>

" ከተማ ውስጥ ያሉ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ሆን ተብሎ ታቅዶበት እያፈረሷቸው ነው...!!! " (ይድነቃቸው ከበደ)

” ከተማ ውስጥ ያሉ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ሆን ተብሎ ታቅዶበት እያፈረሷቸው ነው…!!! “

ይድነቃቸው ከበደ
  *  “የኦሮሚያ ብልፅግና የወታደር ካምፕ ልገነባ ነው ብሎ ቅርሱን አፍርሶ ፍርስራሹንም ወደ ውጪ አስወጥቶ ጥሎታል”
አቶ አበባው አያሌው የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር
 ቅርሱን ሆን ብለው አውድመው እና አፍርሰው ፍርስራሹንም ወደ ውጪ አውጥተው ጥለውታል። አርብ እለት ጣሪያ ማፍረስ ሲጀምሩ ወደ ቦታው ስንሔድ ወታደሮቹ አትገቡም ብለውናል። የኦሮሚያ ብልፅግና የወታደር ካምፕ ልገነባ ነው ብሎ አፍርሶታል። ጉዳዩ ወደ ቅርስ እና ጥበቃ፣ባህልና ቱሪዝም ሲደርስ በማሽን ተደብቀው እያፈረሱ የነበሩት እኛ ጆሮ መግባቱን ሲያውቁ በህብረት አፈረሱት” የወታደር ካምፕ መስራት ከፈለጉ ቅርሱን ሳያፈርሱ ከጎኑ ማስገንባት ይችሉ ነበር። ያም ሆነ ይህ እኛ ክስ እንመሰርታለን እስከ 25 አመት ያሳስራል–አቶ አበባው አያሌው ለሸገር ኤፍ ኤም ከተናገሩት
“ቅርሱ ሆን ተብሎ ታቅዶበት የፈረሰ ነው። እኛን ጨምሮ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሒሩት እንደሰማን ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ኦሮሚያ ብልፅግና ጋር ስንደውል ሆን ብለው ሁሉም ስልካቸውን አጥፍተዋል። ቀኑን ሙሉ ሚኒስትሯ ሲሯሯጡ ቢውሉ ምንም መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለን ቅርስ ሆን ብሎ አቅዶ ማፍረስ ጉዳዪ ሌላ ነገር ነው”በቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን የቋሚ ቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ዳይሬክተር  ወ/ሮ ሰላማዊት ለሸገር ኤፍ ኤም ከተናገሩት
የደጃዝማች አስፋው ከበደ መኖሪያ ቤት በቅርስነት ከተመዘገበ በርካታ አመታትን አስቆጥሯል።
Filed in: Amharic