። እናም ከስያሜው ጀምሮ ለሕዝባዊነት ስልጣን መፍት ሄ ሳይሆን ችግር ፈጣሪ ነው።
ስለዚህም መፍት ሄው ሕገ መንግስት አለመሆኑን ከተረዳን፣ሌላ ጥቅም ፍለጋ ፊታችንን ካላዞርን ሕገ- ሕዝብ ብቻ ያለአማራጭ መፍትሄ ይሆናል።እንዴት ብትሉኝ መንግሥትን ቀጣሪ ምንጊዜም ሕዝብን ስለሚያደርግ ነው።መንግስት ደግሞ ምንጊዜም ተቀጣሪ መሆን አለበት፤የሚያሳዝነው ግን በተግባር ላይ ቆላፋ እና አቋራጭ የተገላቢጦሽ አፈጻጸም ይፈጠርና፣መንግስት ሕዝብን በቀጥታ እንደቀጣሪ  ማዘዝ ይጀምራል፤ የ”ዙፋኑን”ም ህልውና ሕዝብ መቆጣጠሩ ቀርቶ ይሸረሸራል።የኢትዮጵያ  ሕዝብ   በሕገ-ሕዝብ እስካልተመራ ድረስየሚያቁለጭልጨውን”ዙፋን”ለማግኘት መጀመሪያ ሠይጣን በስውር ይቀመጥበታልና ሥልጣን በርኩስ መንፈስ እንዳይረክስ መባረክ እና መቀደስ ይገባዋል፤ቃለ መሐላው የሚፈጸመውም ከዚያ በኋላ ሊሆን ይገባዋል።
የሚሾሙት ደግሞ እንዳሻቸው የፈለጉትን ዓይነት የፈረስ ሥም እንዲወጣላቸው አያስደረጉ በመረጡት ግልቢያ ችሎታቸውን ማስመስከር ብቻ ነው፤ታሪክ ይመዘግበዋል።
 “ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?”
ሮሜ ፱፥፳፩
 
 
በኢኮኖሚ ግንባታ ዘረኛው ፋሺስት 
በዶላር በብር ቢሸሸግም፤ 
በግድብ ተስፋ ለመኖር 
የሕዝቡን ሥልጣን ቢፈልግም፤ 
ዘረኝነትን የሚዋጋ 
ኢትዮጵያዊነትን የሚያነግስ፤ 
ቆየ’ኮ ከተፈጠረ 
ግልገል ወያኔን የሚያረክስ። 
ልባቸው ባልተቸነፈ 
ሕሊናቸውን ባልሸጡ፤ 
ኢትዮጵያዊነትን አንግበው 
ነፃነትን በሚያምጡ። 
እየደሙ እየሞቱ 
በትግል አሳት እየፋሙ፤ 
ባልታሰበ አቅጣጫ 
ከጉጅሌው በሚቀድሙ። 
እሳት ባሕርን ሊያሻግሩን፤ 
በልብ አፍንጫቸው አሽትተው፤ 
ግልገል ወያኔን አር አብልተው። 
ሥልጣናቸውን በአመፅ፣
በመራር ትግል ቀምተው፤ 
የገዳዮችን ሬሳ፤
በሞት ሸለቆ ሸኝተው። 
በትዕግስት ስንጠብቅ 
የሠላምን ጫፍ ፍቅሩን፤ 
ይቅርታቸውን ነሱን 
በዐቢይ ፍቅር አሰሩን። 
ቦጊዜ ለኩሉ እያልን 
ያሳለፍነውን መከራ፤
በጌታም እንጠብቃለን 
የጠላትን ሞት ሳንፈራ።
ይቛጠር የትግሉ ዕትብት
በዲሞክራሲ ይጠላለፍ፤
ሕዝቧም ለነፃነቱ  
ቀናዒ ትግሉ  ይለፈፍ።
Filed in: Amharic