>

«ባለፉት 27 ዓመታት የተዘራው መርዝ ቀላል አይደለም  - ሕዝቡ  ሁሉን ችሎ በትዕግስት አሳልፏል...!!!»  (ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

«ባለፉት 27 ዓመታት የተዘራው መርዝ ቀላል አይደለም  – ሕዝቡ  ሁሉን ችሎ በትዕግስት አሳልፏል…!!!» 
-ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
(ኢ ፕ ድ ) 

አንድነታችን ተሸርሽሯል የሚሉ ወገኖች በዓድዋ ላይ የታየው አንድነት በህዳሴ ግድብ ላይ መደገሙን ካለማየት የተነሳ የሚያነሱት ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አስታወቁ።
ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አንድነታችን ተሸርሽሯል የሚሉ ወገኖች ዓድዋ ላይ የታየው አንድነት በህዳሴ ግድብ ላይ መደገሙን ካለማየት የተነሳ የሚያነሱት ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።
ለእኔ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን አልተሸረሸሩም፤ አሁን እየተከሰተ ላለው ችግር ሁለት ነገሮችን፣ ቅጽበታዊና ነባራዊ መነሻዎችን ማንሳት እንደሚቻል ያመለከቱት ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል፣ ነባራዊ መነሻው፣ በሀገረ መንግሥትና በብሔረ መንግሥት ግንባታ ላይ በጅምር የቀሩ ያልተሠሩ ሥራዎች መኖራቸው ነው ብለዋል፡፡
ከዘመናዊ መንግሥት ከአፄ ምኒልክ በፊት ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ብዙ መንግሥታት ነበሩ፡፡ ያም ሆኖ ግን አገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ ክፍተቶች ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔሮች ማንነታቸውን በሚገባው ተገንዝበው አገራቸውን የሚያሳድጉበት ሁኔታ ላይ በርካታ ሥራዎች እንዳልተሰሩ አመልክተዋል፡፡
ለቅጽበታዊ ክስተቶች ደግሞ ያለፉትን 27 ዓመት ማንሳት እንደሚቻል የጠቆሙት ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል፣ ባለፉት 27 ዓመታት በሕዝቡ መካከል የተዘራው መርዝ ቀላል አይደለም፣ ሕዝቡ በተፈለገው ልክ ቀውስ ውስጥ ሳይገባ ሁሉን ችሎ በትዕግስት አሳልፏል ብለዋል፡፡
Filed in: Amharic