>
5:13 pm - Tuesday April 19, 8766

የጄነራሉ ዳግማዊ ስህተት...!!! (ተስፋየ ገ/አብ)

የጄነራሉ ዳግማዊ ስህተት…!!!

ተስፋየ ገ/አብ

 

ህወሃት ለሁለት ሲሰነጠቅ የቀደሞው ጠ/ሚንስትር መለሰ ዜናዊ የመጠቃት እድል በተቀናቃኞቼ በኩል ይደርስብኝ ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ከስልጣን ካባረሯቸው በርካታ ባልደረቦቻቸው አንዱ ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ አንዱ ነበሩ።ጀነራሉ ሲባረሩ ለምን ሳይሉ አድፍጠው ቆዩና የራያ ቢራ መስርተው የአክሲዮን ባለድርሻ መሆናቸውን ሰማን።ታዲያ እኒህን ጡረተኛ ጀነራል ትንሽ በአመለካከት ሻል ይላሉ ተብሎ ስለሚገመት አሮጌውና በስህተት የላሸቀው ህወሃት አመራር ውስጥ ይገባሉ ብሎ ማን ያምናል?
መቼም ጄኔራል ጻድቃን እንዲህ ያለ ዳግማዊ ስህተት ላይ ይወድቃል ብዬ ገምቼ ባለማወቄ ራሴን ታዘብኩት። ራሴን የታዘብኩት እነ ስዬ፣ እነ ጻድቃን፣ እነ ስዩም፣ እነ አባይ በትክክል ያቀዱትን፣ ያለሙትን፣ የተመኙትን የከሸፈ ህልም ከሰማሁ በሁዋላ ነው።እቅዳቸው ወዲህ ነው!
በቅድሚያ የኢትዮጵያን መከላከያ ሃይል ማጥቃትና መቆጣጠር። በመቀጠል ጎንደር፣ ባህርዳር እና ደሴን መቆጣጠር።ልክ በዚህ ጊዜ አብይ አህመድ ቤተሰቡን ይዞ ስለሚኮበልል አዲሳባ ላይ በተደራጁ አባላት እና ደጋፊዎች ቤተመንግስቱን መቆጣጠር።
በመቀጠል ትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን በማስገደድ ከፊት በማስቀደም እንደ ፓሎኒ ኩዋስ እየነጠሩ አስመራ እና ምጽዋን መያዝ።
ከዚያም ህሊና አልባ ኢትዮጵያውያንን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ምኒስትር አድርጎ በመሾም ኢትዮጵያን በእጅ አዙር መግዛት።በመቀጠል ኤርትራን ለዘላለሙ እንዳትነሳ አድርጎ ማውደም። መሰረተ ልማቶችን ማፈራረስ፣ የኤርትራውያንን ትውፊት፣ ማህበራዊ ክብር፣ አገራዊ ስሜት እና ሰብአዊ ኩራት መድፈር እና ማዋረድ – ነበር የታሰበው።
እዚህ ለመግለጽ የማልፈልገው አሰቃቂ ድርጊት በኤርትራውያን እና በአማራ ማህበረሰብ ላይ ለመፈጸም አቅደው እንደነበርም በቂ መረጃ አለኝ። ልገልጸው ግን ፍላጎት የለኝም። ምክንያቱም ታሰበ እንጂ ስላልተፈጸመ መግለጹ ጥቅም የለውም።
ዞረም ቀረ ወያኔ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ንጹሃን ዜጎች ላይ ለመፈጸም ያቀደውን አሰቃቂ ድርጊት መፈጸም በጀመረ ልክ በ18ኛው ቀን ነገሮች ሌላ ሆኑ።
ክፉ አሳቢ የወያኔ መሪዎች ክፉ ገጠማቸው። ተማረኩ ወይም ተገደሉ። ባህርዳር እና አስመራን ለማውደም ያሰቡትን ራሳቸው በራሳቸው ላይ ፈጸሙት። በ30 አመታት የገነቡዋትን ትግራይ በ3 ሳምንታት አፈራረሷት። እናም የወያኔ መሪዎች ከሚሳኤል መተኮስ ወደ መማረክ ተሸጋገሩ። ከዚያም አልፎ በአሜሪካ መሬት ላይ ሲንደባለሉ ታዩ። ይህ መንደባለል አሳፋሪ ትርኢት ሆኖ ታየ።
ጄኔራል ጻድቃን በእግሪ መኸል ውጊያ በገጠመው አሰቃቂ ሽንፈት ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰ ሰው እንደመሆኑ እንዴት ዳግም ሊሳሳት እንደቻለ ግን መረዳት አቅቶኛል።
Filed in: Amharic