>

በማንነታቸው ምክንያት የዘር ፍጅት ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን "አለን" እንበላቸው። (ክርስቲያን ታደለ)

“አለን…!

ክርስቲያን ታደለ

ርስቴንም ወስዶ ከአድባር ከቀየዬ እያፈናቀለኝ፣
ውስጡ የቀመለ የዘመን እንክርዳድ …
አዳራሹ ቤቴን ወሰደብኝና  ሰማይ አስጠለለኝ!
ሰማያዊ ጣሪያ፤
ሰማያዊ ጥበብ፤
ሰማያዊ ዙፋን፤
ሰማያዊ ኅብረት፤
የአያት ቅመአያቴ የመንፈስ ከፍታ ረቂቅ ምርምር፣
እንዲህ እንዳሁኑ ተፈጥሮ ሲዛባ ቅል ድንጋይ ሲሰብር።
አለው መላ መላ እያቀነቀኑ ሜዳ ላይ ቢጣሉም ተንጋለው ሚቀኙት፣
የአማራነት ቅኔ ሞተው የማይሞቱት ተኝተው ማይተኙት።
እኛው ለታረድነ ተከሳሽ ብንሆንም፣
በእኛው ኃዘን ድንኳን ገዳይ ቢሞሸርም፣
የተነሳን ለታ
እንኳን በቀናችን በመንፈቀ ሌሊት ጎህ መቅደዱ አይቀርም።
አለን አለን ብለን በአማራነት ክብር በአማራነት ኅብር የተሰባሰብን ለት፣
ገዳይን አያርገኝ  አርዶ ለሚፎክር ዋ ሁዬ ዋ ሁዬ ዋይ ለልስ ነው ማለት።
በማንነታቸው ምክንያት የዘር ፍጅት ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን አለን እንበላቸው። የፊታችን እሁድ ጥር 02/2013 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በዋሸንግተን ሰዓት አቆጣጠር 2:00 PM ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብሩ ይጀምራል። አላችሁ? እንግዲያውስ መኖራችንን ወዳጅም ሰምቶ ደስ ይበለው! ገዳይም ኅያውነታችንን ይወቅ!
Filed in: Amharic