>
5:13 pm - Thursday April 20, 4305

አንበሶችና ጅብ (መስፍን አረጋ)

አንበሶችና ጅብ

መስፍን አረጋ


በእኔ ነግስ እኔ ነግስ ውጊያ በመቀስቀስ

አንበሳና አንበሳ ተፋልመው እርስ በርስ፣

አንደኛው ድል ሆኖ የሞት ጽዋ ሲቀምስ

ሌላኛው ሲያጣጥር ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ፣

የሞተን ተራምዶ የቆሰለን ገድሎ ጅቦ ሆነ ንጉስ፡፡ 

አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ

ርስበርስ ተናክሰህ በምክኒያት ተልካሻ

ስትዳከምለት በስተመጨረሻ፣

ቁርጥምጥም አድርጎ የቦረና ውሻ

ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ዑመር ዋሻ፡፡

ያገርህ፣ የምነትህ፣ ያንተነትህ ዳራ       

ባንድኛችሁ እንኳ እንዲኖር ሲጠራ፣

ሳትፋለም በፊት ከወንድምህ ጋራ

የጋራ ጠላትህ መሞቱን አጣራ፡፡

ጠላትህን ግን ለይ እንዳትቀላቅል

ኦሮሞና ኦነግ ናቸውና እየቅል፡፡

 

Email: mesfin.arega@gmail.com

                   

Filed in: Amharic