>

የመጣ የሄደው ሁሉ ከዝች ቤተክርስቲያን ላይ እጁን የማያነሳው ለምን ይሆን....??? (ኤልሳ. ከ)

የመጣ የሄደው ሁሉ ከዝች ቤተክርስቲያን ላይ እጁን የማያነሳው ለምን ይሆን….???

ኤልሳ. ከ

*….. የድፍረት ድፍረት ቤተክርስቲያን ግቢ ገብተዉ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አንስተዉ ትላንት የመጣ  የክልል ሊያዉም የድርጅት አርማ ሰቅለዋል…
 
< ይሄ የምትመለከቱት የሐረር ፊልጶስ ቤተክርስትያን ነዉ የሚገኘዉም በሐረር ጥምቀተ ባህር ዉስጥ ነዉ። በቤተክስትያኑ በዙርያዉ የምትመለከቱት ደግሞ የሐረሪ ብሄራዊ ክልል አርማ ነዉ። ይንን ፎቶ ያነሳሁት ራሴ ነኝ። በወቅቱ ደንግጫለሁ ዲያቆናቱን እና እዛዉ ያደሩ ምዕመናን አናግሬ ነበር ግን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ አንስቶ ይሄንን ቤተክርስትያኑ ላይ ማን እንደሰቀለዉ የሚግረኝ አጣሁ። አንድ አባት ብቻዬን ሰወራ ሰምተዉ ዉይ ይሄንን ነዉ አሉኝ በከዘራቸዉ እየጠቆሙኝ አዎን አልኳቸዉ ከማዘጋጃ ቤት ነዉ መጥተዉ ሰቅለዉ የሄዱት አሉኝ።የድፍረት ድፍረት ቤተክርስቲያን ግቢ ገብተዉ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አንስተዉ ትላንት የመጣ  የክልል ሊያዉም የድርጅት አርማ ሰቅለዋል።
ሐረሪ ክልል ላይ ባለፈዉ አመት የሆነዉን መቸም አንረሳም። የሐረርጌ ሐገረስብከት ሊቀጳጳስ የሆነዉን ሁሉ በሚዲያ ሲናገሩ ሰምተናል። ዳግም የክልሉ መንግስት እንዲበድለን አንፈልግም። የአምናዉ ይበቃናል ብለን ነበር። ነገር ግን ዘንድሮ ለጥምቀት የምትይዙት ሆነ ቤተክርስቲያን ላይ የምትሰቅሉት የክልሉን አርማ እና  የኢትዮጵያ ኮከብ ያለዉን ባንድራ ብቻ ነዉ ቲሸርትም አሳትማችሁ መልበስ አትችሉም ብለዉ ከወዲዉ ለቤተክርስቲያን እያስጠነቀቁ መሆናቸዉን ሰማዉ።
 የምትመለከቱት የቤተክርስቲያንን አርማ (ባለፈዉ አመት) የተያዘ በአሁኑ መያዝም ሆነ ቤተክርስቲያን ላይ መስቀል እንደማይቻል። ተነግሯቸዋል የቤተክርስቲያን አባትችች ግን እስከ አሁን ምላሽ አልሰጡም። ድሮ የሐይማኖት ነፃነት አለ ይባል ነበር ።አሁን በዘመነ ብልፅግና ደግሞ የሐረሩ ባለ ኃይማኖቱ መንግስት ዘንድሮ ብሶበታል። ጭቆናዉን ከወዲህ አብሶታል። መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም በሚል ህገመንስታቸዉ ላይ ያስቀመጡት ለይስሙላ መሆኑ ግልፅ ነዉ። በክልሉ ህዝብ በጀት እነሱ የሐይማኖት ስራ እንደማይሰሩበት ህገመንግስታቸዉ ይናገራል።
የሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት ታቀብ።የጥምቀት ቦታ ካርታ የሰጡት ድሮም ለይስሙላ ነዉ እንጂ አሁንም የጥፋቱ ዘመቻ አለ።
Filed in: Amharic