>

የጅብ ፖለቲካ....!!!  ከአንሙት አብራሃም (ጋዜጠኛ)

የጅብ ፖለቲካ….!!! 

ከአንሙት አብራሃም (ጋዜጠኛ)

ሐረር ⁽⁽የፍቅርና የመቻቻል ከተማ⁾⁾ ሲባል እውነት ይመስልሃል አይደል ?
● እውነታው ግን :- መገፋት ያንገሸገሸው ፣ አፓርታዊ አገዛዙ መድረሻ ያሳጣው የተገፋ ሕዝብ አለ
* ሐረር ሲባል እንኳን የሰው አብሮነት ጅብ የሚያለምድ የፍቅር አገር ይመስልሃል አይደል?፤
ቤተኞች ገዢ ፈላጭ ቆራጭ፤ ሌላው ባይታወር  ተገዢ፤ ቢወዱ የሚያኖሩት ባይወዱ የሚያፈናቅሉት የሰቆቃ ህይወት የተፈረደበት ህዝብ ነው።
 ይህን ማየት ከፈለክ ሪሰርች ማድረግም ካሰኘህ ሐረርና ህይወቱንም  አጥና !
ለብዙዎች ሐረር ብሔር ከቁብ የማይገባበት  ⁽⁽የደንታ ቢሶች⁾⁾ አገዛዝ የሚመስለው አይጠፋም። አዎ ሠፊው ሕዝብ እንዲያ ነው።
እውነታው ግን ሐረር ላይ ለአንዱ የተፈቀደ ለሌላው የተከለከለ የፖለቲካ መብት ስርዓት  ያለበት ነው። ተወላጆች 50 ፡ 50 ፡ 0: ይሉታል። ላለፉት ሰላሳ አመታት የክልሉ ምክርቤት  36 መቀመጫ ነዋሪውን ሳይሆን ⁽⁽ገዢዎችን⁾⁾ መስሎ የተሠራ ነው።
የክልሉ ፖለቲካ ባለቤት ሐረሪና ኦሮሞዎች ናቸው።
ሐረር ከተማ ካሏት 6 ወረዳዎች አራቱ የአማራ ወረዳ ናቸው፣ ሁለቱ የሐረሪ ናቸው።
በክልሉ ያሉት 17ገበሬ ማህበራት ደግሞ  ኦሮሞ ይኖርባቸዋል።
የክልሉ ምክርቤት ግን ይሕንን አይመስልም። አይደረግም።
● 25% የከተማውን ሲቪል ሠርቫት
● የከተማዋን መምህር ፣ ሐኪም ፣ ነጋዴ ወዘተ ለምርጫ ሲሆን ያምኑታል።
ያልተፃፈው ሕግ ደግሞ ከ36ቱ የምክርቤት ወንበሮች 18ቱ ላይ ከሐረሪ ብሔረሰብ ውጭ ማንም ሊወዳደርባቸው አይፈቀድም።
ዘንድሮ በሚደረግ የተመራጭ ጥቆማ ለወረዳ ፣ ለከተማ አስተዳደር ፣ ለክልል ምክርቤት ከቀደመው የተለየ ባህል እንዲኖር እንጠብቃለን።
አለበለዚያ ⁽⁽የፍቅርና የመቻቻል አገር⁾⁾ እያሉ መሞኘት የሚበቃበትና አፓርታይዳዊ የባዕድ አገርነቱ የሚታወጅበት  ዘመን ነው።
ጅብ የሚያላምድ ሳይሆን የጅብ ፖለቲካ መገለጫው ይሆናል። ሰፊውን ነዋሪ ያገለለ ለኔ ብቻ የሚል ፖለቲካ ከጅቦች ስስት የሚቀዳ ፖለቲካ ነው።
Filed in: Amharic