>

የጦር ወንጀለኝነት ለማ? ለአብቹ???? (መርእድ እስጢፋኖስ)

የጦር ወንጀለኝነት ለማ? ለአብቹ????

መርእድ እስጢፋኖስ

ዋሽንግተን ፖስት በተላንትና ባስነበበው እትሙ”won Nobel prize now accused of war crime “በሚል ርእስ ስር የአብይን አስተዳደር በወንጀለኝነት ከሷል በከፋ ሂስም ጠርቧል።
ጠ/ሚ አብይ በጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቁ ይገባል የሚል አስተታየት ይሁን ቅስቀሳ በ opinion ገፁላይ ይዞ ወጥቷል።ለኢትዮጵያ አሜርካኖች ወዳጅ ሆነው አያውቁም ከሆነም ደግሞ በመልካም ግዚያችን ወቅት ብቻ ነው።በችግራችን ጊዜ ተጨማሪ ችግር ሆነው እንጂ የሚመጡት መፍትሄ ሆነው አይደለም። ይሄንን ደግሞ ከአንድም አራት ጊዜ አሳይተውናል።
1937 አ.ም በጣሊያን ወረራ ግዜ አሜሪካ ከኢትዮጰያ ተቃራኒ የቆመችበት ወቅት ነበር።ወራሪን እና ተወራሪን እኩል በመፈረጅ አሜሪካ ኢትዮጵያን በድላች። 1977 አ.ም አሜርካ ከሶማልያ ጎን በመቆም ኢትዮጵያ እንድትወረር ድጋፍ ሰጥታለች።እንዲያውም በንግሱ ሀይለስላሴ ለጦር መሳሪያ የተከፈለን 80 ሚልዮን ዶላር በውቅቱ በስምምነቱ መሰረት ለኢትዮጰያ እንዳይተላለፍ በማድረግ ለሶማልያ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ በጦርነት ተሳትፋለች ማለት ይቻላል። ሶዎስተኛው በ1987አ.ም የውቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግስቱ በረሀብ የሚርግፈው ህዝብ ላይ ትኩርት ከማድረግ ይልቅ ከሊቢያው መሪ ከኮሎኔል ጋዳፊ ጋሪ ያዙኝልቀቁኝ ሲል(አሜርካ ድብደባ ፈፅማ ነበር)
የውቅቱ 40ኛው የአሜሪካ ፕሪዝዳንት ሮናልድ ሬገን የትግራይ ነፃ አውጭን በይፋ እርዳታ ሰጠ በአሜሪካ አጃቢነት በኢትዮጰያ ታርካዊ ተላቶች ርብርብ ደርግ ወደቀ ወያኔ ዘረኛ አፍራሽ ፖለተካዋን ይዛ 1990 አ.ም ነገሰች።በመቀጠልም ኢትዮጵያን በማስገንጠልም አክትቭ ተሳታፊ ነበረች።
የኦሮሞ የኢትዮጵያዊው አልሽባብ ቄሮ በኦሮምያ ጎዳናዎች ላይ ነውጥ ሲጀምር “እንደ አምባስደር ማርክ ባዝ አይነት ብቅ ብለው” የዘር ፖለቲክስን በኢትዮጵያ ብንመከረው ጥሩ ነው እስከማለት የደረሱ ናቸው።አሚሪክኖች አሁን ለአምስተኛ ጊዜ ታሪካዊ ጠላትነታቸውን በማሳየት ላይ ናቸው።
ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ በአሜርካኖች ብሬን ወሽ ተደርገው ወደ ስልጥስን የመጡ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው።የድጋፍ ስልፍ ላይ የመግደል ሙከራ ተደረገባቸው ተብሎ እንኳ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመድፈር FBI(የፌድራል ቢሮ ኢንቨስጋቲጌሽን ) ከ ዋሽንግተን የተላክከላቸው ሰው ናቸው።
የኖቤል ሽልማት ለጠ/ሚ አብይ እንደሚገባ አድቮኬት ያደረጉ አብዛኛው የሜሪካን ምሁራን እና ስኮልርስ ናቸው።
Now……ጠ/ሚ አብይ ላይ ሁሉም በሚባል ደረጃ የአሜርካን ጋዜጦች ዘምተዋል። ሁልግዜ በኢትይኦጵያ ላይ የተሳሳተ እይታ ካለው ንዮርክ ታይምስ ፥ ጀምሮ ዋሽንግተን ፖስት፥ ዎል ስትሪት ጆርናል ሁሉም…. በሚባል ደርጃ ባለተርጋገጠ ጉዳይ በጦር ወንጀለኝነት ጠ/ሚ አብይን እየከሰሱ ነው።
አሁን ለአምስተኛ ግዜ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን የምፍረስ ሴራ ላይ ተሰማርተዋል።
የጠ/ሚ አብይ ወጣ ወጣና እንደሽንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ እንዳይሆኑ እሰጋለሁ።የስጋቴ ምክንያት መንከባለላቸው ብቻቸውን ቢሆን ው/ሮ ዝናሽ ታያቸው ይጭነቃት ምን አገባኝ ባልኩኝ ነበር።ነገር ግን የሚንከባለሉት ብቻቸውን ሳይሆን መቶ አስር ሚልዮን ህዝብ ይዘው ነው። ይቺ ላለፉት 50 አመታት የመሪ ድሀ የሆነች ሀገር ኢትዮጵያን ይዘው በመሆኑ ያስፈራኛል።
ለሚሰነዘርባቸው ክስ ይኽው መልስ አይሰጡም ያሉት።የት እንዳሉም የሚያውቅ እዝግዚያብሄር ብቻ ነው። ላለፉት 21 ቀናት ይፖለቲካ “ኳራንቲን” ያደረጉ ይመስላል።ችግሩ ግን ጥሩ ጊዜ አልመረጡም ።
ከሳቸው ይሁን ከአጃቢዎቻቸው ባይታወቅም በዚያች 140 ቃለት በሚሰፍርባት ትዊተር ገፃቸው የሚወራው ነገር አንድ አይነት ነው።”የጌታ እራት ይመስል” የሸገር ገበታ ነው።ጥዋትም ማታም።ኮይሻ ጎርጎራ ውንጪ ፓርክ ነው።
መተከል 300 የአማራ እናት አባቶች ህፃባናት አዛውንቶች ታርደው ጠ/ሚ ራችን ያዝኑ ይሆን ስንል …ሶስተኛው ዙር የሽገር ገብታ እራት……ይላሉ
መተከል ላይ ሌላ 270 ሰው ታረደ ጉራ ፈርዳ ላይ 80 ላይ ኮንሶ ላይ 90 የአማራ ተውላጆች ታረዱ እያለ ይቀጥላል።ጠ/ሚ ራችን እንደሰው ያዝኑ ይሆን ስንል የተለመደው ትዊተር ገፃቸውን ስንዳብስ አሁንም ያቺው ፓርክ ነች ያለችው ….ኮይሻ ፓርክ ፥ወንጪ ፓርክ ሶዎስተኛው ዙር የጌታ እራት……
ባንዲራ ዝቅ ብሎ ይውለብ ለብ ይላሉብብለን ስንጠብቅ…ፓርክ የጌታ እራት…ደን እና ዱር አራዊት….
በኢሳያስ ፍቅር ሰክረህ የኪሳራ ጦርንርት ውስጥ አንዳንታስገባን ስንል ስንጮህ ሰሚ ጆሮ ጠፍቶ የተፈራው አልቀረም ወያኔ ራሷም ጠፍታ ይኽው ኢትይጵያን ይዛ መቃብር ለመግባት እየሞከረች ነው።
ኤርትራ ፥ግብፅ ፥ሱዳን፥እና ኦሮሙማ ተባብረው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳትኖር በረቀቀ መንገድ እይሰሩ ነው።ለዚህ ነው የአማራ እና የትግሬ ትንቅንቅ ኢትዮጵያን ለማፈረስ አሰፍስፎ ለሚጠብቀው ኦሮሙማ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራልና ወያኔ ጦስ እንዳይበላን ያለነው። እንደተፈራው አልቀረም
ጦነቱ አበቃ ከተባለ በኋላ ወታደራዊ የክብር ልብሳቸውን ለብሰው መቀሌ ላይ ከታዩ ወዲህ 24 ሰአት ከሚኖሩበት ከሚወዱት የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ጠፉ 21 ቀናቸው።ዛሬ ብቅ ብለው ታይተዋል።
ሞቱም ያሉ አሉ ።ታመሙም ያሉ አሉ።አኮርፉም ያሉ አሉ።በምሀል ደግሞ ስራቸውን እየሰሩ ነው አና ስማቸውን ብታጠፍ አይቀጡ ቅጣት ይደርስባችኋል የሚለው የደህንነት ማእከል ማስጠንቀቂያም አለ…….
እኛ እንግዲህ ስለመሪያችን የማውቅ መብት የለንም ማለት ነው?።መኖራቸው የፈየደው ነገር ባይኖርም አለመኖራቸውን በዚህ ሰአት ግን ጉዳታችን ነው።ምንም ይሁን ምን በዚህ ሰአት አለሁ ሊሉን በተገባ ።ጠ/ሚ አብይ ምርጫ አይደሉም ግዴታ እንጂ አሁን ባለው የፖለቲካ አየር።
ያደቖነ ሰይጣን ሳያቄስስ አተውም እንዲባል።ይቺ መሰውር ንም ከኢሳያስ አፈውርቂ ኮርጀው እንዳይሆን እንሰጋለን…እንደ ሰችዊሽን ሩሙ።
አምባገነን መሪዎች ባህሪያቸው አንድ አይነት ነው።የኩባው ፊደል ካስትሮ 53 አመት በሞላው ስልጣናቸው ዘመናቸው ወቅት አንድ ሰሞን በቴሊቭዥን ይታዩና ….ይሰወራሉ…ይደበቃሉ…ከዛ ከአለም አቀፍ ኢምጴሪያሊዝም(usa) ጀምሮ ተቃዋሚዋች ታመዋል ወይ ሞተዋል ይላሉ።ከዛ ተአምረኛው ፊዳል ክአስትሮ ቶሳክኖውን አፉ ላይ ይዞ እየሳቀ ብቅ ይላል። የሰሜን ኮርያው የኪሚል ሱንግ ቤተሰቦችም እንዲሁ ናቸው …አንድ ሰሞን ይጠፋሉ ከዚያ ብቅ ይላሉ።ህዝቡም መሪያችንን አየሁ ብለው ያለቅሳሉ…የአፍሪካው ኪሚል ኡን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂም እንደዛው ነው አንድ ወር የጠፋ እና የተቃዋሚ ሀይሎች እና የአውሮፓ ሚዲያዎች ሞተ…ወይ ታምመ ይላሉ። ከዚያ ብቅ ይል እና ሲ አይ ኤ እና የወያኔ ጭፍራ ምኞት ነው ይላል….
አሁን የኛው ጎረምሳው ጠ/ሚ መናገር ባለበት ጊዜ የሚነሱበትን ክሶች ማስተባበል ወይም እውነቱ መጋፈጥ ባለበት ግዜ ይኽው ምን ውስጥ እንደገባ…አላሁ አለም….መቼም ሰችዌሽን ሩም ሆኖ ደበረ ፅዮንን እያደነ እንዳልሆነ እንገምታለን…ጠፍተው ከርመው ብቅ አሉ።
አገራችን ወዴት እየሄች ነው ብሎ ለሚጨነቀው ኢትዮጵዊ አለሁልህ ማለት ባለባቸውጊዜ ከቦታቸው አልተገኙም……..ይህ ሁሉ ክስ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን አገርን የሚጠፋ እንደሆነ አልገባቸው ይሆን?፧፧
በፖለቲካ እውቀት ሳሆን በስሜት (populists movement) ወደስልጣን የሚመጡ ሰዎች የምያስፈሩት ለዚህ ነው።ጨኽት ወደስልጣን ያመጣቸዋል ያው ጩኽት ደግሞ ሊያጠፋቸው ይችላል።መሪያችንም የገጠማቸው ችግር ይኽው ነው። 7ኛው ንጉስ የገጠማቸው ችግር ራሳቸውንም ፖለቲካውንም ያለወማቅ ችግር ነው።አገር በትንቢት እና በተስፋ አይመራም ።አገር አለባበስን በማሳመር እና አንድ ቁና ውሽት በመደርደርም አይመራም ።አገር በእኔ ብቻ አዋቂነኝ በሚል ግብዝነትም አይመራም። አገር በጥበብ በሳይንስ በእውቀት ነው የሚመራው።
አሁን አገራችን ችግር ላይ ነች።ታመውም ከሆነ ፈውሱን ይላክላቸው።አኩርፈውም ከሆነ ጋኔሉን ያንሳላቸው(የፕሮቲስትስንት ጋኔል ፀበልም አያወጣውም ዳዳዳዳፖፖፖፖቡትሮ ቡትሮስ ሲሲ ሲሲ ቡርህን….ስም ወጋሁ !ወጋሁ!)ብለውም ቢሆን መሪያችንን ወደ መጀመሪያ የሲመታቸው ዘመን ያምጡልን…… ።ይቺ ጥዋት ማታ በትዊትተር የሚለቋት የኦሮሙማ እርሻ ልማት እና ፓርክ ፎቶ ሰልችቶናል።አንድ ፊቱን የእርሻ እና የደን ሚኒስቴር በሆኑ በተሻለ ነበረ።
በቃ ተሰናበትን ፈጣሪ አገራችንን ያስባት።አሜን! 
Filed in: Amharic