>

የሱዳን ጦር ሰራዊት በሜካናይዝድ ጦር ደረጃ ታጥቆ ወደ ድንበራችን እየተጠጋ ነው!!! (አስናቀ አበበ)

የሱዳን ጦር ሰራዊት በሜካናይዝድ ጦር ደረጃ ታጥቆ ወደ ድንበራችን እየተጠጋ ነው!!!

,አስናቀ አበበ

 ጉዳዮ፡- በኢትዮ ሱዳን ድንበር በኩል ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ ስለማስገንዘብና አፋጣኝ እርምጃ እንድትወስዱ ስለማሳሰብ!
አገራችንና መንግስታችን አሸባሪዉን የትህነግ ሀይል ለማንበርከክ እየሰራ  ባለበት ወቅት  በሱዳን መንግስት ይታዘዝ አይታዘዝ የማናውቀው የሱዳን ጦር ከተራረፉ የትህነግ ሰዎች ጋር በመሆን  አገራችን ያለችበትን አጣብቂኝ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በምራብ አርማጭሆ ወረዳ ከአብጢዮር የኢንቨስትመንት ቦታዎች እስከ መተማ  ደለሎ የእርሻ ቦታዎች ድረስ በድንበር አካባቢ ወረራ አካሂዶብን ሰንብቷል፡፡ በእርግጥ ወረራው ከኑግዲ የሚጀምር ነው፡፡
ያልጠበቅነው የሱዳኖች ወረራ ከነገ ዛሬ ይቆም ይሆናል፣ የሱዳን መንግስትም ወታደሮቹን ያስቆማል ብለን በትዕግስት ብንጠባበቃቸውም በየቀኑ እርሻዎቻችንና ማሳወቻችንን እየተቆጣጠሩ ከአካባቢዉ  እያስወጡ ሀብትና ንብረቶቻችንን አቃጥለውብናል፡፡ከቃጠሎ የተረፈዉንም ሀብትና ንብረት በመኪና እየጫኑ ወስደዉታል፡፡ በርካታ ትራክተር እና የእርሻ ካምፖች አቃጥለዉብናል፡፡ በርካታ ሰራተኞችን ገለዉብናል፡፡በርካታ የቁም እንሰሳትን ወስደዉብናል፡፡የሀገር ሀብትና ንብረት ወድሟል፡፡እስከዛሬዋ እለት ድረስ በርካታ ባለሀብቶች በተለይም ታችኛው አቦጢር በሚባለው የኢንቨስትመንትና የእርሻ ቦታ የሚገኙ ባለሃብቶቻችን  በሱዳን ጦር ከበባ ውስጥ ናቸው፡፡ በአካባቢው ላይ ያሉለሀብቶችና አርሶ አደሮች የእርሻ ማሳቸዉንና የሚኖሩበትን ቀበሌ እየለቀቁ  ወደ አብደራፊና አብርሀጅራ ከተሞች እየመጡ  ናቸው፡፡
ትዕግስት የተፈታተነው የአካባቢዉ ሚሊሻ በዛሬው እለት  በወሰደው  እርምጃ በተወሰነ ደረጃ ቢመለሱም  የባሰ ከሳሽ ሆነው ይበልጥ ተደራጅተው አካባቢዉን ለመዉረር ከፍተኛ ጦር ወደ ድንበር እያስጠጉ ነው፡፡ቶሎ መድረስ ካልተቻለ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱብን መሆኑን ተገንዝባችሁ የፌደራሉም ሆነ የክልሉ መንግስት የሀገር መከላከያ እንዲገባ በማድረግ እና ዲፕሎማሲያዊ ዉይይት በማካሄድ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥበት ስንል የምዕራብ አርማጭሆ ሕዝብ ከፍተኛ ጉዳት ከመድረሱ በፊት በጥብቅ እናእናሳስባለን።
Cc:-Abiy Ahmed Ali
Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia  Demeke mekonnen
Agegnehu Teshager አገኘሁ ተሻገር-Agegnehu Teshager
 ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓም
 ከምድረ ገነት (አብደራፊ) እና አብርሀጅራ
Filed in: Amharic