>

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት [ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም- ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ]

embassy_gunman1413593902እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩበጠረጴዛውይይት እናየሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀንዜጎች ደም ላይ ተረማምዶየጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይልበህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘውየሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እናአረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደርከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስትደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያቡድን ነው፡፡

በዚህች ትችቴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እያራመደ ያለውን የሀገር ውስጥየዲፕሎማሲፖሊሲለመቃኘት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ትኩረት በማድረግ ለመዳሰስ የምሞክረውህዝባዊ ወያኔ ሀርነትትግራይ የተባለውየወሮበላ ስብስብ ቡድን በማራመድ ላይ ያለውን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ፖሊሲንለመቃኘት ነው፡፡ በቅርቡ በአሜሪካየኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ አረመኒያዊ እና ግልብ መንፈስየተጠናወተው አንድ የጦር መሳሪያ ታጥቆኢትዮጵያውያን/ት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ተኩሶ ለመግደልበርካታ ጥይቶችን ሲተኩስ የነበረውን እና ለግድያሀራራውሳይሳካለት የቀረውን የወያኔ ወኪል ለመግለጽየወሮበላ ዲፕሎማሲ እና የወሮበላዲፕሎማት የሚሉትን ቃላትእጠቀማለሁ፡፡

እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል አገላለጽ ‘ባለጠመንጃው ሰው’ እየተባለ ይጠራ የነበረው በአሜሪካየኢትዮጵያኤምባሲቅጥር ግቢ ውስጥ እንደጅብራ ተገትሮ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውንለማቅረብ ወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሄዱትበንጹሀን ኢትዮጵያዊያን/ት ዜጎች ላይ ሲተኩስየነበረው በስም ሰሎሞንታደሰ ገብረስላሴ የተባለው የወያኔ ባለሙሉስልጣን የደህንነት አታሼነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር29/2014 የተደረገው የሰሎሞን ገብረስላሴ አስደንጋጩእናአሳፋሪው የእሩምታ ተኩስ ጉዳይ በዓለምአቀፉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮበክብር እና ሞገስሳይሆን በቅሌት እና በውርደት፣በጥበበኛነት እና በምሁርነት ሳይሆንበጅላጅልነት እና በደንቆሮነት፣ በታጋሽነት እናበአርቆ አስተዋይነትሳይሆን በግልፍተኝነት እናበቅርብ አሳቢነት ሲታወስ ይኖራል፡፡

እንደ ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ “የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ቃል አቀባይ ከቀኑበ12፡15ሰዓትበሰሜናዊ ምዕራብ ዋሺንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ ተኩስእንደተሰማ ፖሊስበስፍራው በመገኘት ተኳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ እስርቤት ልኮታል፡፡ የዓይንእማኞች እንደገለጹት ከሆነየጥይት ተኩሱ የተከናወነው ሰላማዊተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢበተጠጉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥርግቢ ውስጥ ነውብለዋል…“

የወያኔን ኤምባሲ መውረር” 

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች የተወሰዱ በርካታ የቪዲዮ ክሊፖች እንደሚያስረዱት እና የኢትዮጵያሳቴላይትቴሌቪዥን/ኢሳትአገልግሎት እንዳመለከተው በቅርቡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን እናበጋምቤላ ክልሎች በወያኔገዥ አካል ታጣቂዎች በንጹሀንዜጎች ላይ የተወሰደውን አረመኒያዊጭፍጨፋ እና ግድያ በማስመልከትበኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘትተቃውሟቸውንለመግለጽ እና የወያኔው አምባሳደር ከሆኑትከአቶ ግርማ ብሩ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ የፊት ለፊትውይይትለማድረግ በሄዱት የሰላማዊ ተቃዋሚ ቡድንግለሰቦች ጥያቄ ማቅረብ ምክንያት ነበር፡፡

አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ ከወሰደው የቪዲዮ ክሊፕ እንደሚታየው ሰላማዊተቃዋሚዎችበመጀመሪያወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ለመግባት ሲያደርጉ የነበረውን ሁኔታ በግልጽያመለክታል፡፡የተወሰደው የቪዲዮ ምስልየተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ቅጥር ግቢበመግባት በግቢውውስጥ ባለ መቀመጫ ቦታ ላይ የደረሱመሆናቸውን ያሳያል፡፡ የኤምባሲውሰራተኞች ለደህንነት ተብሎከታጠረው መስታወት በስተጀርባ ሆነው በመመልከትላይ ነበሩ፡፡ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አምባሳደሩንማነጋጋር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በርካታዎቹ ሰላማዊተቃዋሚዎችድምጻቸውን ከፍ በማድረግጩኸት በማሰማት መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡ከመካከላቸው አንዱ እንዲህ ሲልተደምጧል፣ “ይህየወያኔ ኤምባሲ እንጂ የኢትዮጵያ ኤምባሲአይደለም፡፡“ ሌላኛው ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህየሚልጥያቄ አቀረበ፣ “ከአቶ ግርማ ብሩ(ከወያኔው አምባሳደር) ጋር ለመነጋገር እንፈልጋለን፡፡ ከእርሳቸውጋርስለኦጋዴን፣ ጋምቤላ እናስለአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መወያየት እንፈልጋለን፡፡“ ሌሎች ሰላማዊተቃዋሚዎችደግሞየአንዳርጋቸው ጽጌ (ከጥቂት ወራት በፊት በወያኔ ገዥ አካል ከየመን ተጠልፈው ወደኢትዮጵያከተወሰዱትየግንቦት 7 የአመራር አባል) ምስል ያለበትን ቲሸርት በመልበስ እርሳቸውከእስርእንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሌላ አንድሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣“እስክንድርነጋ (በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው እና  በወያኔገዥ አካል የ18ዓመታትእስራት ተበይኖበት በአሁኑጊዜ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት በመማቀቅ ላይየሚገኘው)ጋዜጠኛ ይፈታ“ ሌላው ማንነቱበውል ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ጨኸትሲያሰማ ነበር፣“በጎሳ ክፍፍል አገዛዝ ታመናል፣እናም ሰልችቶናል“ በግልጽ እንዲህ የሚል ጥያቄአቅርቦ ነበር፣ “በእንደዚህ ያለ ወሮበላአገዛዝ እስከ መቸድረስ ነው ስንገዛ የምንኖረው? እኛታመናል፣ እናም በዘራፊዎች እና በወሮበሎች መገዛትሰልችቶናል!“

በኢሳት የተወሰደ የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው ሁሉም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙት ነገሮችሁሉከኤምባሲው ቅጥርግቢ የተከናወኑ መሆናቸውን ነው፡፡ ከአራት ሰላማዊ አመጸኞች መካከልአንደኛውየኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የያዘ ሲሆንጥቁር ልብስ ወደ ለበሰው እና መሳሪያወደታጠቀው ገብረስላሴየሚባል የኤምባሲው አታሼ ሲቀርብ ያሳያል፡፡ወዲያውኑም ገብረስላሴበማነጣጠር ወደ ሰላማዊተቃዋሚዎች አቅጣጫ መተኮስ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግን ዒላማውንስቷል፡፡ሰላማዊ አመጸኞች ያለምንምፍርሀት ወደ ገብረስላሴ መቅረብ ጀመሩ፡፡ ማንነቱ በውል ያልታወቀአንድ ሰላማዊተቃዋሚ እንዲህበማለት ድምጹን ከፍ በማድረግ በድጋሜ ጩኸቱን ማሰማትጀመረ፣ “እኛ ወንጀለኞች አይደለንም፣ግርማብሩን ጥሩልን፣ ከእርሳቸው ጋር ለመነጋገርእንፈልጋለን፡፡“ ሌላው ሰላማዊ ተቃዋሚ ገብረስላሴንበድፍረትእንዲህ ይለው ነበር፣ “ወደ ፊትቀጥል፡፡ ተኩስ!“ በዚህን ጊዜ ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊተቃዋሚዎችበማነጣጠር እነርሱንስሜታዊ እንዲሆኑ በመገፋፋት ወደ ኤምባሲው ዋና ህንጻ በመግባትየሽሽት ሙከራማድረግጀመረ፡፡ በዚህ ሂደት ላይም ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችበመደገን በተደጋጋሚለማስፈራራትሞከረ፡፡ በመጨረሻም ጥይቶቹን በሙሉ ተኩሶ ስለጨረሰ ሽጉጡጥይት አልባበመሆን የባዶ ሽጉጥ ድምጽ ሲያቃጭልይሰማ ጀመር፡፡ ባለመሳሪያው እብሪተኛ ደንቆሮወደኤምባሲው ህንጻ ዘልቆ በመግባት አስተማማኝ ጥበቃ ባለበትለእንግዶች ጊዚያዊ ማረፊያወደተዘጋጀውወደ ሰራተኞች አካባቢ በመሸሽ ሄደ፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚወደባንዲራ መስቀያ ቦታውበመሄድ በመሀከሉ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን የወያኔን ባንዲራከተሰቀለበት በማውረድበኢትዮጵያሰንደቅዓላማ በመተካት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅልታየ፡፡ በመጨረሻም ሰላማዊ ተቃዋሚዎችወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ወደጊዚያዊ ማረፊያ ቦታው በመሄድ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግመጮህጀመሩ፣”ነጻነት ነጻነት…“በማለት፡፡

ለተለያዩ ድርጅቶች የሚሰራው የምርመራ ጋዜጠኛ እና ዕውቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋችየሆነውአበበ ገላውከሌላ ምንጭ ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣“በዩኤስ አቃቤሕግ በዋሺንግቶን ከተማየህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ቢል ሚለር በገብረስላሴላይ በመግደል ሙከራእና ታጥቆም በመገኘቱ ምክንያት ለህግቢቀርብ እስከ 30 ዓመታትበእስራት ሊያስቀጣ የሚችል የክስመጥሪያ ወጥቶበታል“ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ መንግስትመምሪያቃል አቀፈባይ የሆኑት ጀን ፔንሳኪ የወያኔገዥ አካል የተኳሹን የገብረስላሴን ያለመከሰስ መብትለማንሳት እናለህግ እንዲቀርብ ለማድረግ ፈቃደኛያለመሆኑን መግለጹን በማስመለከት እንዲህብለው ነበር፣ “ለኤምባሲው የቀረበውጥያቄ ውድቅ ሆኗል፣እናም በአሁኑ ጊዜ የወንጀልተጠርጣሪው ግለሰብ አገር ለቅቆ ወጥቷል፡፡“

አስቀያሚውን የጫካ ትዝታ በዋሺንግተን ዲ.ሲ መተግበር? 

እስከ አሁን ድረስ በዋሺንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማሲ ታሪክ የወያኔ “ዲፕሎማሲ” በሰላማዊመንገድጥያቂያቸውን ባቀረቡዜጎች ላይ መሳሪያ አውጥቶ በመተኮስ ማስተናገድ የዴሞክራሲአባትበሆነችው አሜሪካ ውስጥ ካሉ በየትኛውምኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በታሪክያልተሞከረየመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሰሎሞን ገብረስላሴ አነጣጥሮ ተኳሽነውን? ጫካውስጥበነበረበት ወቅት ከደርግ ጋር ሲያካሂደው የነበረው የዚያ ጦርነት አስቀያሚ ትዝታድንገትብልጭብሎበት ይሆን እንዴ? ሰሎሞን ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥተቃውሟቸውንበሰላማዊመንገድ ለማሰማት በተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ በየትኛውም የዲፕሎማሲያዊተቋምላይተሞክሮ ያልታወቀውን ስልጣኔ የጎደለውን የደንቆሮዎች ድርጊት በመናፈቅ ተኩስከፍቶወገኖቻችንንለመጨረስ መሞከሩ በእውነት በጫካ በነበረበት ጊዜ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩትንወገኖቻችንንሁሉሲጨርስ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ያንን እኩይ ምግባር የዓለም የዴሞክራሲተምሳሌት በሆነችውአሜሪካእምብርት ዋሺንገተን ዲ.ሲ. ላይ ልምዱን ለማስታወስ ያህልሲነሽጠው የክለሳ ስራ መስራቱ ይሆን እንዴ? ‘ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ’ እንዲሉ!

ገብረስላሴ የፈጸመው እኩይ ድርጊት በስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ተመራማሪዎች ‘አስቀያሚትዝታ’በመባልየሚታወቀውን ከአዕምሮ ጋር ተቆራኝቶ የሚኖረውን እና ሳይታሰብ እና በድንገትቅጽበታዊበሆነ መልኩ በአንድምክንያታዊም ሆነ ኢምክንያታዊ ክስተት በሚፈጸምበት ጊዜ ላይ ግንፍልብሎበመውጣት ወደ ድርጊት ከሚሸጋገርስነልቦናዊ ድርጊት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ከዚህ አንጻርገብረስላሴያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በኤምባሲው ቅጥር ግቢአካባቢ በተመለከተ ጊዜበአዕምሮስነልቦናው ውስጥ ተቀርጾ የተነበበው በከፍተኛ ወኔ እና ከባድ መሳሪዎችንታጥቆበመምጣትየእርሱን የአማጺ ቡድን ወያኔን ለመውጋት የመጣ ሰራዊት መስሎ ነው የታየው፡፡በግልብአዕምሮውውስጥ ተጽፎ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሌላ በጎ ነገር በቡድንም ሆን በግልያልለመዱትንእና ያላዩትን ነገር ለሰሎሞንገብረስላሴ ከየትኛው ተሞክሮው ተቀምሮ በአዕምሮውጓዳ ውስጥ አድሮሊከሰት ይችላል ተብሎ ይታሰባል? ጀግናውገብረስላሴ ያንን የመሰለ ድርጊትበሚጽምበት በዚያን ጊዜየሀገሮች መስተጋብር ማስፈጸሚያ የሆነውን ኤምባሲንየሚጠብቅ መስሎአልታየውም፡፡ ይልቁንምበአዕምሮው ላይ ተቀርጾ የኖረው እና አሁንም ያለው የወያኔን የመሬትውስጥምሽግ ጫካ በነበረበት ጊዜከጠላት ለመከላከል የሚያደርገውን ቅጽበታዊ እርምጃመውሰድን ነው የሚያስታውሰው፡፡ወዲ ገብረስላሴበድል አድራጊነት በሚመስል መልኩ ሽጉጡንእያወዛወዘ በዲፕሎማት ወግ ጥቁር ሱፉን ገድግዶለብሶበሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስበታላቋ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በከፍተኛደረጃየውጭ አገርየዲፕሎማት ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ እረስቶታል፡፡አይ ጫካመኖር!የጫካ አስተሳሰብ እኮ በጫካው ውስጥ ያሸነፈ ይኑር የሚለውን የአራዊትአስተሳሰብንየተላበሰ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወዲገብረስላሴ በጫካ ህይወቱ ጊዜ ጠላትን ለመከላከል እናአለቆቹንጠላት ከሚያደርሰው ጥቃት ለመጠበቅ ከአዛዦቹይሰጥ የነበረውን ትዕዛዝ ተቀብሎይተገብርወደነበረበት የወያኔ አማጺ ቡድን እግረኛ ተዋጊነት ስራው ተመለሰ እንጅዘመናዊ አስተሳሰብእናየትምህርት ክህሎት ከሚጠይቀው ዲፕሎማትነት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የሌለውመሆኑንበሚገባተግብሮ እና አስመስክሮ ወደ አገሩ ሳይሆን ወደ መፈንጫው ተመልሷል፡፡

ሰሎሞን ገብረስላሴ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ተልዕኮ እና የውጭ ዲፕሎማት የኗሪነት ፖሊሲእና ህግጥበቃ ምንእንደሆነ እና ምን እንደሚመስል የማያውቀው መሆኑ በግልጽ ይነበባል፡፡አሜሪካ በውጭየሚገኙ ኤምባሲዎቿንከማንኛውም የጠላት ጥቃት ለመከላከል ፈጣን የሆኑ የባህርኃይል ሰራዊቷንበማሰማራት ጥበቃ እንደምታደርገውሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካየሚገኙትን የዲፕሎማሲፋሲሊቲዎችን ጥበቃ በሚመለከት ግን ኃላፊነቱ የወደቀውበአሜሪካየመንግስት መምሪያ፣ በደህንነትአገልግሎቱ እና በአካባቢ የፖሊስ ወኪሎች የጋራ ጥረት ላይ ነው፡፡ከዚህአንጻር የዋሺንግቶን ከተማ ፖሊስለዲፕሎማሲያዊ ፋሲሊቲዎች ደህንነት ሲባል የተለያዩመንገዶችን በመጠቀምአስፈላጊውን ጥበቃበማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለጥበቃው በተለይምዘብ ለተወሰኑ ፋሲሊቲዎች ወይምደግሞለደህንነት ጉዳይ ሲባል እየተዘዋወሩ የሚጠብቁ ዘቦችንበመመደብ እና የፖሊስ ምልክትያለባቸውንተሽከርካሪዎች በማሰማራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡እንደዚሁም ደግሞ መረጃ የማይሰጠውየደህንነትአገልግሎቱ መስሪያ ቤት በዋሺንግትን ዲ.ሲአካባቢ ላሉ የዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ተገቢ የሆነጥበቃይሰጣል፡፡ ይህ የደህንነት አገልግሎትመስሪያ ቤት በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ እና በዲፕሎማቶችፋሲሊቲዎች ላይሊፈጸም የታሰበአስተማማኝ አደጋ መኖሩን ሲያረጋግጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

ያለመከሰስ መብት የተጎናጸፉት ዲፕሎማቶች በማንኛውም መልኩ የጦር መሳሪያን በመጠቀምሌሎችንሰላማዊ በሆነመልክ ተቃውሟቸውን በሚገልጹ ያልታጠቁ ወገኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ዲፕሎማቶችበእራሳቸው ሀገር በሌሎችወገኖች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲባል የጦር መሳሪያ ደብቆመገኘት፣ ወይም ደግሞበድብቅ መሳሪዎችን በማከማቸትበዩናይትድ ስቴትስ ወይም በዩናይትድስቴትስ በሚኖሩ ሌሎች ተመሳሳይተግባራትን በሚያካሂዱ ዲፕሎማቶች ላይጥቃት መሰንዘርንየሚፈቅድ ህግ፣ ፖሊሲ ወይም ደግሞ ልምድበፍጹም የለም፡፡ ዲፕሎማቶች አለመግባባቶችንእናውዝግቦችን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ለመፍታትየቃላት “ጥይቶችን” ይጠቀማሉ እንጅእንደ ወዲ ሰሎሞንገብረስላሴ እየተገበረው እንደነበረው ቁጥር 38የካሊበር ሽጉጦችንአይጠቀሙም፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥርግቢ አካባቢ መሳሪያ በመተኮስያልታጠቁሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለመግደል በተደጋጋሚ ባደረገው የግድያ ሙከራበዋሺንግተንዲ.ሲየዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ህሊና ቢስ እና የሞራል ስብዕናን የጣሰ የወንጀል ድርጊትሆኖሲታወስይኖራል፡፡ ይህ አስነዋሪ የወንጀል ድርጊት ወደፊት ለሚመጡት አስርት ዓመታትየወሮበላየዲፕሎማሲእኩይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የሚያግዙ ለዓለም አቀፍ የህግ እናየዲፕሎማሲተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉየማስተማሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ታላቅ እገዛንያደርጋል፡፡

ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱንልታላቀቀውአትችልም፣ 

የዲፕሎማት ሰዎች ተቀራርቦ በመነጋገር፣ ስምምነት በማድረግ እና በመቻቻል (አብዛኛውን ጊዜበማታለል)ባለመግባባትየሚከሰቱ ውዝግቦችን ለመፍታት ይፈልጋሉ፡፡ የወሮበላ ዲፕሎማቶችሁሉንም ችግሮች እናከዚእነዚህ ክሶች ጋርተያይዘው የሚከሰቱ ውዝግቦችን በመግደል፣በመደብደብ ወደ ዘብጥያ በመወርወርእና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን እናጠላቶቻቸውንበማሰቃየት ይፈታሉ፡፡ ዲፕሎማሲ “በመንግስታትተወካዮች መካከል የሚደረጉ ስምምቶችንለማምጣትየሚያገለግል ትምህርት እና የተግባር ተሞክሮ ነው፡፡“ወሮበላ ዲፕሎማት ሰሎሞንገብረስላሴ የዲፕሎማት ትምህርቱንያገኘው እና የቀሰመው ዙ ኢንላይከሚባለው ተረታዊየዲፕለማት ትምህርት ቤት ነው፡፡ “ሁሉም ዲፕሎማሲበማንኛውም መንገድ ቢሆንየጦርነትቀጣይነት ነው፡፡“ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብትንመደበቂያምሽግበማድረግ ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘለቀውን አከፊውን የወያኔን የጫካጦርነትወደዩናይትድ ስቴትስ ለማምጣት ፈለገ፡፡

የሰለጠኑ ወሮበላ ዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ የሚመረጡት እና የሚላኩት እጅግአናሳበሆነ አጋጣሚነው፡፡ አብዛኞቹ አገሮች ወደ ሌላ አገር የሚያሰማሯቸውን ዲፕሎማቶችየሚመርጧቸውበመንግስት መስሪ ቤቶችከሚመድቧቸው በከፍተኛ ደረጃ ካሉ ሰዎች መካከልነው፡፡ አብዛኞቹየሚመረጡት ዲፕሎማቶችም በከፍተኛ ደረጃትምህርት የቀሰሙ፣ ሰፊ ልምድያካበቱ እና ጠለቅ ያለየፖለቲካ እውቀት ያላቸውን ዜጎች ነው፡፡ ብዙ አገሮችምየዲፕሎማትሰዎቻቸውን ሾመው ወደመደቧቸውአገሮች ከመላካቸው በፊት ሙያዊ የሆነ እና ከሙያው ጋርአግባብነትያለው ስልጠና በማዘጋጀትእንዲሰለጥኑ ያደርጋሉ፡፡

እጅግ በጣም ውሱን ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሀገር ቢሆን እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴያለውን ተራማይምደንቆሮ መርጦ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ባለች አገር ላይ ዲፕሎማት ብሎአይልክም፡፡ በዲፕሎማቲክመስኩ በጣምቀልጣፎች ያልሆኑ አገሮች እንኳ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮየመለመሏቸውን ሰዎች ወደየሀገሮችከመላካቸው በፊትስለዲፕሎማሲ ስራ ሰልጠና ይሰጧቸዋል፡፡በዚህም መሰረት በየጊዜው ከሚለዋወጠውዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር አብረውለመሄድ እንዲችሉእገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ ያ የሚሰጠው ስልጠናምበትክክለኛው መንገድ በዲፕሎማሲ ስራ እናተግባርላይ ትኩረት ያደረገ እንጅ ስለጦርነት ስልት እውቀትወይም ዜጎችን በአገራቸው እንዴት መግደልእንደሚችሉለማሰልጠን አይደለም፡፡ ለምሳሌም ያህልአዘረባጃን የእራሷ የሆነ “የዲፕሎማሲአካዳሚ” አላት፡፡ ቡልጋሪያም የግሏየሆነ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛተቋም አላት፡፡ እንደዚሁምደግሞ ጋና ኮፊ አናን የሰላም ጥበቃ ስልጠና ማዕከል/Kofi Annan Peace Keeping Training Center የሚባል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡በሌላበኩልም የግልየዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ዩኒቨርስቲዎች ማለትም እንደ Tuft University’s Fletcher School of Law and Diplomacy እና ሌሎች ተቋማትም ከዓለምአቀፋዊድርጅቶች ጋር ዝምድና ያላቸውድርጅቶች አሉ፡፡

ሊታምን በማይችል መልኩ የሚያስደንቀው እና የሚገርመው ነገር በአጠቃላይ የወያኔ የውጭጉዳይሚኒስቴር አመራርበዲፕሎማሲ የሙያ ዘርፎች ላይ የሰለጠነ ወይም ደግሞ በዚህ ሙያ ላይበቂልምድ ያለው ዲፕሎማት የለውም፡፡ለምሳሌ ያህል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ቁንጮ የሆነውሰውየዲፕሎማሲ ሙያ ስልጠናም ሆነ ልምድየላቸውም፡፡ ምንም፣ ባዶ! የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርቴዎድሮስአድኃኖም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከአስመራዩኒቨርስቲ በስነሕይወት/Biology የትምህርትመስክ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማስተር ኦፍሳይንስበImmunology of Infectious Diሰዓሰስ በሚል ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ ያገኙሲሆን የፒኤች ዲ ዲግሪያቸውንደግሞበህብረተሰብ ጤና/Community Healthየትምህርት መስክ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘውከኖቲንግሀምዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፡፡ ለጤናሚኒስትርነት ተሾመው ነበር፡፡ በአንድ ጀንበር ምሽት ከመለስዜናዊ ህልፈት በኋላእራሳቸውንየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገኙት፡፡ (እርግጠኛ ነኝ በአንድ ጀንበርምሽት ደግሞ እራሳቸውንጠቅላይሚኒስትር ሆነው ያገኙታል)፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነውመሾማቸው ለጠቅላይሚኒስትርነት መወጣጫነትየመጀመሪያ ደረጃ እና ለሚጠብቃቸው የጠቅላይሚኒስትርነትሹመታቸው ለይስሙላም ቢሆን ለማሟሻነት ቢጠቅምበሚል እኩይ ስሌት የተቀነባበረ ነው፡፡እርግጥ ነው አምባገነንነት እና ወሮበላነት በተንሰራፋባት የመጨረሻ ደኃ ሀገርለዲፕሎማትነትመስፈርቱዘር እና ታማኝነት እንጅ ትምህርት እና ልምድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል! (ሟቹ መለስዜናዊበአንድ ወቅትስለሚኒስትሮቹ አሿሿም የትምህርት ብቃት ማነስ ጉዳይ በቴሌቪዥን ጥያቄበቀረበላቸው ጊዜ“ታማኝነትእንጅ ማይም ይሁኑ” በማለት የሰጡትን አስገራሚ እና ፈጣጣየስላቅ መልስ ልብ ይሏል፡፡)

ጉድ እኮ ነው ጎበዝ እንዴት አንድ ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ልምድ እና በመስኩም አስፈላጊየሆነውትምህርትሳይኖረው ወይም ደግሞ ምንም መነሻ መሰረት ሳይኖረው እንዲሁምበአምበሳደርነት (ስለዓለምአቀፍ ህግ እናዲፕሎማሲ ፍጹም ባይተዋር የሆነ [ከኢትዮጵያ እሳትወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ] በሚልርዕስ ያቀረብኩትን ትችትይመልከቱ)   እንኳ ሳይሰራበድንገት እና ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ የውጭ ጉዳይሚኒስትርነትን ያህል ከባድ ኃላፊነትየሚጠይቅየሚኒስትርነት ቦታን ይይዛል?

ለዚህ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው፡፡ አድኃኖም በዘር ሀረጋቸው ብቻ እና ብቻ ነው የወያኔየከፍተኛዲፕሎማት ስልጣንየተሰጣቸው፡፡ በእርግጥ ይኸ ጉዳይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በአሁኑጊዜ በህይወትየሌለው መለስ ዜናዊ ምን ዓይነትየትምህርት ማስረጃ እና ብቃት አቅርቦ ነውጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው?መለስ በርቀት የትምህርት ፕሮግራም በተልዕኮከእንግሊዝ ሀገርበቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያዲግሪውን አገኘ፡፡ ለሁለተኛ ዲግሪውም ከኢራስመስዩኒቨርስቲየዓለም ብቸኛው ታላቅ አዋቂ ነኝ አያለሲፎከርበት የነበረውን የልማት ምጣኔሀብት/Development Economics የመመረቂያ ጽሁፉንማጠናቀቅ ያልቻለ ሰው ነበር፡፡

ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለወሮበላ ዲፕሎማት ልዩ ስልጠና እየተሰጠ በብቃት ላይሳይሆንበዘር እናበታማኝነት ላይ ትኩረት በማድረግ የሚኸድበት ስልት እውነተኛውንየዲፕሎማሲ ስራ አካሄድእንዲበላሽ አድርጎታል፡፡ለአፍሪካውያን/ት የወሮበላ ዲፕሎማቶችማሰልኛ ተቋም በቅርብ ጊዜ ውስጥከአፍሪከ ህብረት የለማኞች አዳራሽ፣ለአፍሪካ አምባገነኖች እናወሮበሎች መሰብሰቢያ ከተሰራው አዳራሽፊት ለፊት በቅርብ ርቀት ላይ ይገነባል የሚልግምትአለኝ፡፡ የሚያስገርም ጉዳይ ይሆናል፡፡

ከእውነታዎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን፡፡ አሳማን የከንፈር ቀለም መቀባት ይቻላልቆንጆለማስመሰል፣ ሆኖም ግንከዕለቱ መጨረሻ ያው ዓሳማ ዓሳማ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እንደሰለሞንገብረስላሴ፣ ግርማ ብሩ ወይም ቴዎድሮሰአድኃኖም እና ሌሎች በርካታዎቹ ብሪፍ ኬዝ/ቦርሳ እናየይሰሙላ ክብር መስጠት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጨረሻምእራሳቸው እራሳቸውን ሆነውያገኙታል፡፡ ወሮበላዘራፊዎች!

መንግስታዊ አገዛዝ ከወሮበላ (የጫካ አገዛዝ ጋር) ሲነጻጸር፣ 

የወያኔን አገዛዝ የወሮበላ አገዛዝ ነው በማለት በምገልጽበት ጊዜ ከምንም በመነሳት በጥላቻ  ወይምደግሞለቡድኑ ክብርካለመስጠት አይደለም፡፡ አንዲሁም መለስ ዜናዊን “የአፍሪካ የለማኞችአለቃ” ነው በማለትስገልጽ እራሱበሚጠቀምባቸው ቃላት ላይ መሰረት አድርጌ ነው፡፡ የእራሴንቃላት እና ሀረጎች እርሱከሚሰራቸው እውነታዎችበመነሳት ነው የምርጣቸው፡፡

የወያኔ አለቆች በምንም ዓይነት መልኩ ከወሮበላነት (የጫካ) አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርበፍጹምሽግግርአያደርጉም፡፡ በጫካው ዘመናቸው ወጣት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ልምድየምሁርነትአስተሳሰባቸውን፣ የሞራልስብዕናቸውን እና የማህበራዊ ልማት እይታቸውን በጫካውየቅኝት አስተሳሰብብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፣ ሸፍኖትቀርቷል፡፡ ከዚያ አልፎ አንዳንዶቹ ዘመናዊእና ላቅ ያለ የአካዳሚትምህርት የማግኘት ዕድል ያገኙ አባላቱ እንኳ ስልጣንከያዙ በኋላበተመሳሳይ መልኩ ድሮ ወደነበሩበትየአስተሳሰብ አድማስ በመመለስ የአስተሳሰብ ግልብነት እናየሞራልዝቅጠትን እና ባዶነትን አንጸባርቀዋል፡፡

የወጣትነት የመጀመሪያዎቹን ዓመታት በጫካ ውስጥ አማጺ ሆኖ ከማሳለፍ አንጻር ለመቀየርየማያስችል እናቋሚ የሆነየተቸከለ አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ በአካዳሚክ ዓለሙ ያሉም ሰዎችይህን ሲመለከቱቱ የአማጺያንን የጫካ ህይወትመኖር ያልረሱት እና በአዕምሯቸው ላይ የማይለቅችካል ስለሆነ ሆብስ“የመሆን ሁኔታ” እንዳለው በአእምሯቸው ላይበጫካ አስተሳሰብ የተቃኘአንዳች የሆነ ነገር አንደሚፈጠርነው።  የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ቶማስ ሆብስየሰለጠነመንግስት በሌለበት ጊዜ “እያንዳንዱ ሰውከሌላው ሰው ጋር በጦርነት ይኖራል” በማለት የሙግትጭብጣቸውንአቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳህይወት በመሆን የተፈጥሮ ህግ ላይ “ብቸኛ፣ ደኃ፣በጭካኔ የተሞላ፣ አውሬአዊ እናኋላቀርነት አስተሳሰብንየተላበሰ ይሆናል“፡፡ ሆኖም ግን ሊነሳየሚችለው ጥያቄ ሆብስ የመሆን ሁኔታ እዳሉት ለአስርትእና ግማሽዓመታት በአማጺነት በጫካሲኖሩ የነበሩት የወያኔ አማጺ አመራሮች ከጫካ ህይወታቸው ወጥተውስልጣንንበኃይል ነጥቀውበስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ እና የሰለጠነ መንግስታዊ መዋቅር መሪዎችከሆኑ በኋላበእርግጠኝነትሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ሲመሩበትየነበረውንየመሆን ሁኔታ እርግፍ አድርገውትተው የወሮበላነትን መንግስታዊ አገዛዝ በሰለጠነመንግስታዊአስተዳደር እንዲቀየር በማድረግ የህግ የበላይነትንበማስፈን እውነተኛ ሽግግርን ሊያመጡእናህዝቡን በሚፈልገው መልክ ማስተዳደር ይችላሉን?

አጋጣሚ ሆኖ ከእነርሱ አባባል ታምራዊ ሀረጎች በመዋስ “እድገት እና ትራንስፎርሜሽን”ለማምጣትየምሁራዊ እናየሞራል ብቃቱ ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡ ለወያኔ አለቆች በሰለጠነማህበረሰብ ውስጥ ገብቶአብሮ መኖር አሁን ብዙገንዘብ እና ሀብት ከመዝረፍ በስተቀር ለእነርሱህይወት በጫካ ውስጥ ይኖሩበትእንደነበረው ዓይነት ቀጣይነት ያለውነው፣ ምንም ዓይነት ልዩነትየለውም፡፡ በእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስምንም ዓይነት የተቀየረ ነገር የለም፡፡ ለ23ዓመታትበስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ከቆዩ በኋላ ምንምዓይነት የተማሩት ቁም ነገር የለም፡፡አሁንም ቢሆንበጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያራምዱት የነበረውንሚስጥራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናበህዝቡ ላይ በመጫን ለመቀጠልይፈልጋሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜየተጠያቂነት እናየግልጽነት ባህሪን አያራምዱም ነበር፣ አሁንም ቢሆን አንድንታላቅ አገር በቁጥጥራቸውስርአድርገው ስርዓት ባለው መልኩ ተጠያቂነት እና ግልጽነትን በተላበሰ ሁኔታ መምራትሲችሉይህንንመተግበር ተስኗቸዋል፡፡ በጫካ ውስጥ ሆነው ከደርግ ወታደራዊ አምባገነን ጋር ትግልሲያደርጉበነበሩበትወቅት ውሳኔ ሰጭነት በጥቂት የወያኔው መሪዎች ብቻ እና ብቻ ነበር፡፡ በዚያንወቅትእነዚህ ጥቂት አመራሮች ይመሩትበነበረው ሰራዊት እና በአጠቃላይ በቁጥጥራቸው ስርአድርገውትበነበረው ህዝብ ላይ ጥሬ የሆነ አስተሳሰብን፣ ጭካኔየተሞላበት ኃይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ሰላማዊአማጺያንን እና የሰላ ትችት ያቀርቡባቸው በነበሩት ወገኖች ላይ ጭካኔየተሞላበት እርምጃመውሰድጀመሩ፡፡ ከእነርሱ ሀሳብ ጋር ስምምነት የማያደርጉ ዜጎችን ማግለል፣ እንደሰላይነትበመቁጠር መግደል እናማጥፋት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንግስታዊ ስልጣንን ከተቆናጠጡበኋላምየተቃዋሚ የፖለቲካፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ሌሎችንም ለስልጣናቸው አስጊናቸው ብለውየሚጠረጥሯቸውንወገኖች ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል እና ከሀገር እንዲወጡማድረግን ስራየ ብለው መተግበር ጀመሩ፡፡ከእራሳቸው መካከል በሀሳብ በመለያየታቸውየተገነጠሉትን ተስፈንጣሪ ቡድኖች  ርህራሄ በሌለውመልኩአስወገዷቸው፣ አዋረዷቸው!

በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ስልጣንን፣ ገንዘብን በመዝረፍ እራስን እንደማበልጸጊያ፣ የፖለቲካየበላይነትእናማስፈራራትን እንደ መሳሪያ በመቁጠር ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔአገዛዝ በሙስና የበከተእና የሙስናውበሽታ በኢትዮጵያ አካል ላይ እንደ ነቀርሳ እየተሰራጨመሆኑን ሙስናን በኢትዮጵያመመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia በሚል ርዕስ  የዓለም ባንክ አዘጋጅቶባወጣው በባለ550 ገጽ ዘገባው ላይበግልጽአስፍሮታል፡፡ ወያኔ በጫካ በነበረበት ጊዜ አመራር ላይመሆን ማለት የእራስን ስብዕና መትከልየነበረ ሲሆንአሁንም ቢሆን በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስዜናዊ በእርሱ ደቀመዝሙሮችእንደ ትንሹ አምላክ ያህል ይመለክነበር፡፡ የእነርሱ ከጫካ አገዛዝ ወደመንግስታዊ አስተዳደርያደረጉት ሽግግር የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትየነበረውን የደርግ አገዛዝበማስወገድበአንድ ሰው፣ በአንድ ፓርቲ የወያኔ አገዛዝ ተኩት፡፡ የወያኔ አመራሮች በደርግአገዛዝ ላይያደረጉትለውጥ አለ ከተባለ “ለወያኔ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሩነው”የማለታቸውአምባገናናዊ አመለካከታቸው ብቻ ነው!

ከወሮበላነት/ከጫካ አገዛዝ ወደሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር የሚደረግ እውነተኛ ሽግግርየፍልስፍና እናየፖሊሲሁለቱንም ነገሮች ስርነቀል በሆነ መልኩ መቀየርን ይጠይቃል፡፡ ይኸ ግንባዶ ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡በተደጋጋሚ ጊዜእንደምለው የወያኔ አመራሮች ትክክለኛ መንግስታዊመዋቅርን ይመሰርታሉ ወይም ደግሞትክክለኛ መንግስታዊስርዓትን ያራምዳሉ ማለት ሰይጣንከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሰ ያስተምራልእንደማለት ነው፡፡

ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር መሰረታዊ የሆኑትን መርሆዎች ማለትም የህግ የበላይነት፣የስልጣንክፍፍልን፣የቁጥጥር እና የኃይል ሚዛንን እና ህገመንግስታዊ የአስተዳደር ሂደትንበመተግበር በእውነታ ላይየተመሰረተ ትችትንበትክክል ለተከናወኑ ስራዎች ደግሞ አድናቆትመስጠት እና መግባባትን ይጠይቃል፡፡የወያኔ ወሮበላ አመራሮችለእንደዚህ ዓይነቶቹ ጉዳዮችእጅግ በጣም አነስተኛ የሆኑ ልምዶች ወይም ደግሞየተግባር ተሞክሮ ጭራሹንምየላቸውም፡፡በዚህም መሰረት ማንም ቢሆን እነዚህ የወሮበላ ስብስብአመራሮች በፖለቲካ ህይወታቸውውስጥያልነበራቸውን እና በተሞክሮም የማያውቁትን ተጠያቂነትን እናግልጸኝነትን ሊያሰፍን የሚያስችልየፖለቲካስርዓት ለህዝቡ ማስፈን እና መተግበር ይችላሉ ብሎ መጠበቅየዋህነት ነው፡፡ በጫካውስጥ በነበሩባቸው ጊዚያት ምንምዓይነት ነጻ ምርጫ አካሂደው አያውቁም፣በመሆኑም እ.ኤ.አበ2005 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በዝረራበተሸነፉበት ወቅት ተአምር የሆነያህልተገርመው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ታላቅ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010በተደረገውአገርአቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት (በመዝረፍ አላልኩም) ድልተቀዳጅተናል፡፡በጫካ በነበሩባቸው ጊዚያት የሚናገሯቸው ቃላት እራሳቸው ህግ ነበሩ፣ ስለ የህግየበላይነት ምንም ዓይነትሀሳብአልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ የእነርሱቃል እራሱ ህግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡በእራሳቸው ስልጣንያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ በጫካ ውስጥበነበሩበት ጊዜ እነርሱ እራሳቸው ዳኛ፣ችሎት እና አስፈጸሚ ነበሩ፡፡በስልጣን ላይ ባሉበት ጊዜበጫካ ላይ ከነበሩበት ጊዜ የተለየ ነገር የላቸውም፣ልዩነት አለ ከተባለም በጫካው ጊዜይፈጽሙትያልነበረ አሁን ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅርንከተቆጣጠሩ በኋላ ለይስሙላ የዝንጀሮፍርድቤቶችን በማቋቋም እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ውሳኔውእንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ በጫካውስጥ በፍርሃት እና በበቀልነው የኖሩት፣ እናም የሲቪል ነጻነቶች እናየእነዚህ ነጻነቶች አተገባበርለእነርሱ ባዕድ ናቸው፣ ፈጽሞ አይተዋወቁምና፡፡በአሁኑ ጊዜም ህዝቡበድንገተኛ መሬትአንቀጥቅጥ አመጽ ያስወግደናል በሚል ፍርሀት ውሰጥ ተቀርቅረው ሌት ቀንሲባንኑይውላሉ፡፡እናም የሲቪል ነጻነቶች እና መብቶች ቅንጦት የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ እነዚህ ቅንጦት የሆኑነገሮችምለእኛሳለይሆን ለምዕራባውያን ሰዎች ብቻ የተተው እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ሆኖምግንእነርሱ፣ የእነርሱደቀመዝሙሮች እና ደጋፊዎቻቸው ለሚሰሯቸው ወንጀሎች እና የሲቪልወንጀሎችሳይቀር ያለመከሰስ መብትንበመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እራሳቸውን በማስደሰትላይይገኛሉ፡፡ በአጭሩ ከዚህ የእኩይ አስተሳሰብባለቤት ከሆነው የወሮበላ ቡድንዴሞክራሲያዊአስተዳደርን የተላበሰ ስርዓት በኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚያስችለልመንግስታዊ መዋቅርመጠበቅከባዶ ተስፋ የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዴት? 

በአንድ ታትሞ በወጣ ዘገባ እንደቀረበው የወያኔ አገዛዝ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014በዋሽንግተንዲ.ሲ በኢትዮጵያኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወገኖቻችን ላይክስ ለመመስረትእንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል፡፡ ዲናሙፍቲ የተባሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር ቃል አቀባይይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፣“የዩናይትድ ስቴትስመንግስት በኤምባሲው ቅጥር ግቢገብተው ጸረ መንግስት የሆኑ መፈክሮችን እያሰሙየኢትዮጵያንባንዲራ በማውረድ ሁከት በፈጠሩት ሰዎችላይ የኤምባሲውን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እናበአጥፊዎችላይ ክስ መመስረት እንዳለበት ይጠበቃል፡፡“በሌላ በኩል የወጣ ዘገባም እንደጠቆመውሰላማዊ ሰልፈኞች በአዲስ አበባበሚገኘው የዩናይትስ ስቴትስኤምባሲ በመሄድ “ሰላማዊሰልፈኞች ለህግ መቅረብ አለባቸው” የሚል ጥያቄ ያቀረቡመሆናቸውንአሳውቋል፡፡ “ በቪዲዮክሊፑ ላይ እንደሚታየው ሰላማዊ ሰልፈኞች የኢትዮጵያን ብሄርብሀረሶቦችየሚወክለውን ባንዲራበማውረድ የጥንቱን እና የነጻነታችን አርማ ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አረንጓዴ፣ቀይእና ብጫቀለም ያለበትን የህዝቦች ነባር ባንዲራ በክብር ወደነበረበት ቦታው መለሱት፣አከበሩትእንጂአላዋረዱትም፡፡  ሰላማዊ ሰልፉ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የመድረክ ላይ ተውኔት ነው፡፡

ሙፍቲ፣ ቴዎድስ አድሀኖም እና ሌሎች የወያኔ ደናቁርት ምን መመኘት እንዳለባቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

መጀመሪያ፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ጥፋተኛ ለማድረግ በሚደረገው የውንጀላ ብያኔ ላይ ግልጽ መሆንአለበት፡፡በአሜሪካአገር የፌዴራል ወይም የኮሎምቢያ ወረዳ ግዛት ወንጀል ስርዓት ኮድ ላይ“ሻጥር ለመስራት”የሚል የወንጀል ጥቅስአይታወቅም፡፡ ምናባዊ የሆነ የወንጀል ክስ በመፈብረክክስ እንዲመሰረት ቢያስቡእና ህዝቡን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉየእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስበምን ያህል ጥልቀት እንደወረደ እናስለአሜሪካ ህግ ያላቸውን ድንቁርና የሚያመላክትነው፡፡(በእንደዚህ ዓይነት ፍጹም ድንቁርናየተጠናወታቸው ፍጡሮች “ኢትዮጵያ የምትመራ” መሆኗንስመለከት በጣምተሸማቀቅሁ፣ አዘንሁም!)

ሁለተኛ፡ የወያኔ ደናቁርት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አገር ማንኛውንም ዓይነት ባንዲራ የኮከብእናነጠብጣብ ምልክትያለባትን የአሜሪካን ባንዲራም ቢሆን ማውረድ ወይም ማዋረድ ወንጀልአለመሆኑንሊያውቁ ይገባል፡፡ እ.ኤ.አ በ1989በቴክሳስ ግዛት ጆንሰን የዩኤስ አሜሪካንንባንዲራ እ.ኤ.አ በ1984የሬፐብሊካን ብሄራዊ ጉበኤ በዳህላስ፣ በቴክሳስ)ባቃጠለበት ወቅትጀስቲስ ዊሊያም ብሪናን በአጠቃላይሀሳብ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣“በሀሳብመለያየትን የማስተናገድ መብት ማረጋገጥየአሜሪካ የመጀመሪያው የህግ ነጻነት ማሻሻያችንየመሰረት ድንጋይነው፣ መንግስት በዜጎቹ መካከልአንድነትን የሚያጠፋ ነገር በመፈብረክ የዘፈቀደትዕዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግአይችልም፡፡“ይላል፡፡ ስለሆነም ያ አንድ ዓይነት ባህሪ እናመርህ ያለው መንግስት የአንድነት መገለጫ የሆነውንምልክትበመጣስ ከዚያ መርህ ጋር የሚጣረስትዕዛዝን ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ በቀላል አነጋገር እንኳንስይህንንበሸፍጥ የተዘጋጀ የብሄርብሄረሰቦች የሸፍጥ ባንዲራ ከተሰቀለበት ማዕዘን ማውረድ ይቅርና ጥንታዊውንእናየተከበረውንያሜሪካ ባንዲራም በእሳት ማቃጠል ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡

ሦሰተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት በጋዜጦች እና በድረ ገጾች የሚለቀቅ የዲፕሎማሲስራንእንደማይሰራየወያኔ አገዛዝ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ እነዚህ ደናቁርት የዩናይትድስቴትስ መንግስትየሚፈልጉትን ነገርእንዲያደርግላቸው ከተፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮቶኮልስነስርዓትን ማክበርይጠበቅባቸዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስየመንግስት መምሪያ ከውጭ መንግስታትየዲፕሎማቶች የተቃውሞጥያቄ ሲቀርብለት የውጭ መንግስታቱ የሚፈልጉትንለማግኘት ሲፈልጉእነዚህ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልጉመንግስታት መከተል ያለባቸውን ህጎች እና የአካሄድስነስርዓቶችበመከተል እንዴት ምላሽ መስጠትእንደሚችል በጣም ዝርዝር በሆነ መልኩአስቀምጧል፡፡ የወያኔ ደናቁርት በቀጣይነትየሚደርስባቸውንውርደት እና መሸማቀቅ ለማስቀረትበማሰብ ለእነርሱ ወገናዊነት እገዛን ለማድረግ የዩኤስአሜሪካንንየመንግስት መምሪያ የውጭ ጉዳይሰነድ ቮሊዩም 5 የእጅ መጽሐፍ ቁጥር 1ን እንዲመለከቱእጋብዛለሁ፡፡(በነገራችን ላይስለዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይን በማስመልከት ጥያቄአቅርባችሁልኝለነበራችሁአንባቢዎቸ በግንባር በመገኘት ምላሽ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሆኖም ግንለዚህስራይጠቅማችኋል በሚል እሳቤ “Diplomatic and Consular Immunity: Guidance for Law Enforcement and Judicial Authorities“በሚል ርዕስየተዘጋጀውን በመረጃ የበለጸገ ሰነድ እንድታነቡትእጋብዛለሁ፡፡

አራተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች እንደ ወያኔው የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶችሳይሆኑተከላካዮች የተሟላህገመንግስታዊ መብት ያላቸው እና አስገድዶ ቃል ያለመቀበልን፣ያለመደብደብእና በሰውነት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃትማስረጃዎችን ጭምር በማካተት አዘጋጅቶ ያስቀመጠመሆኑንየወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ የወያኔ ደናቁርትእነዚህን የነጻነት ታጋይ ወገኖቻችንንበህግፊት አስቀርበው ለማስቀጣት ከልብ ፈልገው ከሆነ በዚህ በአሜሪካ የህግ ሰነድላይ የተዘረዘሩትንእናየታጨቁትን ህጎች በሙሉ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አምስተኛ፡  የህግ ስርዓት ቢኖር ኖሮ ግርማ ብሩ እና ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች እንዳደረጉትሁሉገብረስላሴምበታላቁ የፍርድ ቤት ችሎት ቀርቦ ቃሉን መስጠት እና የማስተባበያ ማስረጃመስጠትየነበረበት መሆኑን የወያኔ ደናቁርትሊገነዘቡት ይገባል፡፡ በችሎት ፊት ቴዎድሮሰአድሃኖም እና የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦቻቸው ለተፈጠረው ነገርሁሉ ቃል መስጠትየጽሁፍ ማስረጃዎች ማቅረብይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ተከላካይ በግርማ ብሩ፣በገብረስላሴ፣በአድሃኖም እና በሌሎች ቀሪ ሰዎች ላይመስቀልኛ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመስቀለኛጥያቄዎችሲጠበሱ ምነው ጫካ ገብተን ደርግንበተዋጋን በለው ሳይመኙ አይቀሩም።

ስድስት፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል መጠበቅይኖርበታል፡፡ማስረጃለመስጠት ወደአሜሪካ የሚመለስ ከሆነ የዲፕሎማት ያለመከሰስ መብትእንደሌለው ማወቅይኖርበታል፡፡ በጣም ከባድበሆነ ወንጀል ክስ ምክንያት ምንም አይነትአስተያየት በዩናይትድ ስቴትስአሜሪካ አቃቤ ህግ በኩል አያገኝም።ያለመከሰስ መብቱእንደማይሰራ እና ክስ ተመስርቶበት ወደ ፍትህአካል ከመቅረብ እንደማያመልጥ ሊታወቅ ይገባል፡፡ገብረስላሴ አንድ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ ከተገኘ እናያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ ጉዳዩ ፍርድ ቤትየሚታይ ከሆነ ወደ ፍርድቤት ችሎት ከመቅረቡ በፊትወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ ካለምንምዋስትና በቀጥታ ወደ ዘብጥያ ሊወርድእንደሚችል ሊገነዘብይገባል፡፡

ሶሎሞን ገብረስላሴ እና የወያኔ አለቆቹ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ህግ ያለበትን እና አስከ አሁንድረስበህይወታቸውአይተውት በማያውቁት የፍትህ ችሎት ላይ ይገለገላሉ የሚል ከጥርጣሬ የዘለለእምነትአለኝ፡፡ በገብረስላሴ ድርጊትምክንያት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረውንጉዳት ከግምትውስጥ በማስገባት የወያኔ ኤምባሲ እና ገዥአካል ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችልየረዥም ጊዜ የፍርድ ሂደትሊኖር ይችላል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ በሲቪል ጉዳዮች ላይየሚታየው እናየሚሰጠው ብይን የመረጃ መለኪያመስፈርቱነ ባገናዘበ መልኩ በአብዛኛው በሚቀርቡትማስረጃዎች ላይመሰረት ተደርጎ ሲሆን ይህንንምለማሳካት ከባድ አይደለም፡፡

አብዛኞቹ አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማድረግ ስምምነት አድርገው ዲፕሎማት ልከውበመተባበርከሚሰሩባት ሀገርላይ የተላከው ዲፕሎማት ወንጀል ሰርቶ ከዚያች ሀገር በመሸሽአምልጦ ወደ ሀገሩየመጣን ዲፕሎማት በሀገራቸው ህግመሰረት የሚቀጡ መሆኑን ማስተዋልአስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሶሎሞንገብረስላሴ በኢትዮጵያ ባሉት የወያኔ አለቆቹ ቅጣትሊጣልበትእንደማይችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይልቁንምየወያኔን ኤምባሲ ከጠላት ለመከላከል ባደረገውጀግንነትበወሮበላ ጓደኞቹ የበለጠ እንደሚወደስ እና ጀግናእንደሚባል መገመት ይቻላል፡፡

አገሮች እነርሱን በውጭ አገር ሄዶ ሊወክላቸው የሚችለውን ዲፕሎማት ለመምረጥ በአገሪቱካሉትየመንግስትሰራተኞች መካከል በደረጃው እና በትምህርት ዝግጅቱ እና ብቃቱ ላይበመመስረትእንዴት እንደሚመርጡ እና ለምንምየማይሆን የወሮበላ ዲፕሎማት ለምን መርጠውእንደማይልኩየእራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ እነዚህ የመንግስትሰራተኞች በዲፕሎማትነትተወክለውሲሄዱ ምን መስራት እንደሚጠበቅባቸው እና የሄዱበትን ሀገር ህጎች እና ደንቦችማክበርብቻምሳይሆን የእራሳቸውን አገር ክብር ሊያዋርዱ ከሚችሉ ነገሮች እራስን ንጹህ በማድረግበጥንቃቄመራመድእና በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ህዝቡ የእራሱን ፍርድ መስጠት እንዲችል መሰረትእንዲያዝዕድሉን መስጠት እንዳለባቸውሊገነዘቡ ይገባል፡፡

ዲፕሎማቶች ወንጀለኛ ከሆኑ የወሮበላ አፋኝ ስርዓቱ ታማኝ ሎሌዎች የሚመረጡ ከሆነገብረስላሴየሰራውን የመሰለእኩይ ምግባር የተንጸባረቀበት ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ስለሆነምወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱንልታላቀቀውአትችልም።

ገብረስላሴ በመግደል ሙከራ ምክንያት የተባረረ መሆኑ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጉ ብቻ ነውእርሱን ነጻሊያደርገውየሚችለው፡፡ በአገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነትበማስመልከትየ1961ዱ የቬና ስምምነትአንቀጽ 31 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ ”አንድየዲፕሎማት ወኪል የሆነሰው ከሚቀበለው አገር የወንጀለኛ ህግያለመከሰስ መብቱን ተጎናጽፏል“ይላል፡፡ ወደድንም ጠላንም የህግየበላይነት ማለት ሌላ ሳይሆን እንደዚህ ነው፡፡

አንደው በነገራችን ላይ….

“በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በሶማሌ ሚሊሻዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችልአስጠነቀቀ“ 

እ.ኤ.አ ኦክቶበር 15/2014 ሬውተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት የዩናይትድ ስቴትስኤምባሲየሚስጠንቂያ መግለጫሰጥቷል በሚል የሚከተለውን ዘገባ አስነብቧል፣ “በቦሌ በሚገኙየምግብ ቤቶች፣ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ የእምነትቦታዎች፣ የገበያ አዳራሾች እና ታላላቅ የመገበያያቦታዎች ሌላ ማስታወቂያእስካልተሰጠ ድረስ የአሜሪካ ዜጎችእንዳይደርሱ መራቅ አለባቸውምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች ሊከሰቱበሚችሉ በአሸባሪ ቡድኖች የጥቃት ኢላማ ውስጥናቸው“ይላል፡፡ ሬውተርስ በተጨማሪም እንዲህ የሚልጥቆማ ሰንዝሯል፣ “የኢትዮጵያ ባለስልጣኖችባለፈው ዓመትመጫረሻ አካባቢ አልሻባብ በአዲስ አበባከተማ ጥቃት ለመሰንዘር የአውጠነጠነውአስከፊ የሆነ የአጥፍቶ መጥፋትየሽብር አደጋ እንዳለ መረጃከደረሰው በኋላ የደህንነት ኃይሉበተጠንቀቅ ላይ መሆኑን“ ጠቁሞ ነበር፡፡

ይቅርታ አርጉለኝና ፣ ይኸ አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ የወያኔ ገዥ አካል እንደገና ሶማሊያንለመውረርእያደረገ ያለውዝግጅት አለ ማለት ነውነው? እብደት ወይስ ብልሀት!? የዩኤስ ኤምባሲማስታወቂያኢትዮጵያ እንደገና ሶማሊያንእንድትወር የቀረበ ሀሳብን የመሞከረያ/መገምገሚያየዳግም ወረራ ወሬማናፈሻ ዘዴ ነውን? ዓላማው ይህ ከሆነ ሁሉምነገር ሁሉ ፍጹም ውድቀትመሆኑን መገንዘብይኖርባቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፈው ሴፕቴምበር 23/2014 ከወያኔ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመጠንያለፈክብካቤ ሲያደርጉመታየታቸው እና በቪዲዮ ክሊፕ መለቀቁ ስለታሰበው ወረራ በትክክልእንድጠረጥርአድጎኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ ሲሉተደምጠዋል፣ “…እኛ[ከወያኔ የልኡካን ቡድን አባላት ጋር] ሰላምማስከበር እና በሰላማዊመንገድ የግጭት አፈታትንበሚመለከት አሰራሮቻችንን በማሻሻል እንዴት ውጤታማ በሆነመልኩመፍታት እንዳለብን ተወያይተናል፡፡ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከዓለም ከማንኛውም ሀገር የተሻለችትሆናለች –ሰላምን ከማስከበር አንጻርከብዙዎቹ አንዷ ናት፣ በጣም መጥፎ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜእና ግጭትን በማስወገድ ረገድከዓለምውጤታማ የሆነ የውጊያ ኃይል ያላት ናት…“ በቅርብ ጊዜየተደረገው ማስታወቂያ የማይቀር የአሸባሪዎችጥቃትሊሰነዘር እንደሚችል እና ሌላኛው ጫማየወደቀ መሆኑን የሚያመላክት ነገር ነውን?

ወደ ኋላ መለስ በማለት እ.ኤ.አ በ2006 አጋማሽ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ህዝብ ላይ ሙሉአስደንጋጭእና አስከፊየጦርነት ጥሪ ከማስተላለፉ እና ታንኮቹ የሞቃዲሾን ከተማ ከመውረራቸውእናከመርመርመርሳቸው ሁለት ወራትቀደም ብሎ አልሻባብ እና ጂሀዲስቶች በኢትዮያ ላይ ጥቃትለመሰንዘርእየተባለ ብዙ ዲስኩሮች ተደርገው ነበር፡፡እ.ኤ.አ በ2006 “ጂሀዲስቶች እየመጡነው/Jihadists are coming“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ጦርነቱከመካሄዱበፊት ይደረግ የነበረው የፕሮፓጋንዳስራ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር14/2006 የዩኤስአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞእረዳት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ጃንዳይፍሬዘር እንዲህ የሚል ውንጀላ ሰጥተው ነበር፣“የዲፕሎማቲክ እናየደህንነት ባለስልጣኖችየእስልምና ህብረት ተዋጊዎች ከሌላው ወገን እገዛ ለማግኘት እና ከእነርሱጎንመሰለፍ እንዲችሉበኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ“ የሚል ውንጀላ አሰምተው ነበር፡፡እ.ኤ.አዴሴምበር27/2006 በስተሰሜን በኩል በ90 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኘውንሰትራቴጂካዊየሆነችውንየጆሀርን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የመለስ ዜናዊ ተዋጊ ኃይሎች ወደሞቃዲሾየሚያቃርበውን በረሀ መውረር ጀምረውነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያየእስላማዊህብረት ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ “ተጨባጭነት ያለውየደህንነት አደጋ ደቅነዋል”በማለትየወረራውን አስፈላጊነት እና ፍትሀዊነት አጸደቀች፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከትየዩናይትድስቴትስየመንግስት መምሪያ ቃልአቀባይ የነበሩት ጎንዛሎ ጋሌጎስ እንዲህ ብለው ነበር፣“ኢትዮጵያበሶማሊያእየተደረገ ባለው የመሻሻል እድገት ላይ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ የደህንነት ስጋትተደቅኖ እንዳለእናህጋዊ እውቅና ያለው የሶማሊያ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት በጠየቀው እርዳታመሰረት ኢትዮጵያ ድጋፏንእየሰጠችነው፡፡“

ሶማሊያን የመውረር ዕቅድ በተግባር ለማዋል እየተሰራ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እውነትለመናገርይህ አካሄድአሁንም ቢሆን የሚፈይደው ነገር ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እ.ኤ.አኦክቶበር8/2008 “በሶማሊያ የመለስዜናዊ የሰላም አስከባሪነት ሸፍጥ ፍጻሜ/The End of Pax Zenawi in Somalia” በሚል ርዕስ ባቀረብኩትትችት ላይ እንዲህ የሚልጽሑፍ አስነብቤ ነበር፣“እውነተኛው ጉዳይ ሲታይ ሶማሌዎች በመለስ ዜናዊ ወይም በሌላበማንምግለሰብ ወይም ቡድን በኃይልበሚደረግ ተጽዕኖ ሰላም ማምጣት አይችሉም ፍላጎትም የላቸውም፡፡ ሶማሊዎችእና ሶማሊዎች ብቻናቸው የእራሳቸውን ችግሮች መፍታት የሚችሉት፣እናም ይህንን በሚጻረር መልኩየሚደረጉጣልቃገብነቶች ሁሉ አንድም የለየላቸው ውሸቶችናቸው፣ አለያም ደግሞ ምንም ባለማወቅ የሚደረግአሳዘኝየሆነ የዋህነት ነው፡፡“

ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀው አትችልም።

 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 12 ቀን 2007 .

Filed in: Amharic