>
5:13 pm - Sunday April 20, 9597

የዘር ፍጅትን እንደታክሲ ግፊያ በይቅርታ…? (ክርስቲያን ታደለ)

የዘር ፍጅትን እንደታክሲ ግፊያ በይቅርታ…?

ክርስቲያን ታደለ

*… መተከል ላይ የተፈፀመው የዘር ፍጅት ወንጀል ነው። ወንጀሉ ለተከታታይ 4 ወራት በላይ የዘለቀ ጭፍጨፋ የተፈፀመበት ነው…!
የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለተፈጸመው ግድያና ውድመት ይቅርታ ጠይቀናል ብለዋል ይቅርታ በራሱ ለተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ እውቅና ይሰጣል ብዬ አልገምትም የህግ ክፍተቱን ካልሆነ በስተቀር ነገር ግን ሁሉም የክልሉ ባለስጣናት ሃላፊነት ተረክበው ክልሉን እንዲሚመሩት መጠን ይህ ድርጊት ሲፈጸም በየደረጃው ያሉ የሚመለከታቸው ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ ባለስልጣናትና ወንጀለኞችን በሕግ እስካልተጠየቁ ድረስ ተገቢውን ካሳ ለተጎጂዎች እስካልተሰጠ ድረስ ይቅርታው የፖለቲካ ቀልድ እንጂ ከቃላት ያለፈ ፋይዳ የለውም የምርጫ አጀንዳ ካልሆነ በስተቀር !!?
መተከል ላይ የተፈፀመው የዘር ፍጅት ወንጀል ነው። ወንጀሉ ለተከታታይ 4 ወራት በላይ የዘለቀ ጭፍጨፋ የተፈፀመበት ነው። በዚህ ወንጀል በቀጥታም
ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዲሁም ወንጀሉ እንዳይፈፀም መከላከል እያለባቸው ይህንን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የመንግስት ኃላፊዎች በሙሉ ለፍትኅ መቅረባቸው አይቀርም።
የዘር ፍጅት ወንጀል እንደታክሲ ላይ ግፊያ በይቅርታ የሚታለፍ አይደለም።
ምኅረትም ሆነ ይርጋም አይኖረውም።
Filed in: Amharic