>

"ታዬ ደንደኣ የኦሮሞው ብልፅግና ፓርቲ ስብሀት ነጋ ለመሆን የሚጋጋጥ ሰው ነው" (ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

“ታዬ ደንደኣ የኦሮሞው ብልፅግና ፓርቲ ስብሀት ነጋ ለመሆን የሚጋጋጥ ሰው ነው” –
ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

የትህነጉ የፖለቲካ ቆማሪ ስብሀት ነጋ በተለምዶ አቦይ ስብሀት የሚባለው ሰውየ ባለፉት 30 አመታት ስም ያለው የመንግስት ስልጣን ሳይኖረው ነገር ግን በየመገናኛ ብዙሀኑ ብቅ እያለ እንደልቡ በመናገር የሀገሪቱን የፖለቲካ ሙቀት እንደ ቴርሞ ሜትር ይለካ እንደነበር ይታወቃል። በዚህም ትህነግ የሚፈልገውን እርምጃ በመውሰድ ስልጣኑን ያጠናክር ነበር።
ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ሶስት አመታት ደግሞ ታየ ደንደኣ የሚባለው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓለቲከኛ ስብሀት ነጋን በመተካት ጊዜ ጠብቆ በፌስ ቡክ ገጹ በሚጽፋቸውና ባገኘው መገናኛ ብዙሀን አማካኝነት በሚገልጸው ሀሳብ አጀንዳ በመስጠት የአማራን ፖለቲካ ሙቀት ለመለካት ይጠቀሙበታል። ይህንን በመጠቀምም ይበልጥ ይዘጋጃሉ።
“የኋላዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ላይ ታሳድራለች” እንደሚባለው ስብሀት ነጋም ሆነ ታየ ደንደኣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ ሁኔታ “እብድና ዘመናይ እንደልቡ ይናገራል” እንደሚባለው ያሻቸውን እንዲገልጹ የሚያደርጋቸው በዕውቀታቸው ሳይሆን የሀገሪቱን ፖለቲካ እንደቅደም ተከተሉ እነሱ ያሉባቸው ፓርቲዎች በበላይነት የሚቆጣጠሯቸው መሆኑ የልብ ልብ ስለሰጣቸው ነው።
የታየ ደንደኣ ሰሞነኛ ዲስኩርም ከዚህ ሁኔታ የሚመጣ መሆኑን ልብ ማለት ደግ ነው። ስብሀት ነጋ አንዳንዴ ከመለስ ዜናዊ የተለየ የሚመስል ሀሳብ ያራምድ ነበር። አሁንም ታየ ደንደኣ ከዶ/ር አብይ ለየት ያለ ሀሳብ ያቀረበ ለመምሰል ይሞክራል። እውነታው ግን አንድና ያው መሆኑ ነው።
Filed in: Amharic