>

ፖለቲካዊ ብሔር ለሌለን አማሮች: መዳኛችን  ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነዉ...!!! (ተክለሚካኤል አበበ)

ፖለቲካዊ ብሔር ለሌለን አማሮች: መዳኛችን  ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነዉ…!!!
ተክለሚካኤል አበበ

የአማራ ብሄርተኝነት: የማይገባኝ ብሄርተኝነት ነው። ለአማራ ብሔሩ ኢትዮጵያ: የሚያዋጣው/የሚያምርበት ብሄርተኝነትም: ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ነው። የአማራ ብሄርተኝነት: እንደሚባለው አማራን ለመታደግ ሣይሆን: የአማራን የዘመናት የኢትዮጵያዊነት claim ለማሥጣልና: አገሩ ኢትዮጽያ የሆነውን አማራን: ባንድ ጠባብ ክልል/ግዛት በመወሠን: ከክልሉ ውጪ የሚኖሩትን ደግሞ: ዘወትር መጤነትና ባእድነት: ሁለተኛ ዜግነት እንዲሠማቸው ለማድረግ: በዋንኛነት በሕወሓት: በሻእቢያና ኦነግ የተፈበረከ: fake ብሄርተኝነት ነው። ከብዙ አመታት ትግል ኋላ ወዶገብ ወራሾችን: ባለቤት ነኝ ባይ አገኘ። የአማራ ብሄርተኝነት: በአሑኑ የአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችን መብት ካሥጠበቀ: ይሑንላቸው: ይደረግላቸው: ይመቻቸው። የአማራ ብሄርተኝነት ከአማራ ክልል ውጪ ያሉ የፍርጃ አማራዎችን ግን አያድናቸውም። አይጠብቃቸውም። አያድነንም። ሕወሐት ድርጅቱ እንጂ: ርእዮተአገሩ እንዳልተሸነፈ: ይልቅሥ የተከለው ብሔርን መሠረትና ማእከል ያደረገ ብሔርተኝነት ሕያው እንደሖነ የማሥበው: አማራ አማራ የሚሉ: እንደአሸን የፈሉ ብሄርተኞችን ሣይ ነው። ለአማራ አገሩም: ብሔሩም: ኢትዮጽያ: የሚያዋጣውም ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነው። ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት እንጂ: የአማራ ብሄርተኝነት ጉራፈርዳ: ጉምዝ: ነገሌ: ባሌ: ሐረርጌ ያለውን አማራ ከጥቃት አያድነውም። ለጊዜው ኢትዮጵያዊነትም ሙሉ በሙሉ አላዳነ ይሆናል። Ultimately ለኛ ፖለቲካዊ ብሔር ለሌለን አማሮች: መዳኛችን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነዉ። አማራን ከሌሎች ብሔረሠብ አባላት ያሥተሣሠረውና አብሮ የሚያኖረው ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነው።  ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ይለምልም። ያንሠራራ።
Filed in: Amharic