>
5:13 pm - Thursday April 20, 4333

በማይካድራ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ንጹሀን ተገድለው የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ ...!!! (ኢ ፕ ድ)

በማይካድራ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ንጹሀን ተገድለው የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ …!!!
(ኢ ፕ ድ)
• በማይካድራ የተገደሉት አየማራ ተወላጆች ቁጥርም ከ1300 እንደበለጠ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል…!!!

የማይካድራ ከተማ ከንቲባን አቶ ቸሩ ሀጎስ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አብሪሁ ፋንታሁን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ ጌቲኢሜጅስ በምስል አስደግፎ ባሰራጨው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፤ እአአ ማርች 5/2020 በአቡነ አረጋዊ ቤተክርሲቲያን የጅምላ መቃብር ውስጥ ከ13000 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።
የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት እነዚሁ ሟቾች ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች  እና በፖሊሶቹ አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ሟቾቹ በአከባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሀን መሆናቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል።
አብዛኛዎቹ ሟቾች በስለተማ መሳሪያዎች ተጨፍጭፈው የተገደሉ ሲሆን፤ በዚህ ጭካኔ ከተሞላበት ጥቃት ነፍሳቸው የተረፈችውን ደግሞ በጥይት እንደገደሏቸው ነው ዘገባው ያስታወቀው።
ሟቾቹ በወቅቱ በየመንገዱ ዳር፣ በውሃ መፈሳሻ ቦይዎች፣ በህወሓት አመራሮች በተቆፈሩ ጉድጓዶች እና በእርሻ ቦታዎች ላይ ተጥለው እንደተገኙም ገልጿል።
በማይካድራ አካባቢ አሁንም ድረስ የሟቾች አስከሬን በተለያዩ ቦታዎች እየተገኘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
Filed in: Amharic