>

«"የሞተው የተፈናቀለው የእከሌ ብሄር ስለሆነ አያገባኝም !" የሚል አስተሳሰብ መቆም አለበት...!!!»  ወይዘሮ አሚና ሴኮ የአፋር ክልል ዋና አፈጉባዔ

«”የሞተው የተፈናቀለው የእከሌ ብሄር ስለሆነ አያገባኝም !” የሚል አስተሳሰብ መቆም አለበት…!!!»
ወይዘሮ አሚና ሴኮ የአፋር ክልል ዋና አፈጉባዔ
(ኢ ፕ ድ ) 

* “አማራ ከሞተ አፋር ሞቷል፤ አፋር ከሞተ ትግሬ ሞቷል፤ ትግሬ ከሞተ ከምባታ ሞቷል፤ ከምባታ ከሞተ ሌላውም ሞቷል ብለን ማሰብ አለብን” ያሉት አፈ ጉባኤዋ፣ ይህም በልዩነት መካከል ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ እንደሚያስወግድና አንድነትን ,እንደሚያጠናክር  መታወቅ አለበት
አገሪቷ ላይ በጥፋት ኃይሎች ምክንያት ሰብዓዊ ጉዳቶች ሲደርሱ የሞተው የእከሌ ብሄር ስለሆነ አያገባኝም የሚል አስተሳሰብ መቆም እንዳለበት የአፋር ክልል ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሚና ሴኮ አመለከቱ።አንዱ ክልል ያለ አመራር የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም አካባቢዎች ችግር ለመፍታት መስራት እንዳለበት ጠቆሙ፡፡
የአፋር ክልል ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሚና ሴኮ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፤ በአገሪቷ በጥፋት ኃይሎች በሚከሰቱ ጉዳቶች እንደ ኢትዮጵያዊ ማንነት እሳቤ የሞተው የእከሌ ብሄር ስለሆነ አያገባኝም የሚል አስተሳሰብ መቆም አለበት።
“አማራ ከሞተ አፋር ሞቷል፤ አፋር ከሞተ ትግሬ ሞቷል፤ ትግሬ ከሞተ ከምባታ ሞቷል፤ ከምባታ ከሞተ ሌላውም ሞቷል ብለን ማሰብ አለብን” ያሉት አፈ ጉባኤዋ፣ ይህም በልዩነት መካከል ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ እንደሚያስወግድና አንድነትን እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል፡፡
“የኢትዮጵያን ህዝብ በደም ስሩም ሆነ በአኗኗሩ ፈጣሪ ባርኮ አንድ ላይ እንዲሆን አድርጓል።በሁሉም አካባቢ ያለው ኢትዮጵያዊ ወንድምና እህት ነው። በሌላ አካባቢ የሚደርሰውን ሀዘን ሌላው መጋራት ይኖርበታል። የተፈናቀለውና የሞተው የእከሌ ብሄር ነው አይመለከተኝም የሚል አስተሳሰብ መጥፋት አለበት።በተለይ አዲሱ ትውልድ ለአጉል ሥልጣኔ ባለመገዛት የአብሮነት ባህሉን አጥብቆ መያዝ ግድ ይለዋል” ብለዋል፡፡
Filed in: Amharic