>

በአዲስ አበባ የሚካሄደው መንግስት መራሽ የመሬት ወረራ!! ( ኤርምያስ ለገሰ)

በአዲስ አበባ የሚካሄደው መንግስት መራሽ የመሬት ወረራ!!
    
                 ኤርምያስ ለገሰ

፩. በአዲስ አበባ የተካሄደው የመሬት ወረራ ተፈላጊውን ትኩረት ለምን እንዳላገኘና ባህሪያቱ፣
1.1. ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገር የመቀጠል የህልውና አደጋ ስላጋጠማት የህዝቡ ትኩረት ተቀይሯል፣
     *በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሬት ወረራ አገሪቱ አደጋ ውስጥ መውደቋና የአስተዳደር ለውጥ መካሄዱ አንድ ማሳያ ተደርጐ ይወሰዳል።
  1.2.  በኢትዮጵያ የተፈጠረው ቀውስ ከመሬት ጉዳይ በላይ ሆኗል፣
    * እንደ ሰው ልጅ መኖር ያለመቻል ቀውስ፣
   *አሰቃቂ ጭፍጨፋና የጅምላ ግድያ
     *ዘር-ተኮርማፈናቀል።
    *የዘር-ማጥፋት(ጄኖሳይድ)።
     *በጦርነትና ድህረ-ጦርነት ሰብዓዊ ቀውስ መከሰት።
 1.3.  በአዲስ አበባ እየተፈራረቀ ያለው አገዛዝ የምስለኔ እና የተረኝነት አባዜ የተጠናወተው መሆኑ፣
 1.4. በማህበረሰቡ ዘንድ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” የሚል ድውይ አመለካከት መኖር፣
1.5  ምርጫ የመምጣት ምልክት ተደርጐ ይወሰዳል።
1.6.  መንግስት መራሽ ወረራ የሚካሄድ መሆኑ ( የፓለቲካ ምስለኔ ሹመኞች፣ የመሬት አስተዳደር ባለስልጣንና ሙያተኞች፣ ደንብ ማስከበር፣ ቢሮክራሲው የሚሳተፍበት መሆን፣
  1.7.  የሚዲያዎች መታፈን
     *የመንግስትና የተደጋፊ ተደማሪው ሚዲያ በተሰጠው አቅጣጫ ብቻ የሚሰራ መሆኑ፣
     *የሞጋችና ምርመራ የሚሰሩ ሚዲያዎች መታፈን)
  1.8. በማህበረሰቡ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ፣ ባይተዋርነት እና “ምን-ተዳዬ” እየተንሰራፋ መሄድ፣
    1.9.  የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ሁኔታ  (‘መታፈንና መታሰር’፣ ‘ወረተኝነት’፣ ‘ከጊዜያዊ የፓለቲካ ትርፍ በላይ አለመስራት’፣ ‘መፍራት’፣ ‘በወረራው ላይ ተሳታፊ መሆን’፣ ‘አድርባይነት’)
፪: የአዲስ አበባ መሬት ወረራ ለምን ማቆሚያ ያጣ ሆነ? መዋቅራዊ ምክንያቶቹ ምንድናቸው?
   2.1. ሕገ-መንግስታዊ እግረ-ሙቅ የተጠለቀለት የመሬት ፖሊሲ፣
     *ከአዲስ አበባ ውጪ መሬት ብሔር/ብሔረሰብ አለው።
   2.2. አዲስ አበባ በታቀደ መንገድ ባለቤት አልባ መሆኗ። ክልላዊ ቁመናዋ በመገፈፉ
    2.3. በመረጠችው መተዳደር አለመቻሏ (በተለያዩ ጊዜያቶች የመጡት ምስለኔዎች አፓርታይድና ፋሺዝምን እያዋሃዱ መግዛታቸው፣
   2.4. መሬትና ከመሬት ጋር ያሉ ተያያዥ ጉዳዮች ዋነኛ የመንግስት የገቢ ምንጮች መሆናቸው፣
አዲስ አበባ የራሷ የፀጥታ ኅይል የሌላት መሆኑ
፫:የመሬት ወረራው የአስተዳደር ለውጥና የምርጫ መምጣት ምልክት እንዴት ተደርጐ ይወሰዳል?
3.1. አዲሱ አስተዳደር ቅቡልነቱን የሚያረጋግጠው የተሰናባቹን ወንጀሎች በመዘርዘር ነው። ( በጥናት፣ በቃለ-መጠይቅ፣ በዶክመንተሪ መልኩ)
3.2. በህብረተሰቡ ዘንድ ምርጫ በመጣ ቁጥር አዲሱ አስተዳደር ሕገ-ወጡን መሬት ሕጋዊ ያደርጋል የሚል እምነት ተይዟል።
Filed in: Amharic