>
5:13 pm - Saturday April 19, 8177

ወገን ሆይ ያልገባቹህ ነገር አለ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ወገን ሆይ ያልገባቹህ ነገር አለ!!! 

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አብርሃ ደስታ እያለ ያለው “መቀማት የፈለግነውን እንቀማለን፣ መዝረፍ የፈለግነውን እንዘርፋለን፣ የራሳችን ማድረግ የፈለግነውን የሌላን ንብረት ሁሉ የራሳችን እናደርጋለን! የራሳችን ያደረግነውን ሁሉ ባለቤቱ መልሶ እንዲወስድብን አንፈቅድም!” ነው እንጅ እያለ ያለው “ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ጠለምትና ራያ የትግሬ ርስቶች ናቸው፡፡ ለዚህም ሳንዱቅ ሙሉ የታሪክ መረጃ አለን!” አይደለም እያለ ያለው!!!
እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደምታዳምጡት እንኳንና ወልቃይት ራያ አክሱምም የአማራ እንደሆነ ሚዲያ ላይ ቀርቦ የመሰከረው አብርሃ ደስታ እንዲህ ሊል አይችልምና!!!
እሱ እያለ ያለው “እኛ ትግሬዎች ቋንቋችንና የመጫወቻ ሕጋችን ዝርፊያና ውንብድና ብቻ ነው፡፡ ሌላ ቋንቋና የመጫወቻ ሕግ የለንም፣ አይገባንም፣ አንቀበልምም!” ነው እያለ ያለው!!!
ስለዚህ “ቋንቋየና የመጫወቻ ሕጌ ዝርፊያና ውንብድ ብቻ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ ነገር አልሰማም!” ብሎ ጆሮውን የደፈነንና አሜሪካንና አውሮፓንም የዚህ አረመኔያዊ፣ ኢሰብአዊና ጨካኝ በሆነ የዘር ማጥፋት ጥቃት የታጀበው ዝርፊያና ውንብድናው ተባባሪ አድርጎ ያሰለፈን የጥፋት ኃይል በራሱ ቋንቋና የመጫወቻ ሕግ ለማናገር ቆርጦና ጨክኖ ከመውጣትና ከማናገር ውጭ ሌላ ምንም አማራጭና መፍትሔ የለንም!!!
ምንም እንኳ ከእነሱ ጎን የአውሬው የ666 አገልጋይ መንግሥታት አሜሪካ አውሮፓና ሌሎችም ቢሰለፉም ከእነኝህ ከአውሬው ከ666 አገልጋዮች መንግሥታት ኃይልና ጉልበት ይልቅ የእውነት አምላክ የእግዚአብሔር ኃይልና ጉልበት ይበልጣልና በእግዚአብሔር ታምነን እንሰለፍ ድሉ የእኛ ይሆናል ነውም!!!
“ጽኑ አይዟቹህ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ያለውን ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም!” 2ኛ ዜና መዋ. 32፤7 እንዲል ቃሉ!!!
እመኑኝ በእግዚአብሔር ታምነን ከተሰለፍን ትናንትና ኃይሉን በብላቴናው ዳዊት ወንጭፍና አንዲት ጠጠር ላይ አሳድሮ እጅግ ግዙፉን፣ ኃይለኛውን፣ ጉልበተኛውን፣ ጦረኛውን፣ የጦር ትጥቅ ታጣቂውን ጎልያድን  የገነደሰ፣ በግንባሩ የደፋ፣ የገደለ፣ ያዋረደና የእስራኤል ልጆችን ከመማረክ፣ ከመጋዝ፣ ከመበዝበዝ፣ ከባርነት፣ ከመሰበር፣ ከመዋረድ የታገደ አምላክ ዛሬም ከእኛ ጋር ይሆናል!!! 1ኛ ሳሙ. 17፤12-54
ምነው እግዚአብሔርን አምነንና በእግዚአብሔር ታምነን ከተሰለፍን ኃይለኞችን እንደምናሸንፍ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የአድዋ ጦርነት ላይ አላሳየንም እንዴ???
ውጊያውን የተዋጋው ማን ነበር??? ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ጊዮርጊስን ልኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ ላይ ሆኖ ውጊያችንን አልተዋጋልንም ወይ??? ይሄንን እውነት የጠላት የፋሽስት ጥሊያን ወታደሮች ሳይቀሩ አልመሰከሩም ወይ??? ያንን የሚያህል ግዙፍ ጦርነት በአጭር ሰዓታት ውስጥ የተጠናቀቀው በእኛ ኃይልና ጉልበት ነው እንዴ ታዲያ???
እናም ወገን ሆይ “እመን ብቻ እንጅ አትፍራ!!!” ማር. 5፤36
Filed in: Amharic