>

በፓስተርነት  ካባ የተጀቦነው ጥራዝ ነጠቁ ነውረኛ ...!!! (ጎዳና ያቆብ)

በፓስተርነት  ካባ የተጀቦነው ጥራዝ ነጠቁ ነውረኛ …!!!

  ጎዳና ያቆብ

አንድ ወዳጄ ዛሬ በጠዋቱ የፓስተር ዮናታንን ቅዱስ ብልግናና ቅዱስ ድንቁርና የሚያመላክት ቪዲዮ ላኮልኝ ተመልቼ እንደው ከጥቃቅንና አነስተኞች ሁሉ ጋር ወርዶ በጭቃ መጫወት የማይመጥንና የማይጠቅም ቢሆንም አንዳንዴ ከደፋርና ባጊጌዎች ጋር በልካቸው ማውራት አስፈላጊ መስሎ ስለተሰማኝ እነሆ!
ስለአምላክ ሚስጢረ ባህሪያት የተናገረውን ሙሴ በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 29 ቁ. 29 ላይ “ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው” የሚለውን እንዲያነብ ጋብዤ ልለፍ። የአምላክ ባህሪ መገለጫ “በሁሉ ቦታ መገኘቱ ነው” የሚል ሊያሳየኝ ስለማይችል ማለት ነው። ስለዚህ ስለክርስቶስ ውልደት እሱ ምን አለ፡ መጽሐፍስ ምን ይላል የሚለውን እንደአንድ አማኝ ልመርምረው። ዮናታን “ከስጋዋ ስጋ ነስቶ ከደሟ ደም ነስቶ ተብለን እንማራለን ነገር ግን እሱ ከመንፈስ ቅዱስ የተፀነሰ ነው። ከመንፈስ ቅስዱ የተፀነሰ ነው ማለት ወንድና ሴት ልጅ ሲወልዱ “Y” እና “X” ያዋጣሉ ማለት አይደለም። የመንፈስ ቅዱስ DNAው (“X” ወይም “Y”) ከድንግል ማሪያም (ዮናታት የምናገርበትን መደዴ ተውላጠ ስም “እሷ” የሚለውን መዋስ ስላልፈለግኩ ነው) ተፈጥሮዋዊ “X” ወይም “Y” ሊቀላቀል አይችልም ሲል ፓስተር ዮናታን ተናግሯል። መቼም አባጨሪሬም “አባ” ተብሏልና ከነብልግናው እራሱን የሾመበትን ማንጠልጠያ “ፓስተር” የምለውን አልነፍገውም።
ምንም እንኳን እሱ በጣም በትንሹ “ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይላሻል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ትውልድ ተሻጋሪ “ሁሉ”፡የሚለው ደግሞ የማያቋርጥ፣ ዘላለማዊና ይህንን ደፋር ትውልድም የሚያካትት መሆኑ ዕንደዚህ አይነቱ መናገር ትርፉ ጉንጭ ማልፋት ብቻ የሚሆን ከንቱ ጥረት ቢሆንም።
ወደ DNAው ስንመለስ፡ የስነ-ህይወት (Biology) ትምህርት እስከ 10ኛ ክፍል የተማረ አንድ መካከለኛ ወይም አነስተኛ የማሰብ አቅም ያለው ሰው ሴት “Y” Chromosome፡(ክሮሞሶም) እንደሌላት በምትኩም ሁለት X (XX) ክሮሞሶም እንዳለትና ወንድ ደግሞ አንድ “X” ና  “Y” (XY) እንዳለው በዚህም ምክኒያት ሁልጊዜ ከእናት X እንደሚወሰድ በውህደቱም ወቅት ከወንዱ (ከአባት) የተወሰደው X ከሆነ የእናት X እና የአባት X ተደምረው የውህደቱ ውጤት ሴት ልጅ እንደሚያስገኝ ነገር ግን ከአባት የተዋጣው “Y” ከሆነ ከእናት ሁሌም ከሚገኘው “X” ጋር ተጣምሮ ውጤቱ ወንድ ልጅ እንደሚሆን ያውቃል የሚል ግምት ነበረኝ። የዮናታንን ትንተና እስከምሰማ ድረስ! እውነት ለመናገር የእውቀት ማነስ ይህን ስህተት አገልፀውም ከእውቀት ነጻ ደግሞ ልለው አልፈልግም ስለዚህ አንባቢዎች በእውቀት ማነስና ከእውቀት ነጻ መሆን መካከል የሚያስታርቅ ቃል እንድታውሱኝ እጠይቃለሁ።
“ከስጋዋ ስጋ ነስቶ ከደሟ ደም ነስቶ” የሚባል ነገር የለም ይለናል ምንም እንኳን መፅሐፍ ቅዱስ “በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ” ሲል ወ ዕብራውያን ምዕራፍ 2:15 ይነግረናል። እንደዮናታን አይነት ሀሳዊ አስተማሪዎች ““ከስጋዋ ስጋ ነስቶ ከደሟ ደም ነስቶ” የሚባል ነገር የለም” የሚል የሀሰት ትምህርት ይዘው እንዳይመጡና ያልተዋሀደ የመንፈስ ቅዱስ DNA ይዞ ነው ጌታችን የተወለደው የያሉ እንዳያስቱን ደግሞ “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” ሲል እዛው ምዕራፍ ቁጥር 16 ላይ በማያሻማና ለትርጉም ባልተጋለጠ መንገድ ግልጽ አድርጎ ያስቀምጥልናል።
እንደሚመስለኝ ዮናታን ምንም እንኳን አቁማዳ ወይን ጠጅን ቢሸከምም የወይን ጠጁ ከአቁማዳው የሚጋራው ተፈጥሮ የለወም ስለዚህ ሊዋሀድ የማይችል የተለያየ ተፈጥሮና ስሪት ያላቸው ግን አንዱ አንዱን የሚሸከም ነው ለማለት የፈለገ ይመስለኛል። እንደዚህ ካልሆነ “በዘይትና ውሀ” እንዴት ሊመስለው ይችላል? ከርስቶስ በነገር ሁሉ ሰው ባይሆን ከአብርሃም ዘር ባይወለድ እንዴት ሰውን ለሜበዠት ስለሀጢያታችን ቤዛ ሊሆን ይችላል? መጽሐፍስ ስለምን “ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፡ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነርገ ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው” ይለናል? ወይ መጽሀፉ ተሳስቶአል ወይ ዮናታን ተሳስቷል። የሚቀስደው (ክርስቶስና) የሚቀደሱት (እኛ) ሁሉ ከአንድ ናቸውና ስለምን መጽሀፍ ይለናል? ክርስቶስ በስጋ እንደመጣ የማያምን የተረገመ ይሁን ሲል መጽሀፍ የሚደነግገው መቅሰፍትም እንዳይደርስብን የአብርሃምን ዘር የያዘው የመላእክትን አይደለም የሚለው ቃል የታመነ ነውና እኔና ቤቴ “ከስጋዋ ስጋ ከደሟ ደም ነስቶአል” እንላለን።
ደግሞም “ ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ” ሲል ዕብራዊያን 10:3 ይናገራል። መቼም ስለሜቤዥት ህግ እና ስርዓት ከሙሴ መጽሀፍት እንዳልጠቅስልህ ለብ-ለብ ተደርጎ ከዮሀንስ ወንጌል የጀመረ የተለመደ አስተምሮት አይፈቅድልህም በሚል ነው ዕብራዊያን ላይ ብቻ ቆይታ ያደረኩልህ። አነሰ ካልኩ እጨምራለሁ።  ስለክርስቶስ ከስጋ ስጋ ከደም ደም ስለመንሳት ይህን ብዬ ሳበቃ ለረጅም ጊዜ በአምላክ እናት ላይ ያለ ጥላቻና ንቀት ከየት የመነጨ ነው ብዬ እራሴን ስጠይቅ የደረስኩበት ነገር ቢኖር በብዙ የፕሮቴስታንት እምነት የሚጸባረቀቅ ጥላቻ የአምላክ እናት ላይ ብቻ ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ላይም እንደሆነ ነው። አንዳንዶች የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር ፍትህ ይጎድለዋል ሲሉ ምላሳቸው እንኳን አይደናቀፍባቸው። ክርስቶስን እግዚአብሔር ከሚባል ጨቋኝ ነጻ ያወጣቸው አድርገው ማቅረብም የተለመደ ነው። ስለዚህ ክህደት፣ ድፍረትና ጥላቻ የሚመስል ንቀትም ለአምላክ እናት ላይ በግልጽ፣ የአምላክ አባት (እግዚአብሔር አብ) ላይ ደግሞ በስውር የእምነቱ አካል ስለሆነ መደነቅም መደመምም ከተውኩ ቆይቻለሁ።

ቅዱስ ብልግናና ድፍረት

ደፋርነት፡ ብልግና ተሳዳቢነትን (ወይም በሌላ አገላለጽ ቅዱስ ባለጌነትን) ስለምን የፕሮቴስታንት ተፈጥሮአዊ ባህሪና ልዩ መገለጫ ሆነ? ከአባታቸው ከእግዜር ወይስ ከአባታቸው ከዲያቢሎስ እንዲህ አይነት ድፍረትና ብልግና የተማሩት? ይህን ባህሪ ከማን ወረሱት? ልጂ መቼም በምግባርም ይሁን በባህሪ አባቱ እንደሚመስል ጌታችን የሆነ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይናገራል። እናንተ የአባታችሁ የአብርሀም ልጆች ብትሆኑ ኖሮ ልትገድሉኝ አትፈልጉም ነበር፤ ነገር ግን የአባታችሁ የዲያቢሎስ ልጆች ስለሆናቹ ልትገድሉኝ ትፈልጋለችሁ፣ እሱ ከጥንቱም ነብሰ ገዳይ ነውና” ይላል።
ድፍረትና ብልግና የእግዚያብሔር ባህሪ እንዳልሆነ ይሁዳ በመልዕክቱ ሲያስረዳ “የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከር ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲናገር፦ ጌታ ይገሥጽህ፡ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም” ይላል። ዲያቢሎስን እንኳን በድፍረት ቃል እንዳይናገር ያደረገው ዲያቢሎስት ስለማይገባው ሳይሆን የአምላኩን የእግዚአብሔር ባህሪ የተላበሰ ትሁት እና ጨዋ ስለሆነ ነው። እንደ ዮናታት አይነቱ ግን ምንደኛ እረኛ ከቤተ መንግስት የሚያገኘው ፍርፋሪ እንዳይቀርበት ኢሬቻን በሚመለከት ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ምን ትላለህ ሲባል አፉን የለጉመ ይሁዳ በመልክቱ “ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት” ራሱን አሳልፎ የሰጠ፤ የወንጌል ሳይሆን የወንጀል ሰባኪው እራሱን ኮፍሶ “ጸጋን የተሞላሽ ሆይ” ብሎ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም መልዐክ “ይህ ምን አይነት ሰላምታ ነው” ብላ ድንግል ማሪያም እንድትገረም ያደረጋትን የአምላክ እናት፤ ከሌዊ ነገድ ከአሮን ወገን የሆነቸውና የታላቁ ካህን የዘካሪያስ ሚስት ፣ የመጥምቁ ዮሀንስ እናትና የድንግል ማሪያም አክስት የሆነቸው ኤልሳቤጥ “የማሪያምን ሰላምታ በሰምች ጌዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፡ በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባርክሽ ነሽ፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” የተባለላትን ድንግል ማሪያምን እንዲህ እንደቆሎ ጓደኛቸው ማውራት፣ አጥላላት እና ማናናቅ የጴንጤነት መለኪያ ሆኖአልና እያንዳንዱ ደፋር የመመረቂያ ወረቀቱን የሚጽፈው ድንግል ማሪያምን በመሳደብ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ስድብ ደግሞ የማን እና ከማን እንደሆነ መጽሀፍ ቅዱስ ሲለሚነግረን አባታቸው ማን ነው የሚለውን ፍንትው አድርጎ ያስረዳናል። “እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያ ለፍርሀት ራሻቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰፉ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፡፡ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀ ሉበበጋ የደርቁ ዛፎች፣ የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል” ናቸው እያለ ይሁዳ በመልዕክቱ የሚገልጻቸው ደፋር ፓስተሮች አንዱ ዮናታን መሆኑ እንዳልኩት ባያስገርምም ማሳዘኑ አይቀርም።ቤተ-ክርስቲያንን ወደየዋህነት እና እግዚያብሔርን ለመምሰል ሳይሆነ እንደሱቅ ለትርፍ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አድረገው ሲከፍቱ መጨረሻው ገደብ የሌለው ብልግናና ቅዱስ ባለጌነት ነው።
Filed in: Amharic