>
5:13 pm - Thursday April 20, 8609

አንዱን የመጣል አንዱን የማንጠልጠል የፖለቲካ ትርፍ...!!! (መርእድ እስጢፋኖስ)

አንዱን የመጣል አንዱን የማንጠልጠል የፖለቲካ ትርፍ…!!!

መርእድ እስጢፋኖስ
 
 “አንድም ሲቪል ሰው አልሞተም” ያሉት መሪያችን በ10ሺህዎች ነብስ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ…!!!

 

ገና ከጅምሩ ውሽት ማታለልን ፖሊሲ አድርጎ የፖለቲካ ጉዞውን የጀመረው የዶ/ር አብይ መንግስት አሁን መልስ የሚፈልጉ ብዙ ጥያቄዎች ከበውታል።
በትግራይ በተደረገው ጦነት አንዳችም ሲቪል አልተገደለም ብለው ሲያበቁ አሁን ከአንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብቻ 1000 ሰው ማለቁ ሪፖርት እየተደረገ ነው ።በሪፖርት ብቻ የሚያበቃ ጉዳይ አይመስልም ።ወደ አለም የዘር ጭፍጨፋ ተመልካች ድርጅቶች ከተወሰደ ነገሩ ቀላል አይሆንም። በፈረንሳይ አብዪት 1789 አ.ም ለመጀምሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው የአለም አቀፍ የሰውልጅ የዚጎች መብት ጥበቃ በ1948 አ.ም ደሰምበር 10 የተባበሩት መንግስታት ድርጂት ተቀብሎት በአንቀፅ 217 A ላይ አስፍሮ አፅድቆታል።
ኋላም በ1956 አ.ም 1972 አ.ም የሰበዊ መብት ዲክላሬሽንን ይበልጥ ተሻሽሎ ፀድቋል ።ከመጀመሪያ የ ተ.መ.ድ ምስረታ ጀምሮ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ ስምምነቱን ካፀደቁ አገሮች ውስጥ ትገኛለች።በሆኑም ከትግራይ እየወጡ ያሉ መርርጃዎች እውነትነታቸው ከተረጋገጠ በሰበዊ መብት ወንጀል ተጠያቂ ከመሆን የሚይስጥላት የለም።
ዶ/ር አብይ እንደ እነ ሎሮን ባግቦ የኮት ዲቮር መሪ እንደ ፍራንሲስ ቡዚዜ የሴንትራል አፍሪካ መሪ በአለም አቀፍ ክርሚናል ኮርት መቅረባቸው አይቀርም ማለት ነው።ወይም እንደ የሱዳኑ ጄነራል ኦማር አልበሽር በስልጣን የመቆየት እድል ካላገኙ በስተቀር።ወጣ ወጣና እንደሽንበቆ ተንከባልአለ እንደሙቀጫ የሆኑት መሪያችን አሳዛኝ የታርክ ባለቤት የሚደርጋቸው ደሞ ትላንት የሰላም ኖቤል ባለቤት ሆነው በማግስቱ በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ተጠያቂ መሆናቸው ነው.።ይህ ምናልባት በታሪክ አብይ አህመድን የመጀመሪአው ሊደርጋቸው ይችላል።
በአጨብጫቢዎች እና በገፅታ ግንባታ አስመሳይ ሰዎች የተክበቡት መሪያችን። እስከዛሬ የትጓዙበት መንገድ በተአምር እሳቸው ብቻ ሊፈፅሙት የሚችሉት ለውጥ እንደሆነ ያምናሉ።አለም በአብይ አህመድ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ነው የሚመስላቸው።
በጠ/ሚ አብይ አህመድ አለም እና የኛ አለም የተለያየ ከሆነ እጅግ ሰነበተ። በሳቸው አለም ኢትዮጵያ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ በኢኮኖሚ እገሰገሰች ነው።እንዳውም በዚሁ ትቀጥልና የዛሬ 30 አመት በአለም ላይ ሁለት የበለፅጉ ሀብታም አገሮች ይኖራሉ አንደኛዋ ኢትዮጵያ ነች ይሉናል።
በጠ/ሚ አብይ አለም የዘር ፖለቲካ የለም ።ብልፅግና ከዘር ፖለቲካ የፀዳ ነው። በኛ አለም ደግሞ ቀደም ባለው ጊዜ የነበረው ኦህዴድ አሁን ብልፅግና ኦህዴድ ነው። ቀደም የነበረው በአዴን አሁን ያለው ብልፅግና በአዴን ነው።ቀደም ያለው ሱማሌ ክልል አሁን ያለው ብልፅግና ሱማሌ ነው
በጠ/ሚ አብይ አለም ተረኝነት የለም። በኛ አለም 78% የፌድራሉ ሴክተር መስራቤቶች ስራስኪአጆች ኦሮሙማ ናቸው።73%የአዲስ አበባ ፖለስ ኦሮሙማ ናቸው።ትራፊክ እንዲሁም አገር ውስጥ ገቢ እና አየር መንገድ ከዚህም ሌላ የአዲስ አበባ ቀበሌ ፅ/ቤቶች ከመዘጋጃ ቤት ጀምሮ ኦሮሙማ ናቸው።
በጠ/ሚ አብይ አለም ሰላምና መረጋጋት ከመቼውም ይበልጥ ሰፍኗል። በኛ አለም ደግሞ ጥዋት በሰላም ከቤታችን ወጥተን በሰላም እንደምንመለስ እርግጠኞች አደለንም። በዘር ተለይቶ በሀማኖት ተለይቶ ከሰባት ሺ አማራ በላይ በኦሮምያ በመተከል እና በደቡብ ህዝቦች በግፍ ታርደዋል።
በጠ/ሚ አብይ አለም የስራ አጥ ቁጥር ቀንሷል። በኛ አለም ደግም ቀድሞ የነበረችው ኮብል ስቶን እንኳን ጠፍታ ዲግሪ ይዞ ሊስትሮነት ተጀምሯል።
በጠ/ሚ አብይ አለም ኢትዮጵያ ወደከፍታ እየሄደች ነው።ሜጋ ፕሮጄክቶች እየተከፈቱ ነው።በኛ አለም ደግሞ የነበሩትም እየተዘጉ ነው።ያሉትም በዚሁ የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ከቀጠሉ የመዘጋታቸው እድል በደጅ ነው።
አሁን ዋናው የፅሁፋችን መነሻ ደረስን።የጠ/ሚ አብይ አለም እና የኛ አለም እንደተለያየ ነው። እሳቸው በቅዥት አለምነው የሚኖሩት። በህልም አለም ነው የሚኖሩት።በምኞት አለም ነው የሚኖሩት። ምናልባትም ነብይ ስለሆኑ ሊሆን ይችላል። የሳቸው ነብይነት ግን ትንብቱን ስቷል ወይ አብይ እራሳቸው ትንቢቱ ሲመጣላቸው “አሰማማቸው” ተሳስቷል አላያም ከትክክለኛው ቦታ አይደለም ትንቢቱን ያገኙት።
ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለውናል። አዎ ቀንደኛው የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ ተውግዷል።የሰውም የኢኮኖሚም ከፍተኛ ዋጋ ምናልባትም ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ በአጭር ጊዜ ጦርነት የበዛ እልቂት ታሪክ የሚመዘገብበት እንደሆነ ከውዲሁ እየተገመተ ነው።በዚህ በከፋ ደረጃ ሌላ አሳፋሪ ጦርነት አድርገን ….አዎ ወያኔ ተወግደዋል።ነገርግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልግ ወያኔ ብቻ ሳይሆን የሳቸው ብሄር ኦሮሙማ እና የወያኔ ህገ መንግስት ጭምር መሆኑን ሊገነዘቡ በተገባ ነበር።
ይህ ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትራችን አለም በ (fantasy) ተይዞ አሁን ማለዳ ማለዳ በማያልቅ ውሽት እየነዱን በኢሳያስ ፍቅር ናውዘው በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአገራችንን በጎረቤት ሀገር ጣልቃ ገብነት የውስጥ ችግራችንን ለመፍታት ሞከሩ።
የውሽታቸው ብዛት በዚያው በሚያጨበጭብላቸው እና ቁጭ ብድግ በሚልላቸው የሞተው ፖርላማ ቀርበው “ኤርትራን አመሰገኑ ።ለምን?….።ኤርትራዎች ትንኮሳ በወያኔ እንኳን ቢካሄድባቸውም ለኢትዮጵያ ክብር ሲሉ መልስ አልሰጡም አሉ”…….ሳምንት ሳይሞላ ኢርትራዉያን በትግራይ የበቀል ግድያ ፥ዘረፋ፥አስግዾ መድፈር፥ንብረት ማውደም ላይ እንደተሰማሩ በራሳቸው አብይ በሾሙት የሰሜን እዝ ጀርነራል ታወቀ።
ጠ/ሚ አብይ አሁንም የሱዳንን መንግስትን አመሰገኑ።ለምን?….ለአካሄድነው ህግ ማስከበር እርምጃ ተገቢውን ድጋፈ ስለሰጡን አሉ።ሳምንት አልምላም ሱዳኖች የኢትዮጵያትን መሬት 2000 በላይ ሰዋችን እና በአለ ሀብቶችን አፈናቅለው ያዙ።ትንሽ ቆይቶ የሱዳኑ ጄነራል የኢትዮጵያን መሬት የያዝኩት በራሳቸው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፈቃድ ነው አሉ። እንዳውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ክደዋል መባልን ሲሰሙ “ጤናው የተቃወሰ ውሽታም ነው አሉ” የሱዳኑ ጀነራል አል ቡርሀን።(ከጦርነቱ አ4በፊት አብይ እጃቸውን እያሳሙ ፈረስ ፥ጋሻ፥እና ካባ ሽልመዋቸዋል)
ከአለም ህዝብ አይን እንዲርቅ ተደርጎ የተፈፅመው ይሄ የትግራይ ጦርነት ዳፋው ገና የሚያልቅ አይደለም። ለኢሳያስ አፈውርቂ የበቀል ካራ ያመቻቸው አብይ አህመድ አሊ ነው።የኤርትራ ጦር እንዲገቡ የፈቀዱት ደግሞ ራሳቸው አብይ አህመድ ናቸው።
በስብዊ ፍጡሮች ላይ ግፍ ተፈፅሟል።ኢርትራውያን የትግራይ ወንድሞቻችንን አርደዋል። ጨፍጭፈዋል። ይህ አሁን በአለም ሚድያዎች ክ4 ወር በኋላ የተፈቀደ የሚዲይ ተደራሽነት ጉድ ይዞ ብቅ እያለ ነው።
“አንድም ሲቪል ሰው አልሞተም” ያሉት መሪያችን በ10ሺህዎች ነብስ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ።
ኢሳያስ አፈውርቂ ለሰራው ጭፍጨፋዎች አብቹ ተወንጃይ??

Filed in: Amharic