>
5:14 pm - Friday April 20, 3027

የኦሮሙማ ፕሮጀክትን ማስቀጠል የሚችሉ ብዙ ጃዋሮች አሉ፤  አዲስ አበባን ለማዳን ስንት እስክንድሮች አሉ?  (አቶ ጎዳና ያዕቆብ)

የኦሮሙማ ፕሮጀክትን ማስቀጠል የሚችሉ ብዙ ጃዋሮች አሉ፤  አዲስ አበባን ለማዳን ስንት እስክንድሮች አሉ? 
አቶ ጎዳና ያዕቆብ

* እነሱ 10 አይን ይዘው አንዱን አጥፍተው  በዘጠኙ እያዩ የእኛን ያለንን አንዱን አጥፍተው
 ” የእኛም ጠፍቷል” ይሉናል?!?
* እህ… እስክንድር ነው ለጃዋር ማባያነት የታሰረው ? ወይስ ጃዋር ለእስክንድር ማባያነት የታሰረው???
ዶ/ር አብይ አህመድ ከነጃዋር እስር በኃላ << ለጉርሻ ስንጣላ: ማእዱን  ደፋነው>> ሲል ተደምጧል:: የሲዳማን ክልልነት ጃዋር ተዋደቀለት: አብይ አህመድ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ሲል ገለፀው: አባ ዱላ አሳለጠው: ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አበቤ ካዝናቸውን ከፍተው በድምር 150 ሚሊዮን ለገሱ:: ሲዳማን በተመለከተ በማእዱ ላይ ልዩነት የለም::
አዲስ አበባን ፊንፊኔ በማድረግ ያላሰለሰ ትግልም በማእዱ ላይ የነጥብ ልዩነት የለም:: በመጪው ምርጫም ኦፌኮና ኦነግ ተሳተፉም አልተሳተፉም የጉርሻ ጉዳይ እንጂ ማእዱ ላይ ልዩነት የለም:: ለዚህም ነው ከጃዋር ጋር ተጣሉ: ከለማ ጋር ተጣሉ የሚለው ድራማ ላይ ከአጀንዳ ያለፈ ፋይዳ የለውም ብዬ የደመደምኩት::
ማእዱን በሚመለከት ያም የኦሮሙማ ፕሮጀክት በቤተ መንግስት ያለው አብይ አህመድና በእስር ቤት ያለው ጃዋር ወይም መረራ: ዳውድ ኢብሳ: ሽመልስ አብዲሳ እያልን ስንደረድር ብንውል እነሱ ፍጽም የአላማ ጥራትና አንድነት ያላቸው:: ነገር ግን አንዳንዴ ማን ትልቅ ይጉረስ ላይ ፀብ ነው::
አንዳንዴ እስክንድር ነው ለጃዋር ማባያነት የታሰረው ወይስ ጃዋር ለእስክንድር ማባያነት የታሰረው ብዬ እጠይቃለሁ:: የኦሮሙማ ፕሮጀክትን ማስቀጠል የሚችሉ እጅግ ብዙ ጃዋሮች አሉ:: ነገር ግን አዲስ አበባን ለማዳን ስንት እስክንድሮች አሉ?
እነሱ 10 አይን ይዘው አንዱን አጥተው በተቀሩት 9 አይኖች አላማቸው ሲያስፈፅሙ: የኛን አንድ ያለችንን አይን  አጥፍተው ከኛም እኮ ጠፍቷል የሚል ብልጣ ብልጥ ምክኒያት ሲያቀርቡልን የኛዎቹ ጅሎች ደግሞ ጃዋር እስከታሰረ ድረስ እስክንድርም ስራው ያውጣው ብለው ቁጭ ብለዋል::
ወዳጄ በአብይ አህመድና በእስክንድር ነጋ መካከል ያለው አለመግባባት የማእዱ ሲሆን ከጃዋር ጋር ያለው የጉርሻ ብቻ ነው::
Filed in: Amharic