>

የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማሲው ጦርነት የተሸነፈባቸው  አምስት ምክንያቶች - ጋዜጠኛ ኃይሌ ሙሉ

የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማሲው ጦርነት የተሸነፈባቸው  አምስት ምክንያቶች
ጋዜጠኛ ኃይሌ ሙሉ

• የትግራይ ልዮ ኃይል ሰሜን እዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ባደረሰው ጥቃት የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል በተመለከተ ወዲያውኑ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብና ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዝርዝር መረጃ በመስጠት የህወሓትን ሰይጣናዊ ድርጊት ማጋለጥ አለመቻሉ
• ደብረፅዮን “ከመከላከያ በዘረፍንው ዘመናዊ መሳሪያ እሳት እናዘንብባቸዋለን”   ሴኮ ቱሬ ደግሞ  “በአርባ አምስት ደቂቃ የተጠናቀቀ መብረቃዊ ጥቃት ነው የፈፀምንው”  በማለት  ወንጀለኛነታቸውን አምነው ሲቀባጥሩ መንግስት  ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቶ የእነ ደብረፅዮንን በቪድዮ ማስረጃ የተደገፈ ንግግር ለጋዜጠኞች በማቅረብ “ጦርነቱን ማን ጀመረውና ለምን ተጀመረ?” በሚል አለም አቀፉ ማህበረሰቡ ሲወዛገብ የቆየበትን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ አለመቻሉ
• የማይካድራ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንደተፈፀመ ወዲያውኑ የውጪ አገር ጋዜጠኞችን በሄሊኮፕተር ይዞ ወደቦታው በመውሰድ የትግራይ ሚሊሻዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአይናቸው ተመልክተው ለዓለም ህዝብ የሚያሳውቁበትን ሁኔታ ማምቻቸት አለመቻሉ
• የኢትዮጵያ ሰራዊት በጦርነቱን ድል እያስመዘገበ ሲሄድ እንደሞናሊዛ አይነት የተማረኩ ህፃናት የትግራይ ልዮ ኃይል ወታደሮችን ዮኒፎርማቸውን እንደለበሱ ቪድዮ በመቅረፅ፣ አስፈላጊ ከሆነም የአገር ውስጥና የውጪ ጋዜጠኞች በቦታው ተገኝተው እንዲያነጋግሯቸው በማድረግ ህወሓት ህፃናትን ለውትድርና በመመልመል( recruitment of child soldiers) ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆን አለማድረጉ
•  እንደ አሌክስ ዴ ዋል፣ ማርቲን ፕላውትና ዊሊያም ዴቪድሰን የመሳሰሉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተንታኞች፣ የውጪ አገር የሚዲያ ተቋማትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች  ህወሓት በሚሰጣቸው የገንዘብ ክፍያ ልክ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ  የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህ ተቋማትና ግለሰቦች ገና ከጥንስሱ ተአማኒነታቸው ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አለማድረጉ መንግስትን ትልቅ ዋጋ አስከፍሎታል።
 መንግስት አሁንም ከስህተቱ ተምሮ የህዝብ ግንኙነት ተቋሙን ሙያውና አቅሙ ባላቸው ሰዎች በተጠናከረ መልኩ ሊያደራጅ ይገባል! እንደ ሀገር በፕሮፖጋንዳው ዘርፍ ከመከላከል ወደማጥቃት መሸጋገር አለብን። ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን በወታደሮቻችን መስዋዕትነት ያገኘነውን ድል ሞቶ ለተቀበረው ወያኔ አሳልፈን ላለመስጠታችን ምንም ዋስትና የለንም።
Filed in: Amharic