>

የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ ... (ታጠቅ መ ዙርጋ)

የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ በቴሌፓቲ (telepathy)

 ታጠቅ መ ዙርጋ

 


በቅድሚያ የዚህ የቴሌፓቲ ቃለመጠይቅ (interview) ፈቃደኛ ሁነው፤ሰዓቱንም አክብሮ በመገኘቶ በራሴና በቴሌፓቲ ዜና አዘጋጆዎች ስም ላመሰግኖት እወዳለሁ።

አቶ መለስ ፥እኔም ይህ እድል ለሰጣችሁኝ የቴሌፓቲ ጋዜጠኞችን ላመሰግን እወዳለሁ።

ጥያቄ ፥ አቶ መለስ ልጅ እያሉ ቤተሰብዎት ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አንስተው ሲወያዩ ወይም ሲጫወቱ ይሰሙ ነበርን?

መልስ፥አው እሰማ ነበር።

ጥያቄ ፥ በቤተሰብዎት በተለይም በወላጆችዎ አመለካከት ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምን ትርጉም ነበር የሚሰጡት?

መልስ፥በቤተሰቤና በወላጆዎቼ አመለካከት ኢትዮጵያ ማለት የአማራ አገር፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት አማራነት ነው እያሉ ነበር የሚያወሩት።

ጥያቄ ፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህክምና ሳይንስ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንደነበሩ ከመስማት ሌላ ከዚያ በፊት የት የት እንደተማሩና የተማሪነትዎ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የምናውቀው ነገር ስለሌለ፤ ሊገልጹልን ፈቃደኛ ኖዎትን?

መልስ፥የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴ ያጠናቀኩት በንግሥት ሳባ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አደዋ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴ ያጠናቀኩት በጀነራል ዊንጌት ት/ቤትአዲስ አበባ ነው። የተማሪነቴ ዘመን ትልቁ ችግሬ ጓደኛ ማጣት ነበር።

ጥያቄ፥ለምን ጓደኛ ወይም ጓደኞች (peer groups)የማግኘት ችግር ገጠሞዎት?

መልስ፥የከሃዲ ቤተስብ፣የባንዳ ቤተሰብ፣ እየተባልኩ እገለል፣እሰደብ፣ኧናቅ ሰለነበረ፤ የተማሪነት ሕይወቴ፥ ምሬት፣ሃዘን፣ብስጭት፣ትካዜ ወዘተ የተሞላበት ነበር።

ጥያቄ፥ ከየትኛው የብሔረሰብ አባሎች ነበር የዚያን ዓይነት ስድብ የሚሰነዘርቦት?

መልስ-፤ በአብዛኛው ከአማራ ብሔረሰብ ሲሆኑ ጥቂት አማራይዘድ የሆኑ ትግሬዎችም ነበሩበት።

ጥያቄ፥ ወደ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራ  (ህወሓት) እንዲሄዱ የግፋፋዎት ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ናቸው ማለት ይቻላልን? 

መልስ፥ አው! በሚገባ!

ጥያቄ፥ የሕወሃት ዓላማ ምን ነበር?

መልስ፥ ከአማራ ነጻ  የሆነ  የትግራይ ፕብሊክ ለመመሥረት ነበር።

ጥያቄ፥ ከአማራ ነጻ  የሆነ የትግራይ ሪፕብሊክ (sovereign Tigraye) ለመመስረት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም ያገኛችሁት መቼ ነበር?

መልስ፥ የአውዜን ገበያተኞችን በደርግ አውሮፕላንካስደበደብን በኋላ ነበር።

ጥያቄ፥  እንዴት ንጹህ ገበያተኞችን በቦምብ መደብደብለሕወሓት ሃይል ለኢሆን ቻለ? እስቲ ያብራሩት?

መልስ፥ (1) የትግራይ ወጣቶችን ስሜት ስለቀሰቀ ቁጥሩ ማስተናገድ ከምንችለው በላይ ወጣት ወደ ሕወሃት ጎረፈ (2) ያንን እልቂት በቪዲዮ ቀርጸን የዓለም ሕዝብ እንዲያየው በማደረጋችን ከምእራባዊያን መንግሥታት በተለይ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ ከፍተኛ የመሣርያ፣የገንዘብ፣የቁሳቁስ፣የሞራል፣የስለላ ደጋፍ ወዘተ ስላስገኝልንና የውጊያ ሃይላችን እጅግ በጣም ከፍ በማለቱና በደርግ ሠራዊት ምርኮኞችስንጥለቀለቅነው ከአማራ የነጻ የትግራይ ሪፕብሊክ የመመሥረት አቅማችን ያወቅነው።

ጥያቄ፥ፖለቲካዊ ርዕዮታችሁ (ideology) ሶሻሊዝም (socialism) እንደነበረ፤ ጫካ እያላችሁ ያውም ሥልጣን ላይ ልትወጡ ሁለት ዓመት ሲቀራችሁለ(BBC)ጋዜጠኞች የምትከተሉት የአልባኒያን ሶሻሊዝም እንደሆነና የወቅቱ የአልባኒያ መሪ‘ኤንቨርዎዣንንም’ አድንቃችሁ ስታስረዱ አውስትራሊያ ሆኜ አዳመጥኩት። ታዲያ እንዴት እንግሊዝና አሜሪካ ከጎናችሁ ሊሰለፉላሁ ቻሉ?

መልስ፥ እንደዚህ የምትረዱን ከሆነ እናንተ የምትሉን ሁሉ እንፈጽማለን ብለን ቃል ገባንላቸው።

ጥያቄ፥ የወያኔ አባላት የደርግ ካድሬ በመሆን በርካታ የኢሕ አፓ አባላትገለዋል፣አስገድለዋል፣ አስጦቁሞዋል ወዘተ እየተባለ ይወራል፤ ለዚህ ምን መልስ አልዎት?

መልስ፥ ትክክልነው፤ ደርግ ባካሄዳቸው የገፍና የተናጥል ግዲያዎች ሁሉ የእኛ ስውር ሚና አሉበት። ከጀነራል ተፈሪ ባንቲ እስከ ስልሣዎቹ ጀነራሎች ግዲያ የእኛ ስውር ምክርና ቅስቀሳ አሉበት። መንግሥቱ ሊቀደም ነው፤ እነ-እገሌ ልያጠፉት ተዘጋጅቷል የሚል ወሬ ለመንግሥቱጆሮ እንዲደርስ በማድረግ።

ጥያቄ፥ የመንግሥቱን በሕይውት መቆየት ለምን መረጣችሁት?

መልስ፥ መንግሥቱ እጅግ በጣም አምባገነን፤በፖለቲካ ያልበሰለና በሕዝብ የማይወደድ ሰው ስለነበረ፤እሱን ማሸነፍ ከባድ እንደማይሆንእናምን ነበረ። የመንግሥቱ ቀድሞ መሞት የኢሕአፓ መጠናከር እንደሆነ እናውቅ ስለነበረ በጸረ ኢሕአፓ አቋም ከምንግሥቱ ጋር  በሥውር  ተሥማማን።

ጥያቄ፥ከእነዚያ ሁሉ ምሥራች የ(ሕወሓት) አባሎች እንዴት እርስዎ የወያኔዎች መሪ ሊሆኑ ቻሉ?

መልስ፥ የሕወሓት አመራሮች በእኔ ሥር ማድረግ ለእኔ ከባድ አልነበረም።ምክኒያቱም እነ-ሌኒን፣ እስታሊን፣ ማዎ፣ ሂትለር፣ ጀነራል ፍራንኮ ወዘተ ሥልጣን ለመጨበጥ የተጠቀሙባቸው ስልትዎች አዘውትሬ በጥንቃቄ አንብ ነበርና።

ጥያቄ፥ የሕወሓት መሪ ለመሆን ከተጠቀሙባቸው ሥልቶች አንዱን ወይም ጥቂቶቹን ሊጠቅሱልን ይችላሉን?

መልስ፥ (1) እያንዳንዳቸውን የፖለቲካ ብስለት፣ጥንካሬ፣ድክመትና ለሥጣን ያላቸው ምኞት ወይም ጉጉት ተከታትዬ አጠናሁ (2) ማርክሲስት-ሌኒኒስት የጥናት ቡድን ወይም ክንፍ መሥርቼ ደጋፊዮቼን አጠናከርኩ (3) ለሥልጣን  የሚያሰጉኝን  መርዮች ደካማ ጎን እያጋነንኩ ለሕወሓት አመራር ብቁ እንዳልሆኑ ሥውር ቅስቀሳበማድረግና በማስደረግ በአስቾካይ በሞት እንዲቀጡ ወይም ከሕወሓት እንዲወገዱ እያደረኩ ደካሞችን ሁሉበቁጥጥሬ ሥር አዋልኳቸው።

ጥያቄ፥ የ(ሕወሓት) አባል ከመሆኖ በፊትም ሆነ ከሆኑም በኋላ ኢትየጵያን እገዛታለሁ የሚል ምኞት ኖርዎት ያውቃሉን?

መልስ፥ አው፤ በኅልሜም በውኔም ያቺ አገር የመግዛት ምኞት ነበረኝ።

ጥያቄ፥ለምን ?የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብ ለመቀየር? ኢትዮጵያን ለማሳደግ? ከስልጣን የሚገኝ ምቾትና ዝና ከመፈለግ አኳያ?

መልስ፥የዚህ መልስ ሁልትም ሦሥትም አይደለም። መልሱ አንድ ነው፤ ዋናው ምኞቴ ያቺን አገር እየገዛኋት ብትንትኗን ለማውጣት ነበር።

ጥያቄ፥ ያቺን አገር ለማፍረስ ያወጥዋቸው ዕቅዶች ምን ምን ነበሩ?

መልስ (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 1)፥ በአማራ ሥርወ መንግሥታት የሰለጠኑትንየቀድሞቹ ፡ የምድር ጦር፣ የፖሊስ ሠራዊት ፣ የባህር ኃይል፣ የደኅንነት/የፀጥታ ኃይል፣ የመሣርያ ግምጃ ቤቶች ወዘተ በቁጥጥር ሥር ማዋልና መደምሰስ፤

መልስ (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 2)-: ከላይ የተጠቀሱትን ተቋማት፣ የከፍተኛ ትምህርት (የዩኒቨርስቲዮችና የኮሌጆች) ተቋማት(institutions)ማፍረስ ፤ 

መልስ (ያጭር ጊዜ ዕቅድቁጥር 3)፥ ከላይየጠቀስኩትን የምድር ጦር፤ የአየር ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የደኅንነት፣ የከፍተኛ ትምህርት ኃይሎችና ተቋማት ለትግራይ ነጻነት በተዋጉና በትግርኛ ተናጋሪ ኃይሎች መተካት፤

መልስ (ያጭር ጊዜ ዕድቅ ቁጥር 4)፥ በሥልጣን ላይ ለመረጋጋት እንቅፋት ይሆኑብናል የምነላቸውን መመንጠር፤

መልስ (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 5)፥ በእኛ እምነት ያቺ አገር የመቶ ዓመታት ታሪክ ብቻ ያላት ስለሆነች ያንን ማስተማርና መጻፍ።በእኛ እምነት የዚያች አገር ባንድራ (እናንተ ሰንደቃዓላማ) የምትልዋት ጨርቅ  መሆኑንማስተማርና በ (ሕወሓት) ወርቃማ ባንድራ መተካት።

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 1)፥ ትግራይን ከሚያጎራብቱ ክፍለ ሃገራት ለም የሆኑትን መሬት ወስደን ወደ ትግራይ በማጠጋጋት ትግራይን አንድ ትልቅ ረፕብሊክ ማድረግና ማበልጸግ፤

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 2)፥ምጽዋና  አሰብ  ጨምሮ  ኤርትራነጻ አገር  እንድትሆን  መደገፍ፣ 

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 3)፥  የጦር መሣርያዎችን፣ የጤፍ፣የገብስ፣ የኑግ፣ የሠሊጥ ምርታ ምርቶችን በመስጠት፤የገንዘብ ካሳ በመክፈልናየቡና ምርት ወደ ውጭ ገበያ እንዲልኩ (export) እንዲያደርጉ በማድረግ ኤርትራን ማጠናከር፤

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 4)፥በጎሳ ቋንቋ የተዋቀረ ክልላዊ አስተዳደር በመፍጠርና እርስ በርሱን በማናከስ (by creating Bantustanization)የዚያችን አገር ዳርድንበር፣አንድነትና ማኅበራዊ ባህሉን (social culture)ማፈራረስና ማናጋት፤

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 5)፥የዚያች አገር የምጣኔ ሃብት (economy) እና የንግድ ዘርፍ በኤፈርት፣ በትግራይና በኤትራ ተወላጆጅችንእጅ እንዲገባ ማደረግ፤

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 6)፥ ከዚያች አገር መሬትቆርሰን ለባለውለታችን ለሱዳን  በመስጠት  የመልካ   ምድርግዛትዋ እንድታስፋፋ ማድረግ፤

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 7)፥ ትግሬዎችን በገፍወደ፥ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውሮፓ፣ እስካንዳናቪያ አገሮች ልኮ በማስተማር የነገውን የዚያችን አገር ሕዝብ  የአገዛዝና  የእውቀት  ሞተር ማድረግ። ያ  ካልተሳካ  የትግራይ  ሪፐብሊክ  መስርተን ዞር  ማለት ፤ 

መልስ (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 8)፥ ከዩኒቨርስቲ እስከ አንደኛ ደረጃ ያሉትን የዚያች አገር የትምህርትና የመምህራን ጥራት ዝቅ ማድረግ፤ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቭርስቲ ያሉትን የሃገረ ትግራይ ትምህርት ቤቶችየትምህርትና የመምህራን ጥራት ካደጉ አገሮች የትምህርትና የመምህራን ጥራትጋርተመጣጣኝ ማድረግ ወዘተ ።

ጥያቄ፥ ከላይ የተጠቀሱትን ያቺን አገር የማጥፋት ዕቅዶችን ያረቀቁና አሁንም በሕወሓት አመራር ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙት፤ እርስዎንም ጨምሮ- በወንድ አያታቸው ወይም በአባታቸውወይም በእናታቸው አባት በኩል ጣልያንን ወግነው ኢትዮጵያን የወጉ (የባንዳ ኤርትራውያን ቤተስብ) ስለመሆናው ነዋሪነታቸው አውስትራሊያ የሆነው አቶ ገብረመድህን አርአያ መስክሮዋል። ይህመሰረተቢስ ክስ (allegation) ነውን ውይስ እውነትነት ያለው ክስ ነው?

መልስ፥ ገ/መድህን አርአያ እውነቱ ነው፤ ከአሁን በኋላ እኔ በደብቀው ታሪክ ፀሐፊዮዎች ስለሚያጋልጡትና የምድር ላይ ውሸቶቼንም ባለሁበት በሰማይ ቤት ክፉኛ እያሰቃዩኝ ስለሆነ ከአሁን በኋላ ላለመዋሽት ወስኜአለሁ።

ጥያቄ፥የኤርትራዊነት ዝርያ ያለባቸውን በበትረ መንግሥትዎ ወሳኝ ወሳኝ በሆኑ የሥልጣን ተዋረዶች ያስቀመጡበት ምክንያት ምንድነው?

መልስ፥ (1) አማራ ኤርትራውያንን በቅኝ እንደገዛቸውሁሉ ኤርትራውያን በተራቸው በአማራ ላይ የጅ አዙር ቅኝ  ገዢ  (indirect colonizers) ለማድረግ (2) ባባትም በእናትም የኤርትራዊነት ዝርያ ከሌለባቸው ከሕወሓት መሪዮዎችና ከወያኔ አባላት ከሚቃጣብኝን ጥቃት እንዲጠበቁኝ ቃልስለገቡልኝና የበለጠም ስለማምን ናቸው ።

ጥያቄ፥ ለምን ነበር ያባትዎን አገር (ያቺን አገር) እያዳከሙ የእናትዎን አገር ኤርትራና የጎረቤት አገር ሱዳንን ማጥናከር የመረጡት?

መልስ፥ በአጭሩ ሁለቱም- ለደረስኩበት የሥልጣን ምንጭ ወይም መሠረት ስለሆኑ ወለታቸውን መክፈል ነበረብኝ።

ጥያቄ፥ ዓለም በጎሣ፣ በብሄር፣በብሄረሰብ፣በእምነት፣በርዕዮት ወዘተከተከፋለበት ታሪካዊ ወቅት አሁን እስከ ደረስንበት ታሪካዊ ወቅት አንድመሪ የሚገዛውን አገር ለማስፋፋት ሲጥር እንጂ-የዚያን አገርየባህር በርና ዳርድንብር ለባዕዳን ያቀራምት ወይም አሳልፎ የሰጠ መሪ ‘እርስዎ ብቻኖዎት’ ይባላል። ይህንን እንዴት ያዩታል?

መልስ፥ (1) አዎን ጥሩ ታሪክ ያላቸው መሪዎች እንዳሉ ሁሉ መጥፎ ታሪክ ያላቸው መሪዎችአሉ። ይህንን ጠንንቅቄ አውቃለሁ (2)እኔ ቁጭቴን ተወጥቼ እንደዚህ ለየት ያለ (unique)ታሪክ እንዲኖረኝ ነው የፈለኩት(3)ማስደሰት የፈለኩት ያቺን አገር የሚጠሉትን የከበርቴምዕራባውያን መንግሥታት እና አረብዎችን ነው ። ታርኬም አሳምሮ፣ አድንቀውና አጀግንነው የሚጽፉት እነዚሁ ሃይሎች ናቸው (4) የእኔ ታሪክ የዝያች አገር ሕዝብ ምኑም ስላልሆነበፈለጉት መልክ አጨማልቀው ቢጽፉት ግድየለኝም።

ጥያቄ፥ ከትግራይ ሪፕብሊክ አልፋችሁ ኢትዮጵያን መግዛት የሚያስችላችሁን ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ያወቃችሁት መቼ ነበር? 

መልስ፥ (1) በዋናነት የኢሕአፓ ከአሲምባ መውጣትና የመዋጋት አቅሙን መዳከም (2) የስልሣ ጀነራሎች መገደል (3) የደርግ ሠራዊት የመዋጋት ችሎታ ከግዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መሄድ (4) የምእራቡን የከበርቴ መንግሥታት በተለይም እነ-አሜሪካና እንግሊዝ  ከጎናችን መሰለፍ (5) የመንግሥቱ ኃይለማርያም አጋር የነበረው ረሺያ ከእነ-ጭፍሮቹ ከነበሩበት የኃይል ሚዛን መውደቅ፤ ወደ አዲስ አበባ የመገስገስ   መንገዳችን ጨርቅ አደረገልን። 

ጥያቄ፥ ጠቅላላውን ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ወደ አዲስ አበባ በመገስገሱ ላይ አብዛኛውን የሕወሓት ሠራዊት ስላልተስማማ በመካከላችሁ ጭቅጭቅ ተከስቶ ነበር ይባላል፤  ይህንን ሊያብራሩልንይችላሉን?

መልስ፥አዎን በእኔ ሥር የሚመራውየሕወሓት አመራር አጀንዳና የሕወሓት ሠራዊት አጀንዳ እየብቻ ነበር።የሕወሓት ሠራዊት የተዋጋው ትግራይን ከአማራ አገዛዝ ነጻ ማውጣት በሚል ነበር።ስለሆነም ሠራዊቱ ትግራይን ነጻ አውጥተናልና ከዚህ ማለፍ የለብንም ብሎ ተምሟገተን። አማራ ለረዥም ዓመታት ስለገዛን ተራችን እንግዛቸው በሚል ስላሳመናቸው ወድ አ/.አ በመገስገሱ ላይ ተስማማን።

ጥያቄ፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዲግ) እንድታዋቅሩ የመከርዋችሁ አሜሪካኖችናእንግሊዞች ናቸው ይባላል፤ ይህ አባባል ምንያህል እውነትነት አለው?

መልስ፥ እውነት ነው፤ የእነሱ ምክር የሌለበት አንዳችም ነገር አልሠራንም። በዚያች አገር ሕዝብ የተሻለ ተቀባይነት እንዲኖራችሁ ኢሓአዲግ (EPRDF) አዋቅሩ ብለው መከሩን።

ጥያቄ፥ የአጼ ኃይለሥላሤና የዳግማዊ ምኒሊክ ቤተመንግሥት  ምቾት እንዴት ነበር?

መልስ፥ ምንም አይሉም፤ በተለይም ለጫት መቃሜያና በተቃዋሚዮቻችን ላይ ለማሴር። አዜበ ግን እጅግ በጣም ወዳቸው እስከ እለተሞታችንን መልቀቅ የለብንም ብላ ትሟገት ነበር።

ጥያቄ፥ያቺን የሚጠሏት አገር ለሃያ አንድ ዓመታትያህል እገዛታልሁ የሚል ምኞትና ዕቅድ ነበሮትን?

መልስ፥ እውነቱን መናገር ካስፈለገ ለፕሮፓጋንዳ  መቶ  ዓመት  ልበል  እንጂ ከአምስት ዓመት በላይ ያቺን አገር እገዛታለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር።

ጥያቄ፥ ታዲያ ለሃያ አንድ ዓመታት ለመግዛት ያስቻልዎት ጥበብ ምንድነው?

መልስ፥(1) የጠመንጃ አፈሙዝ (2) ካድሬዮችን በብዛት አሰልጥነን አንድ ካድሬ አምሥት ሰዎች እንዲመለምልና እንዲሰልል በማሰለፍ (3)ኦሮሞችን በአማራው ላይ በማስነሳትና የዚያች አገር ሕዝብ በቋንቋና በጎሳ በማካለል(4) ወህኔ ቤቶችን በማስፋፋት (5)አሜሪካን፣እንግሊዝን፣የአውሮፓንና የእስካንዳናቪያንከበርቴአገሮችመንግሥታት ከጎናችን በማሰለፍ (6)ቻይናን እንደ አማራጭ ኃይል ከጎናችንበማሰለፍ (7) በጥትቅም ሆነ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ጠንካራ ተቃዋሚ ስላልገጠመን የስልጣን ዘመኔ አልጋ ባልጋ ሆነልኝ። 

ጥያቄ፥ መተክልዎ (principle) የጠመንጃ አፈሙዝ ሥልጣን ከነበረ፤ ለምን ለዲሞክራሲ ጥብቅና የቆሙ መስለዎ ይለፍፉነበር?

መልስ፥ (1) ዶላር (dollar) በገፍ ለሚሰጡኝ የከበርቴ አገሮች መንግሥታት ለማታለል (2) ዲሞክራሲ!! ስል ሥልጣኔን የማይነካ/ኩ ዲሞክራሲ ማለቴ ነው ፤ ለምሳሌ የእኔ በትረ-መንግሥት የማይቃወሙና በሥውር እኔን የሚደግፉ ተቃዋሚዮችን ማቋቋም፣ መጠጣት፣መጨፈር፣ ጫት መቃም፣ የራቁት ዳንስ ቤቶች መክፈት፣ የወንድና የሴት ግብረሰዶሞች ከተለያዩ አገርች ወደ እዚያች አገር እንዲጎርፉበመፍቀድ የማይጠይቅና  ሞራል  የሌለው  ትውልድ በመፍጠር ወዘተ.. 

ጥያቄ፥ እስከ ብሔራዊ ምርጫ 1997 ባለው ጊዜ፤ ሥልጣን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዮዎች በምርጫ እንዳይሳተፉ መንገድ ዘግተዋል ወዘተ እየተባሉ ሲወቀሱና ሲከሰሱ፤ የእርሰዎ መልስ ጠንካራ ተቃዋሚ ስላጣሁ ነው፤ ለማን ላስረክብ የሚል ነበር። ታዲያ በ 97ቱብሔራዊ ምርጫ ሲሸነፉ ለምን የመንግሥትዎ ሥልጣን ለአሸናፊው ፓርቲ አለቀቁም?

መልስ፥ (1) ከላይ እንደጠቀስኩት በሥልጣን ላይ እንድቆይ ለረዱኝ በከበርቴ አገሮች መንግሥታት ዘንድ ዲሞክራት መሪ ለመምሰል ነበር ስለዲሞክራሲ እለፍፍ የነበረው (2) እሸነፋለሁ ብዬ ጭራስ አልጠበኩም ነበር (3) አዜብ ሥልጣን አስረክበህ ከዚህ ግቢ ከወጣን አብረንም አንተኛም፤ እንደውም እፈታሃለሁ አለችኝ (4) የከበርቴ አገሮች መንግሥታትበተለይም ቶኒ ብሌርና ጆርጅ ቡሽ ሥልጣን ላይ እንድቆይ ፈለጉ

ጥያቄ፥ ያንን የሕዝብ ሥልጣን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን፥ ሽማግሌዎችን፣ አሮጊቶችን፣አዛውንቶችን፣ ለጋ ወጣቶችና ሕጻናትን በእርስዎ ተዛዝ በልዩ ገዳይ ሃይል (squad)በአጋዚያን ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ ሲጨፈጭፉ፤ እርስዎ በሸራተን ሆቴል ሴት ልጆዎን አቅፈው ልደትዋን ሲያከብሩ እንደነበረተዘግቦዋል። ይህ ዜና ያፀድቁታል ወይስ ይክዱታል?

መልስ፥ (1) ካሜራ የያዘው ነገር ለመካድ ስለሚያስቸግር ዜናውን አፀደኩት ማለት እውነተኛ ዜና ነው (2) የዚያች አገር ሕዝብ እንኳን ሁለት መቶ-በሚሊዮንምቢሞት ግድየለኝም።

ጥያቄ፥ እ.አ.አ ግንቦት 18/2012 በተርመንት ሜሪላንድ (Thurmont,Maryland,USA) በኢንዱስትሪ ባደጉት ስምንት (G8) አገሮች ስብሰባ ንግግር በማድረግ ላይ እያሉ ጋዜጠኛ አቶ አበበ ገላው “ መለስ አምባገነን!!!፣ ከልማት በፊት፣ ከምግብ በፊት ዲሞክራሲ፣ መለስ አምባገነን!!!” በማለት እንድመብረቅ ሲጮሁብዎት፤ ለምን ነበር ያን ያህል የደነገጡት?

መልስ፥ (1) ያንን ያህል በሚያደንቁኝና በሚያከብሩኝ ታላላቅ የዓለም መሪዮች ፊት እንደዚያ በመደፈሬና ተክለሰውነቴ በመገፈፉ ነበር እጅግ በጣም የደነገጥኩት።

ጥያቄ፥ ከዚያ ክስተት በኋላ ለተወሰኑ ሣምንታት አደባባይ ላይ ካል መታየትዎም ሌላ ጭልፊት እንዳስደነገጣት ጫጩት ወይም ተቅማጥ እንደለቀቅበት ስው ኮስስዎ ወደ አደባባይ ብቅ አሉ።ድንጋጤውን ነው እንደዚያ ያደረጎት ወይስ ሌላ ችግር ነበረቦዎት?

መልስ፥ (1) አው በድንጋጤው ምክንያት ለሁለት ሣምንታት ያህል በተቅማጥ ተሰቃየሁ (2) ድንጋጤው ጽኑ አእምሮ መረበሽ (acute depressive or major depressive disorder-MDD) ስላደረሰብኝ ቀድሞ ከነበረብኝ አእምሮ በሽታዬ ጋር ተደማምሮ ለሞት አበቁኝ።

ጥያቄ፥ በ57ዕድሜዎ አሁን ወደ አሉበት ዓልም ባይሄዱኖሮ ያቺን አገር ምንያህል ተጨማሪ ዓመታት ሊገዝዋትያስቡ ነበር?

መልስ፥ (1)ዕድሜ እንደሙጋቤ ቢረዝም ኖሮ ያንን ያህል (80-90) አመታት እየገዛኋትና እየቸረቸርኩ ላጠፋትና ከጎን የትግራይ ሪፕብሊክ ለመመሥረት ዕቅድ ነበረኝ።

ጥያቄ፥ በእርስዎ ሰም የተቀመጠ $3.5 ቢሊየን ዶላር፣ በልጆዎ እስማሃል መለስ ስም የተቀመጠ $5.00 ቢሊየን ዶላር ተገኝቶ የዓለም ሕዝብ መወያያ ሆኖዋል።ባለቤትዎ አዜብ ግን የባለቤቴ የመለስ የወር ደሞዝ $4000 ብር ብቻ ነበር በማለት ይሟገታሉ። ይህንን እንዴት ያዩታል?

መልስ፥ ጉድ ሆንኳ! በዘመኑ ታላላቅ መሪዮዎች ያንን ያህል የተከበረውንስሜ ጠፍቷላ!  በሕይወት እያለሁበጠመንጃ ሃይል ለረዥም ጊዜ የተገዛ ሕዝብና በቅኝ ግዛት ሥር የዋለ ሕዝብ አእምሮ (mind) ከሰውኛ ባሕሪ ወደ እንሰሳኛ ባሕሪ ስለሚቀየር የሚነገረውን ሁሉ ይቀበላልእያልኩ እነግራት ስለነበረ፤ አዜብ ያንንነው ያንጸባረቀችው።  

ጥያቄ፥ በርግጥም አስክሬንዎ በአዲስ አበባ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ተቀብሯልን?

መልስ፥ ሞኛችሁን ፈልጉ፤ ነገ ወያኔ ሲወድቅ አስክሬኔ ከመቃብሬ አውጥታችሁ ለጅብ ልትሰጡ? የሬሳዬ ሣጥን ብቻ ነው አዲስ አበባ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የተቀበረው ቴናዚዤ ስለነበረ እውነተኛ አስክሬኔ የተቀበርው አደዋ ው ።

?ጥያቄ፥ አሁን ያሉበት ዓለም ሕይወት ምን ይመስላል?

መልስ፥ ምቾት በዚያች አገር ቤተመንግሥት ቀረ። እዚህ ከማንም ተራ ሰው ነፍስ (soul) ጋር መተራመስ ነው። ልክ ከርቸሌ ውስጥ እንደ መኖር ማለት ነው። ለሊት ለሊት አጋንንቶች እየወሰዱ በምድር ላይ የሠራኸውን ተናገር እያሉ ይገርፉኛል። ያሰቃዩኛል። ከሞት በኋላ (life after death) ገሃነምና መንግሥተሰማይ የሚባል ነገር የልም የሚለውን የሶሻሊዝም ፍልስፍናን (socialism philosophy)                  ተከቲዬ የፈጸምኳቸውን ግፎች አድነው እያሰቃዩኝ ነው ። ነፍሴ የመጨረሻውን ፍርዱን እየጠበቀ ነው። እስካሁን እየተነገረኝ ያለው ነፍሴ  እነ-ሂትለርና እስታሊን  ያሉበት የዳቦ መጋገሬያ ዓይነት ምድጃ (furnace) ውስጥእንደሚቀመጥ ነው።

ጥያቄ፥ ከርሰዎ ሞት በኋላ ስለሆኑትን ሁኔታዎች ጥያቄ አልዎት?  አው አሉኝ። 

የአቶ መለስ ጥያቄ ፥ የቀብሬ ስነሥራዓት እንዴት ነበር?

መልስ፥ ግሩም ድንቅ የቀበር ሥነሥራዓት ተደርጎልዎታል። የቀረ የዓለም መሪ አልነበረም።በግድም በውድም እንካንስ ጤነኛውን ፣ አንካሣውም፣ዓይነ-ሥውሩም፣ በሁሉም የአገራችን ሆስፒታሎች የሚገኙትን ታማሚዮችን፣ የጎዳና ተተዳዳሪዮችን ወዘተ ተሰለፈሎት፤አለቀሰሎት።

የአቶ መለስ ጥያቄ፥ ማን ነው እኔን የተካው ጠቅላይ ሚኒስተር?

መልስ፥ እርስዎን የተካውአቶ ኃለማርያም ደሳለኝ ነው።

ጥያቄ፥ በዚህ ላይ የሚያክሉት ነገር አለዎትን?

የአቶ መለስ መልስ፥ የአቶ ኃለማርያም ጠቅላይ ሚንስተር መሆን እጅግ በጣም አስደስቶኛል። ምክንያቱም ለወያኔዎች ፍጹም ታዛዥ ነውና። 

የአቶ መለስ ጥያቄ፥ አዜብ ከእኔ ሞት በኋላ በምን ሁኔታነው ያለችው?

መልስ፥አዜብ በብስጭት ራሷን ገላ ወደ እርሰዎ ሣትመጣ አትቀርም። ምክንያቱም (1) ያለውዴታዋ በግድ ከቤተመንግሥት አስወጧት (2) ከኤፈርት ዳይሬክተርነት ተወግዳ በምትካው ከእርሰዎ በፊት ወዳጅዋ የነበረው  የነበረው አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም (ብርሃነ ማርት) ተሾመ (3) በሙስና ክስ ሊመሰርትባቸው እየታሰበ ነው።

ጥያቄ፥ሰዎች ሲሳሳቱ፣ የተመኙትን፣ ያለሙትን፣ያቀዱትን ወዘተ ሣያሳኩ፤ እርጅና ሲደርስባቸው፣ አደጋ ሲያገጥማቸው፣ ታመው ሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ አንጻራዊ ፀፀት አላቸው። እርስዎ ታመው እንደማይድኑ ሲያውቁ ዋንኛና ትልቁ ጸጸት ዎምን ነበር? 

መልስ፥ ያቺን አገር ሱማሌያን ወይም አፍጋኒስታን ሳላስመስላት በሞት መቀደሜ ነው ትልቁን ፀፀቴ።

ጥያቄ፥ ለሕወሓት መሪዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት አልዎትን?

መልስ፥ አው አለኝ፥ (1) ጓዶቼ! በርግጥ የምትውዱኛና ነፍሴን ማስደሰት ከፈለጋችሁ ያቺን አገር ሱማሌ ወይም አፍጋኒስታን ሳታስመስሏት ሥልጣን እንዳትለቁ (2) የአዜብ ነገር አደራችሁ (3) ሓወልቴን በዚያች አገር መዲና በ (አ.አ) እንዳትተክሉ፤ በፍላጎትም ሆነ በግድ እናንተ ሥልጣን ለቃችሁ በአማራ ሲተካ በመዶሻና በዶማ ያፈራርሱታል። የእኔን ሓውልት ለዚያች አገር ሕዝብ ምኑም አይደለም፤ ስለሆነም ሓውልቴ በመቀሌና በአደዋ ትከሉልኝ።

የጋዜጠኛው ስንብት፥ ለትብብሮ እያመስገንን በሚቀጥለው የቴሌፓቴ (telepathy) ቃለመጠይቅ (interview) እስክንገናኝ ነፍሶ (soul) በደህና ይሰንብት።

 

የቴሌፓቲ ትርጉም ለማያውቁ ፦

  • ቴሌ (ከሩቅ)፣ ፓቲ (ሃሳብ)
  • በሁለት ሩቅ ለሩቅ ባሉት ወይም በሚገኙት ሰዎች መካከል “ሃሳብ ለሃሳብ ተወንጫፊነት ወይም ተምዘግዛጊነት በአእምሮ ኃይል” የሚደረግ ግንኙነት ማለት ነው። የቴሌፓቲ ግንኙነት (communication) የሚተኮነው ወይም የሚከናወነው በሁለት በጣም በሚነፋፈቁ ወይም በጣም በሚጥላሉ ሰዎች መካከል ነው።ቴሌፓቲ ከሁሉንም ዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች ማለት፥ ድረገጽ፣ኢሜል፣ ሥልክ፣ የእጅ ስልክ/ሞባይል፣ ቴሌግራም፣ ስካይፕ፣ሳንዳሥ፣ሳናሸት ፣ሳንተያይ ወዘተርፈ  የሚደረግ ግንኙነት ነው።
  • Telepathy-the ancient Greek word.
  • Tele (distant),pathe (perception)
  • Telepathy-the communication of ideas and thoughts directly from one person`s mind or psychic power to another person`s mind or psychic power without the use of modern communication systems or without hearing,touching,seeing etc..sensory organs

ይህ ተረት ተረት አይደልም።እውነት በእውነት የሆነ ነውና በጥንቃቄ አንብቡት።

Filed in: Amharic