>

¨ውታፍ ነቃይ ...!¨ (በገመቹ መራራ)

¨ውታፍ ነቃይ …!¨

 
በገመቹ መራራ

ስለ “ውታፍ ነቃይ”ነት ዶ/ር ዮናስ በገጹ ጥቂት ብሎ ነበር እሷን አስቀድሜ የኔውን ላውጋችሁ:- ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት በቤተመንግስት ውስጥ የነበረ የስራ ድርሻ ነው።
ንግስቲቱ በሄዱበት ሁሉ አብሮ የሚዞር አንድ ባለሙያ አለ፤ “ውታፍ ነቃይ” ይባላል። ስራው ንግስቲቱ ከተቀመጡበት ሲነሱ “የመቀመጫቸው ፍንክት” ቀሚሳቸውን “ጎርሶት” እንዳይቀር ተከታትሎ ስቦ የሚያወጣ ነው!!!
*      *     *
ስለ ውታፍ ነቃይነት ..
አንድ ወቅት የሰማሁት ቀልድ ትዝ አለኝ። ይያያዛል። ሰውዬው ፊቱ አብጦና አይኑ ቀልቶ ሲመጣ መንገድ ላይ ወዳጁ ያየውና ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል። «ቤተክሲያን ሂጄ ሰው መታኝ» ሲል ይመልሳል። ወዳጁም «እውነትቤተክርስቲያን ውስጥ ሰው መታህ?» ሲል ይጠይቀዋል። ሰውዬውም «ከፊቴ የተቀመጡት ሴትዮ ከተቀመጡበት ሲነሱ የመቀመጫቸው ቀሚሳቸውን ጎርሶት ስለነበር ስቤ አወጣሁላቸው። ሴትየዋም ዞረው በጥፊ መቱኝ» ሲል ነገረው።
በሳምንቱ ሰውዬው አሁንም ተመትቶ መጣ። ወዳጁም ምን ሆንክ ሲል ጠየቀው። «ቤተስኪያን ሄጄ ተመታሁ» ሲል መለሰ። ወዳጅም በአግራሞት «አሁን ደግሞ ምን ተፈጠረ?» ሲል ጠየቀው። ሰውዬውም «የባለፈዋ ሳምንት ሴትዮ አሁንም ፊት ለፊቴ ነበሩ። እናም ከተቀመጡበት ሲነሱ ቀሚሳቸው ተነክሶ ነበር። አጠገቤ የነበሩት ሰውዬ አዩና ስበው አወጡት። ከዚያ እኔ ደግሞ ሴትየዋ ሲወጣ አይወዱም ብዬ መልሼ ከተትኩት። ዞረው አሁንም በጥፊ መቱኝ።» ሲል መለሰ። የኛ ውታፍ ነቃይ።
Filed in: Amharic