>
5:13 pm - Monday April 19, 2376

ድንበራችንን ጥሶ ጥቃት ሲሰነዝር በነበረው የሱዳን ሃይል ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው...!!! ሙሉነህ ዮሐንስ

ድንበራችንን ጥሶ ጥቃት ሲሰነዝር በነበረው የሱዳን ሃይል ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው…!!!
ሙሉነህ ዮሐንስ

 

መረጃ – ሱዳን
=========
*…. ከሁለት ቀናት በፊት አዲስ አበባ የነበሩት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብደላ ሀምዶክ ምሽቱን በትዊተር ገጻቸው “ጦራችን የተለመደውን ቅኝት እያደረገ እያለ በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶበት ብዙ ወታደሮቻችን ሞተውብናል፣ መሳሪያዎችም ተወስደውብናል” የሚል የውሸት መረጃ አሰራጭተዋል። ይህንኑ መረጃ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ደግሞታል። የሚገርመው ግን ጦሩ ቅኝት ሲያደርግ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ግዛት ሲያስፋፋ እንደነበር ይታወቃል!
እንግዲህ ለባለፉት ሁለት ሳምንታት ያህል የአማራ ፋኖ፣ ሚኒሻ እና ልዩ ሀይላችን በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ግዳጅ መሰማራቱን ተከትሎ የሱዳን ጦር የአማራ ገበሬዎችን ንብረት እያወደመ፣ ከብቶች እየዘረፈ እና ምሽግ እየቆፈረ እስከ አብደራፊ ድረስ ለመምጣት ሞክሮ ነበር። ይህንንም እንደ ትልቅ ዜና የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እየተቀባበሉ “ሱዳን ከ25 አመታት በኃላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር የነበረው ግዛቷን አስመለሰች” ሲሉ ራሳቸው መስክረው ነበር።
አሁን የሱዳን ጦር የእጁን አግኝቶ ተመልሶ ሄዷል። የአማራ ፋኖ ጦሩን ሲደመስስ መታወቂያቸውን ሳይቀር ጥለው የፈረጠጡ ወታደሮች መኖራቸው ታውቋል። መሪያቸውን ጨምሮ ሌሎች ደግሞ እስከዘላለሙ አሸልበዋል።
 
በትናንትናው እና በዛሬው እለት በምድረገነት(አብደራፊ) አቅጣጫ ድንበር ከጣሰው የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በኢትዮጵያ በኩል ድል ተገኝቷል። ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ሰላም በር የተባለችን መንደር በሃይል ለመቆጣጠር የመጣውን የሱዳን ወራሪ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የኢትዮጵያ ሃይል ብዙ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህ ከባድ የአፀፋ መልስ እና ድንበር የማስከበር እንቅስቃሴ በወራሪው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። የአካባቢው ወገን ሕዝብ በዚህ ግንባር ብርቱ ተጋድሎ ማድረጉ ታውቋል። በተደረገው መልሶ ማጥቃት ቁጥሩን መግለፅ የማያስፈልግ ግን በዛ ያሉ ፓትሮል መኪኖች ከነጫኗቸው ድሽቃ፣ አርፒጂ/ብሬን መትረጊሶች እና መሰል መሳሪያዎች ጋር ተማርከዋል። በተገኘው ድል የምድረ ገነት ሕዝብ ደስታውን አደባባይ ወጥቶ ሲገልፅ አምሽቷል።
ነገር ግን ተስፋፊው የሱዳን ጦር በስናር እና በቁጥር 4 የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ሃይል እንዳሰፈረ ይገኛል። ከላይኛው ከምድረ ገነት(አብደራፊ) አቅጣጫ እስከ ታችኛው የመተማ መስመር ደለሎ አካባቢ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ገበሬዎችን/ኢንቨስተሮችን ካምፖች በብዛት ሲያቃጥል መሰንበቱን ለማወቅ ተችሏል። ወንበዴው ትህነግ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ሱዳን የኢትዮጵያ ሃይል የደከመ ሲመስላት ሰራዊቷ ድንበራችንን ተሻግሮ ጥቃት ሲሰነዝር ሰንብቶ ነበር። የሱዳን ጀነራሎች በባለ ሃብቶች የመዘወር ታሪክ አላቸው። ፈርጥጦ ሱዳን የሸሸው የወያኔ ወንበዴም በዚህ ጀርባ እንዳለበት ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ።
ከታሪክ እንደምንማረው የሱዳን ጦር ኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት ያለ ሲመስለው ድንበር እየተሻገረ ጥቃት ይሰነዝራል፣ የገበሬ ማሳ ያቃጥላል፣ የኢንቨስተሮች ካምፕ ይወራል እና መሰል ጥፋት ያደርሳል። ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል ይገባኛል የምትለው ወሰን በቅኝ ገዥዋ በነበረችው በእንግሊዝ ሻለቃ ጉየን ያለ ኢትዮጵያ ስምምነት የተዘጋጀን ካርታ መሰረት አድርጋ ነው። በአፄ ምኒልክ ዘመን የተደረገው ይህ የአንድ ወገን የቅኝ ግዛት ቅዠት እንጅ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የማትቀበለው መሆኑን ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግስታት አቋም ይዘውበት ቆይተዋል።
ከዚህ ታሪካዊ እውነታ ባፈነገጠ የወያኔ ዘመን ድንበራችንን ሳያስጠብቅ ቆይቷል። በመተማ መስመር ያለውን ሰፊውን የደለሎ ወሰናችንን እና በላይ ከሑመራ ወደ መተማ አቅጣጫ የተዘረጋውን ሰፊ ግዛት ሱዳን ይገባኛል እያለች በተደጋጋሚ ጦር ስታዘምት ቆይታለች። ቦታውን ሱዳኖች አል ፋሽቃ ትሪያንግል ብለው የሚጠሩት ነው። የአልፋሽቃ አካባቢ ብቻ ስፋቱ ከአዲስ አበባ የአስተዳደር ወሰን የሰፋ ነው። በኢትዮጵያ በኩል ጓንግ ወንዝ በተለምዶ የእኛ ገበሬዎች እና ከብት አርቢዎች ሲጠቀሙበት የኖሩት ትልቅ ወንዝ እና በይዞታችን ከጥንትም የቆየ ነው። እንዲያውም የአርማጭሆ እና የቋራ ሕዝባችን ወሰናችን ከጓንግም አልፎ ብዙ እንደሚሄድ ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በድንበሩ ላይ ስፋት እና ጥልቀት ያለው ዝግጅት ማድረግ አለበት። በድንበሩ አካባቢ ያለው ሕዝባችንንም ማሳተፍ ይገባል።
Filed in: Amharic