>
5:14 pm - Saturday April 20, 4329

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብየው ገለልተኛ ነውን??? በፍጹም አይደለም!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብየው ገለልተኛ ነውን??? በፍጹም አይደለም!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

*… የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማለት “የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ ትግራይ ውስጥ በሕዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል!” እያለ ምንም ዓይነት ማጣራትና ምርመራ ሳያደርግና ሌሎች ሞያዊ ክዋኔዎችን ሳይፈጽም በመክሰስና በመወንጀል በተደጋጋሚ መግለጫ ያወጣ የነበረና የራሱን መርሕ ሊታመን በማይችል ሁኔታ በመጣስ አስቀድሞ የለየለት አድሏዊ አቋም የያዘ ተቋም ነው!!!
ጥቂት የማይባሉ ወገኖች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወያኔ “ትግራይ ውስጥ ተፈጽሟል!” ስለሚለው የጦር ወንጀል ለማጣራት አገዛዙ በመፍቀዱ ደስተኛ ሆነዋል!!!
ልብ በሉ ለማጣራትና ለመመርመር የሚገባው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማለት “የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ ትግራይ ውስጥ በሕዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል!” እያለ ምንም ዓይነት ማጣራትና ምርመራ ሳያደርግና ሌሎች ሞያዊ ክዋኔዎችን ሳይፈጽም በመክሰስና በመወንጀል በተደጋጋሚ መግለጫ ያወጣ የነበረና የራሱን መርሕ ሊታመን በማይችል ሁኔታ በመጣስ አስቀድሞ የለየለት አድሏዊ አቋም የያዘ ተቋም ነው!!!
ይሄ አድሏዊ ተቋም ታዲያ ምን እንዲል ተጠብቆ ነው “ገብቶ ማጣራቱ ጥሩ ነው!” የሚባለው???
እነ አቶ ዐቢይ አሕመድ “ሌላ ኮሚሽን መቋቋም አለበት እንጅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትማ አስቀድሞ አቋም በመያዝ ሲከስና ሲወነጅል የነበረ በመሆኑ በገለልተኝነት ሊያጣራና ሊመረምር አይችልም!” ማለት ጠፍቶት ይመስላቹሀል ይሄንን ሳይል ገብቶ እንዲያጣራ የተስማማው??? እንዳይመስላቹህ!!!
ያው እንግዲህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብየው አስቀድሞ የገዛ የገለልተኝነት መርሑን በጣሰ መልኩ ያለምንም መረጃና ማስረጃ ሲከስና ሲወነጅል የነበረ ተቋም እንደመሆኑ አስቀድሞ በመግለጫዎቹ ያሰማቸው የነበሩትን ክሶች ወያኔ ባዘጋጃቸው ሐሰተኛ ምስክሮች፣ መረጃዎችና ማስረጃዎች አጠናቅሮ የአማራን ልዩ ኃይልና ሚኒሻ የሚወነጅል ሐሰተኛ የምርመራ ውጤት እንደሚያወጣ ምንም የሚያጠራጥር አይመስለኝም!!!
ይሄንን ተቋም በዚህ አድሏዊና ኢፍትሐዊ አቋሙ ደጋግሜ ማውገዜ ይታወሳል!!! “የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል!” እንዲሉ ስፈራውና ደጋግሜ ሳስጠነቅቀው የቆየሁት ነገር ነው አሁን የደረሰው!!!
አንድ ሌላ ምን የምጠረጥረው ነገረ አለ መሰላቹህ “ለውጥ!” ብሎ ባመጣው ድራማው ፍጹም ታማኝ አህዮቹን ኦሕዴድንና ብአዴንን አስቀምጦ ሲተውንብን የቆየው ወያኔ በዚህ አማራን ለመፍጃ ሰበብ እንዲሆነው ባመጣውና ከሰሜን ዕዝ መከላከያ እስከ ሲቪሉ የማይካድራ ሕዝብ፣ ከልዩ ኃይሉ እስከ ፋኖ ድረስ ያለውን በዐሥር ሽዎች የሚቆጠር አማራ በፈጀበት የውሸት ጦርነቱ የትግራይ ልዩ ኃይልን የአማራ ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ አልብሶ እንደ ሐውዜን ሕዝብ ሞታቸውን ለፖለቲካ ቁማር መጠቀሚያነት ያዘጋጃቸውን ትግሮች በቪዲዮ እየቀረጸ ያስጨፈጨፋቸው ይመስለኛል!!!
ለነገሩ ጦርነቱ ከላይ ለገለጽኩላቹህና ለሌላም ዕኩይ ዓላማ የተደረገ የውሸት ጦርነት እንደመሆኑ ወያኔ ታጣቂዎቹን የአማራ ልዩ ኃይልን ዩኒፎርም አልብሶ ማስጨፍጨፍ ሳይጠበቅበት ለዚህ አሁን በአማራ ላይ እያነሣው ላለው ዘርፈ ብዙ ክሱ እንዲመቸው ቀደም ሲል በሕዝባዊ ትግሉ ወቅትም ሆነ ከዚያም በፊት አማራን ሲጨፈጭፍበት የነበረውም የአማራን ልዩ ኃይል በብአዴንም በኩል ይሁን ከፈለገም እራሱ በቀጥታ ለጭፍጨፋ ያዘጋጃቸውን ትግሮች እንዲጨፈጭፉ ቢያዝ “አንታዘዝም!” አይሉም፡፡ ስለሆነም በዚህ መልኩም ያስፈጸመው ወንጀል ሊኖር እንደሚችል ብንጠረጥር መልካም ነው!!!
ሆነም ቀረ ፀረ አማራው የወያኔ አህያ ብአዴን የተባለው የጥፋት ኃይል በዚህ ከላይ በጠቀስኩት ዓይነት አሻጥር በአማራ ላይ ለመቆመር፣ የአማራን ስም ለማስጠፋት፣ አማራን ፖለቲካዊ ኪሳራ ላይ ለመጣልና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እንዲጠላ ለማድረግ በማሰብ በወያኔ ታዞ የፈጸመው ወንጀል ካለም ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴን ለአንዲት ሰከንድም ቢሆን የአማራን ሕዝብ ወክሎ፣ ለአማራ ጥቅምና መብት ቆሞና የአማራን ሕዝብ ይሁንታ አግኝቶ አያውቅምና ብአዴንና ኃይሉ ለፈጸሙት ወንጀል የአማራ ሕዝብ ፈጽሞ ተጠያቂና ዕዳ ከፋይ አለመሆኑን ለሚመለከተው ሁሉ አበክረን መናገር፣ ማሳሰብና ማስጠንቀቅ እንዳለብን አጥብቄ ማሳሰብ እፈልጋለሁ!!!
አየኸው አይደል ወገኔ??? በዝርዝር እየተናገርኩ “ተው የጎነጎኑልህ ብዙ ሴራ አለና እንዳትገባ!” እያልኩ ደጋግሜ ባስጠነቅቅ አልሳማ ብለኸኝ በፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴንና በቡችላው አብን “ግባና ተዋግተህ እርስትህን አስመልስ!” ተብለህ ይሄው አሁን እያወሩ እንዳሉት መልሰው ለሚወስዱት ነገር ተታለህ ገብተህ እንደቅጠልም እረግፈህ አሁን ደግሞ እንደገና የሚያመጡብህን የጣጣ መዓት አየህልኝ አይደል???
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሰዎች አሜሪካና እንግሊዝ በዚህ ከቅጥረኛቸው ወያኔ ጋር ሆነው እያራመዱት ባሉት ጣልቃገብነትና ፍጹም አግባብነት በሌለው ፀረ አማራ አቋም አሜሪካንንና እንግሊዝን በዚህ ፍጹም አግባብነት በሌለው ሥራቸው የሚያወግዙትንና የሚኮንኑትን ወገኖች አሜሪካ እና እንግሊዝ የኢትዮጵያ ዋነኛ እረጅዎች መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካን እና እንግሊዝን የሚኮንኑትን ወገኖች ሲዘልፏቸውና መሳለቂያ ሊያደርጓቸውም ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ!!!
ቆይ እንጅ እነዚህ ግለሰቦች ለማለት የፈለጉት “አሜሪካ እና እንግሊዝ አንደኛ እረጅዎቻችን ስለሆኑ የፈለጉትን ነገር ቢያደርጉን እነሱን ፈጽሞ መቃወም የለብንም!” ነው እያሉ ያሉት??? እንዲህ ከሆነ ለማለት የፈለጉት “ሆዳም ደናቁርት!” በሉልኝ እባካቹህ???
ይሄንን ስል ግን አገዛዙ በቅጥረኞቹ በኩል ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ “የአሜሪካንን ጣልቃገብነት ለማውገዝ!” በሚል ያደረገውን ሰልፍ “ትክክለኛ ሰልፍ ነው!” እያልኩ እንዳልሆነ ልብ በሉ፡፡ ይሄ እና ወደፊት በአገዛዙ ቅጥረኞች የሚደረጉ መሰል ሰልፎች አገዛዙ አማራ ለአሜሪካ ጥላቻ ያለው አስመስሎ በማሳየት አማራን ለማስጠቆር የታሰበ የአሻጥር ሰልፎች ስለሆኑ በእነዚህ ሰልፎች ላይ በተለይም አማራ የሆንክ ሁሉ እንዳትወጣ አበክሬ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!
እንደ ሰው በአማራ ላይ የሚፈጸመው ፖለቲካዊ አሻጥርና  ጭፍጨፋ ሁሉ የሚያስከፋቹህ ሰብአዊነት የሚሰማቹህ ሌሎች ወገኖችም በእነዚህ ሰልፎች ላይ ባትገኙ ብየ እለምናለሁ!!!
ይሁንና ግን ሁሉም ኢትዮጵያው እከሌ ከእከሌ ሳይባል ወጥቶ አሜሪካ “ጥቅሜን ያስጠብቁልኛል!” በሚል መርሕ የጣሰና የጠበቀ ግንኙነት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር በመፍጠር ላለፋት ሠላሳ ዓመታት ይህችን ደሀ ሀገርና ምስኪን ሕዝብ እጅግ በሚጎዳ መልኩ ስታደርገው የቆየችውንና አሁንም እያደረገችው ያለውን ኢሞራላዊ፣ ኢሰብአዊና ኢፍትሐዊ ሥራዋንና ግንኙነቷን ሁሉ የሚኮንን፣ የሚያወግዝና እንድታርም የሚጠይቅ ድብልቅልቅ ያለ ሰልፍ ማድረግ ይጠበቅባቹሀልና ጊዜ ሳታጠፉ ሰልፉን አዘጋጁና ውጡ!!!
ለአሜሪካ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብየውም፣ ለእንግሊዝ መንግሥትም፣ ለአውሮፓ ኅብረት ተብየውም እንደዚሁ ማድረግ አለባቹ!!! ከዚህ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና አደራቹህን በዚህ ጉዳይ ላይ ዳተኛ እንዳትሆኑ!!!
Filed in: Amharic