>
5:14 pm - Monday April 20, 4336

"ከበባው ከአዲስ አበባ የጀመረ ነው...!!!"  (ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ)

“ከበባው ከአዲስ አበባ የጀመረ ነው…!!!” 

ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ

* …. ከአዲስ አበባ ብዙም በማይርቁና በዋና መንገድ ዳር ባሉ ከተሞች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ሲከፈት የፌዴራል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር ነበር?
 
ኦነግ ሸኔ በኤፍራታ ግድም ወረዳ አጎራባች የኦሮሚያ ልየ ዞን ቀበሌዎችን ተገን በማድረግ በአጣዬ ከተማ፣ በካራ ቆሪ ከተማና በማጀቴ ከተማ ገብቶ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል፡፡
የኦነግ ሸኔ ቡድን ግን በተደራጀ መልኩ ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ጥቃት እያደረሰባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በነበረው የተኩስ ልውውጥ በአጣዬ እንዲሁም በማጀቴ በርካታ  ንፁሃን ሞትና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡
*     *    *
እዚህ አገር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ግራ ያጋባል፣
እንዴት ከአዲስ አበባ ብዙም በማይርቁና በዋና መንገድ ዳር ባሉ ከተሞች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ሲከፈት የፌዴራል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር ነበር? የሚገርመው ነገር ይኸ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ቀድሞ መረጃ የደረሰው ቢሆንም የጸጥታ ሀይል በብቃት ማሰማራት ባለመቻሉ የአካባቢው ሚሊሻ ነው እየተጋፈጠ ያለው።
ከበባው ከአዲስ አበባ የጀመረ እንደሆነ ቢታወቅም ትላንት
ምሽት 4:00 ጀምሮ የተቀናጀ ጥቃት መፈጸም የተጀመረው ግን አጣየ ከተማ እንደሆነ በስፍራው ከሚገኝ ታማኝ ሰው ከሰአታት በፊት መረጃው ደርሶኛል። ሁኔታውን ለማጣራት ስሞክር ዛሬ ደግሞ የማጥቃት እርምጃው ተስፋፍቶ ካራ ቆሬና ማጀቴ ከተሞች መድረሱ ብሎም ማጀቴ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ከበድ ያለ መሆኑን አረጋግጫለሁ።
ይህም ሆኖ የፌዴራል ፓሊስ ሁኔታውን የሚቀለብስ ሀይል ወደ ስፍራው ለመላክ የዘገየ ቢሆንም አሁንም በቂ የሰው ሀይል ባለማሰማራቱ እስካሁን ድረስ ጥቃቱን ማስቆም አልተቻለም። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የገበሬ ታጣቂዎች ባላቸው አቅም ራሳቸውንና ህዝባቸውን ለመከላከል መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ። እናም የሚመለከተው ክፍል ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል።
Filed in: Amharic