>
5:13 pm - Wednesday April 19, 9893

የአዲስ አበባ መሬት የተወረረው በማን ነው…? ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል:-  ( አሻራ ሚድያ)

የአዲስ አበባ መሬት የተወረረው በማን ነው…?
     ( አሻራ ሚድያ)
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል:-

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከፍተኛ የመሬት ወረራ መካሄዱን አስታውቋል፡፡
አሁን በእስር ላይ የሚገኘው አቶ አስክንድር ነጋ ከግለሰባዊ ትግል አልፎ በአዲስ አበባ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ፓርቲ እስከማቋቋም የደረሰው የኦሮሙማ ወረራ እና የፊንፊኔ ኬኛ ህልመኞችን የወረራ አካሄድ ለማክሸፍ ነው፡፡
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል እንዲሉ አዲስ አበባን ራሳቸው ከወረሩ በኋላ ራሳቸው ተቆርቋሪ እና መግለጫ ሰጭ ሆነው የሚያስተዳድትን ከተማ እንዲህ ሲሉ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋታል፡፡
‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ መልካም አስተዳደር ማነቆ በነበረው በህገ-ወጥ መሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ በጋራ መኖርያ ቤቶችና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ ሢያካሂድ የነበረውን ጥናትና ማጣራት በይፋ ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡
በግኝቱም 1,338 ሄክታር መሬት በህገወጥ የተወረረ መሆኑን፤ 322 ግንባታቸው ያለቀና ያላለቀ ህንፃዎች ባለቤት አልባ ሆነው መገኘታቸውን፤ 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች በተለያየ ህገ-ወጥ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን፤ 14,641 መኖርያና ለንግድ የተከራዩ የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በህገ-ወጥ ይዞታነት የሚገኙ መሆኑን በጥናት አረጋግጠናል!! ሲሉ፡ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ባካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳመላከቱት በከተማዋ በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት 1,338 ሄክታር ሲሆን በገንዘብ ሲተመን በ14 ቢሊየን ብር የሚገመት መሆኑንና የህዝብና የመንግስት ሀብት በሪል ስቴት አልሚዎች፣ በግለሰቦች፣ በሀይማኖት ተቋማትና በቡድን በመደራጀትና መንደር በመመስረት ጭምር በሚገለፅ መልኩ የመሬት ወረራ ተፈፅሟል፡፡
ይህም ድርጊት በአንድ በኩል ባዶ የሆነን የመንግስት መሬት በመውረር፣ በሌላ በኩል ደግሞ በህጋዊ መንገድ ግለሰቦች ከያዙት ይዞታ አጠገብ ያለን የመንግስት መሬት በህገወጥ መልኩ በመውረር የሚፈፀም መሆኑን ጥናቱ ያሳያልም ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አክለው በወረራ ከተያዘውና በጥናቱ ከተለየው 1,338 ሄክታር መሬት ውስጥ 1,050 ሄክታር የሚሆን መሬት እንዲፀዳ በማድረግ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የከተማውን ልማት በሚያረጋገጥ መልኩ በሊዝና ለትልልቅ የልማት ስራዎች በጨረታ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡
የባለቤት አልባ ቤቶች ጥናትን በተመለከተ በሁሉም ክ/ከተሞች በተደረገው የማጥራት ስራ የቤቶቹንና የህንፃዎቹን ባለቤት ሊያሳዩ የሚችሉ ሰነዶች ማግኘት ባለመቻሉና በተደረገውም ጥሪ ባለቤት የሆነ አካል በመቅረብ መረጃውን ማቅረብ ባለመቻሉ 322 ቤቶች ባለቤት አልባ በሚል የተለዩ ናቸው፡፡
ከነዚህ ውስጥ 58ቱ ግንባታቸው የተጠናቀቀ፤ 264ቱ በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ግንባታቸው ቆሞ የሚገኝ መሆኑን በጥናቱ ለመለየቱንና ቤቶቹና ህንፃዎቹ ያረፉት መሬት 229,556 ካሬ መሆኑ ተገልፆአል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ከ1997 ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት በተለያዩ ዙሮች በዕጣ ለተጠቃሚዎች ሲያስተላልፍ የቆየ ቢሆንም ለከተማ ነዋሪው ዋነኛ የቅሬታ ምንጭም ሆኖ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም በአጠቃላይ የቤት ማስተላለፍ ሂደት ችግሮችንና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለማጣራት የከተማ አስተዳደሩ በመወሰኑ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት በሳይንሳዊ አግባብ ዝርዝር ጥናት እንዲጠና አቅጣጫ ተቀምጦ ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰራ ቆይቶአል፡፡
በጥናቱ ዉጤት መሰረትም በህገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶች በጠቅላላው 21,695 ሲሆኑ 16,315 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ፣ 4530 ባዶ የሆኑ ( ያልተላለፉ) ፤ 850 ዝግ የሆኑ ( በአንድ ወቅት ሰዎች የነበሩባቸው ሲሆን ረጅም ግዜ የተዘጉ) ፤ እና 424 በህገወጥ መልኩ በግለሰቦች ተይዘው የሚገኙ ሲሆን የተላለፍበት ሁኔታ ሳይታወቅ ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51,064 ቤቶች ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በቤቶች ኮርፖሬሽን ተመዝግቦ የሚገኘው ባለዕጣዎች የስም ዝርዝር እና በመስክ በተገኘው የተጠቃሚዎች የስም ዝርዝር መሀከል ልዩነት ያላቸው ቤቶች 132,678 እንደሆኑና የህ የሚያሳየው አጠቃላይ የተገነቡት ቤቶች ከ75 እጅ በላይ የሚሆነው ተመቃሚ ኮንዶሚኒየም የተመዘገቡና የቆጠቡ አለመሆናቸውን ነው ብለዋል፡፡
18,423 ቤቶች ደግሞ የቤት ባለቤት ስም የሌላቸው መሆኑን በጥናቱ የተገኘ መሆኑን እና በነዚህ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች መረጃቸውን እንዲያቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም መረጃ ማቅረብ ያልቻሉ ወይም ያልፈለጉ በመሆናቸው ቤቶቹ በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሆናቸውን ያመላክታል፡፡
እንደ ወ/ሮ አዳነች ገለፃ ሳይገነቡ የተገነቡ ተደርገው የተያዙ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና የጋራ መጠቀሚያ ህንፃዎች በአጥኚዎቹ ተለይተዋል፡፡ በጥናቱ 28 ብሎኮች ማለትም ከ782 እስከ 842 የሚሆኑ ቤቶች እና 83 የጋራ መጠቀሚያ ህንፃዎች/ኮሚናል / ሳይገነቡ የተገነቡ መስለው የተዘገቡ ነገር ግን የተባሉት ግንባታዎች በአጥኚዎቹ የሳይት ቆጠራ (ምልከታ) ወቅት ሊገኙ ያልቻሉ መኖራቸውን አመላክተዋል፡፡
በፌደራልና በአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በተሰራው የኦዲት ውጤት መሰረትም በአጠቃላይ ላልተገነቡ ህንፃዎች የቦርድም ሆነ የስራ አመራር የውሳኔ ቃለ ጉባኤ አልተገኘም፤፤ ምንም እንኳን መረጃ ባይገኝም ለግንባታው ክፍያ አልተከፈለም ብሎ መደምደም እንደሚያስቸግር በኢዲት ጥናቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
የቀበሌ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ የተደረገውን የማጥራት ስራን በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ባሉ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች 138,652 ቤቶች በጥናት እንዲለዩ መደረጉን የገለፁት ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጥናቱም 10,565 በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች መገኘታቸውን እና ውጤቱ በዝርዝር ሲታይ 7,723 መኖርያ ቤቶች ውል በሌላቸው ህገወጥ ነዋሪዎች የተያዙ ፣265 ቤቶች በሶስተኛ ወገን የተያዙ ፣ 1,164 ቤቶች ኮንደሚኒየም በደረሳቸውግለሰቦች እንደተያዙ፤ 1,243 መኖሪያ ቤቶች ታሽገው የተቀመጡ፤ 234 የጠፉ ቤቶች ፣ 180 ቤቶች አድራሻቸው የማይታወቅ፤ 54 ቤቶች ግን በምን ምክኒያት እንደፈረሱ በጥናቱ መለየት ያልተቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም 537 በህገወጥ መንገድ ወደ ግል ቤትነት የዞሩ የቀበሌ ቤቶች በጥናቱ የተለዩ ሲሆን በዝርዝር ሲታይ 49 ቤቶች በህገወጥ መንገድ ወደ ግል እንደዞሩ ማስረጃ ያላቸው እና የተቀሩት 488 ቤቶች ግን በምን መንገድ ወደ ግል እንደዞሩ የማይታወቅ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል፡፡
የንግድ የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ በአጠቃላይ 4,076 በህገወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶች የተገኙ ሲሆን በዝርዝር ጥናቱ መሰረት 1,070 ቤቶች ውል የሌላቸው እና ነጋዴዎች እየተጠቀሙባቸው መሆኑ፤ 2,451 ቤቶች በ1086 ነጋዴዎች ከአንድ በላይ የንግድ ቤት የተያዙ ናቸው፡፡እንዲሁም 376 የቀበሌ ንግድ ቤቶች የተከራይ ተከራይ ሆነው በሶስተኛ ወገን የተያዙ እና 179 የታሸጉ መሆናቸውን ለመለየት መቻሉን የም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ መግለጫ ያሳያል፡፡
የባለቤት አልባ ቤቶች ጥናትን በተመለከተ በሁሉም ክ/ከተሞች በተደረገው የማጥራት ስራ የቤቶቹንና የህንፃዎቹን ባለቤት ሊያሳዩ የሚችሉ ሰነዶች ማግኘት ባለመቻሉና በተደረገውም ጥሪ ባለቤት የሆነ አካል በመቅረብ መረጃውን ማቅረብ ባለመቻሉ 322 ቤቶች ባለቤት አልባ በሚል የተለዩ ናቸው፡፡
ከነዚህ ውስጥ 58ቱ ግንባታቸው የተጠናቀቀ፤ 264ቱ በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ግንባታቸው ቆሞ የሚገኝ መሆኑን በጥናቱ ለመለየቱንና ቤቶቹና ህንፃዎቹ ያረፉት መሬት 229,556 ካሬ መሆኑ ተገልፆአል፡፡
በህገወጥ መልኩ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶችን አስመልክቶ በማስለቀቅ ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበው ለሚገኙ ዜጎች የማስተላለፍ ስራ እንዲሁም የቀበሌ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን በሚያሰፍን አግባብ እንዲፈፀም ይደረጋል ሲሉ ወ/ሮ አዳነች ገልፀዋል፡፡
ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመጨረሻም ከተማ አስተዳድሩ ችግሮችን ከስሩ በመንቀል ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን መልስ ለመስጠት እቅድ በማውጣት ግብረ ሃይል አቋቁሞ ሲመራ የቆየ ቢሆንም በየጀረጃው ህዝቡ ሲያደርግ የነበረው ድጋፍ፤ ሲሰጥ የነበረው ጥቆማ ለውጤታማነቱ ከፍተኛ ድርሻ የነበረው በመሆኑ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና የቸሩ ሲሆን በቀጣይም ስርአት አልበኝትንና በአቋራጭ መክበርን በመከላከል ፍትሀዊነትን ለማስፈን የከተማ መስተዳድሩ በቁርጠኝነት የጀመረውን ተግባር በማገዝ የከተማዋ ነዋሪ ከጎናችን እንዲቆም በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡››
አዲስ አበባ አሁንም በሂደት የርክክብ ስነ ስርዓት እየተካሄደባት የምትገኝ ከተማ ሆናለች፡፡
ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው
Filed in: Amharic