>

ኦነግ በምርጫዉ አይሳተፍም‼ (DW)

ኦነግ በምርጫዉ አይሳተፍም‼

DW

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ መወዳደር እንደማይችል አስታወቀ።
የግንባሩ ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ ዛሬ እንዳሉት ግንባራቸዉ በምርጫዉ ሊሳተፍባቸዉ የሚችላቸዉ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዉበታል።
አቶ ዳዉድ በተለይ ከዶቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በየአካባቢዉ የነበሩ የግንባሩ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተዋል፣ባለስልጣናቱና አባላቱ ታሥረዋል ብለዋል።
ግንባሩ በምርጫዉ ለመወዳደር ከአምና ጀምሮ ሲዘጋጅ እንደነበረ አቶ ዳዉድ ገልፀዉ አሁን ግን ኦነግ በምርጫዉ እንዳይወዳደር «ተገፍቷል» ይላሉ-ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ።
Filed in: Amharic