>

“ የዓረብ ሰይፍ ”   -  የበረኅኞቹ ትንቢት  ሊፈጸም ይሆን ?   (ዘመድኩን በቀለ)

“ የዓረብ ሰይፍ ” የበረኅኞቹ ትንቢት  ሊፈጸም ይሆን ?  

ዘመድኩን በቀለ

 …. የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያለው ነው የሚባለው የቤኒሻንጉል ጉምዙ አሻሃድሌ ሀሰን ከሥልጣን ወሰኑ ውጪ ከሱዳን መንግሥት ጋር እየመከረ መሆኑን እያየን ነው። ይሄ ከዐቢይ ዕውቅና ውጪ የተደረገ እንዳይመስለን….!
 
*   “ በሁለት ኃያላን መንግሥታትና በሰባት የዓረብ መንግሥታት”  ወረራ… የሚለውን አስታወሳችሁን? ኣዎ ማስታወስ መልካም ነው። ተዘጋጅቶ መጠበቅም እንዲሁ መልካም ነው። የሚታዩት ምልክቶች ሁሉ ወደዚያው ነው የሚያመለክቱን። 
•••
ባለፈው ሰሞን በጣውንታችን ግብፅ አስተባባሪነትና አዘጋጅነት የተጠራና የተመራ እንዲሁም “ የዓረብ ሰይፍ ” የሚል ስያሜ የሰጡትን ወታደራዊ ልምምድ ዓረቦቹ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሄን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፈቀላጤ አቶ ዲና ሙፍቲ “ መብታቸው ነው፣ አይመለከተንም፣ አያገባንም፣ አያስፈራንም” ማለታቸውንም ሰምተናል።
… ቀጥሎ የግብፅ ቀኝ እጅ ሳዑዲ አረቢያ መጀመሪያ ግብፅ፣ ቀጥሎ ሱዳን፣ ከዚያም ኤርትራን ስትጎበኝ መክረሟም ይታወሳል። በምን ጉዳይ እንደተወያዩ አናውቅም። ግን ዙሪያችንን እያንዣበቡ ነው።
… በሃገር ውስጥ የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያለው ነው የሚባለው የቤኒሻንጉል ጉምዙ አሻሃድሌ ሀሰን ከሥልጣን ወሰኑ ውጪ ከሱዳን መንግሥት ጋር እየመከረ መሆኑን እያየን ነው። ይሄ ከዐቢይ ዕውቅና ውጪ የተደረገ እንዳይመስለን። እነ ደብረ ጽዮን የተወቀሱበትና የተብጠለጠሉበትም ጉዳይ እንደነበር አንዘንጋ።
… በሃገር ውስጥ ኦነግ ከዐቢይ ጋር በዐቢይ መንግሥት ድጋፍ በኦሮሚያ ወለጋ እየፈነጨ ይገኛል። የዐማራ ነገድ አባላትን ማረዱንም አጠናክሮ ቀጥሏል። ለዚህ ጉዳይ የዐቢይ መንግሥት ቁብም የሰጠው አይመስልም። ኬሬዳሽ ነው።
… ዶር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያው ኦነግ ኦህዴዱ የብልጽግና አፈ ቀላጤ በአቶ ታዬ ደንደአ በኩል ለዐማራው ማስጠንቀቂያም፣ ምክርም አዘል ነገር ለማስተላለፍ እየሞከረም ነው። ከታዬም አልፎ ለዐማራው በአሻሃድሌ ሃሰን በኩል ጥብቅ ማስጠንቀቂያም ለዐማራው እነ ሽመልስ አብዲሳ አስተላልፈዋል። ዙሩ እየከረረ ይመስላል። ሰሜን ላይ ደም ለማፍሰስ ዓለሙ ሁሉ የቋመጠ ይመስላል።
… አሁን እንግዲህ ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው ሰሞኑን እሜቴ ሱዳን የመጀመሪያውን የሙቀት መለኪያ ጦርነት በጎንደር ዐማራ በኩል የሞከረችው። ድሮ ድሮ ጎረቤታችን እሜቴ ሱዳን ሆዬ በመንግሥቱም ሆነ በጃንሆይ ዘመን እጅግ አድርጋ ታከብረን፣ ትፈራንም ነበር። ወያኔ መጣችና ንቃ ስታስንቀን ጊዜና ሄጵ አለችብን። ሱዳንሻ ጎንደር ገባ ትልና ጎንደሬዎችን ትተነኩሳቸዋለች። ፋኖ ሆዬ ታዲያ ልክ ሊያናፍጣት ሲጀምር አጅሪት ሂዊ የሃገር መከላከያውን የደንብ ልብስ ለብሳ ትመጣና ፋኖን ከጀርባው ለሱዳን ተደርባ ትወጋው ነበር። ከፊት ሱዳን፣ ከኋላ ሂዊ ወዩዬ ሳንዱዊች ያደርጉት ነበር የዐማራ ፋኖን። ከሁለት ዓመት በፊት እንዲህ ነበር።
… ሰሞኑንም እሜቴ ሱዳን የሂዊን በፋኖ መጠብጠብ አልሰማችም መሰል እንደለመደችው በጎንደር በኩል ሰተት ብላ ገብታ ዐማራን ካልወረርኩ ብላም ወበራች። ተይ ግን እረፊ ብሎ የሚመክራት ደህና ዘመድም ስላጣች ጦርነት ሠርግና ምላሹ ከሆነው ዐማራ ጋር ተሳፈጠች። አልፎም የሱዳን ወታደር የዐማራ ገበሬን ማሳ በእሳት አቃጠለ። እህልም ዘርፎ ጥቂት የዐማራ ገበሬዎችንም ገደለ። ሕግ አዋቂው ዐማራም ለመንግሥቱ አመለከተ። መንግሥትም ለጊዜው ታገሷቸው። የፈለገቱን ይፈጽሙ። ከወያኔ ጋር ለጀመርነው ጦርነት ኃይል ስለሚዳከምብን ታገሷቸው። ሲገድሏችሁም ዝም ብላችሁ ሙቱ ብሎ መከራቸው። የመንግሥት ምክር አስቂኝ ቢሆንም ሱዳኖቹ ያለምንም ይሁንታ የማርያም መንገድ አረንጓዴ የይለፍ መብራት ያሳያቸው አካል አለና ሰተት ብለው እየገፉ እንደፍልፈል አርማጨሆ መግባት ጀመሩ።
… አይ አለልሃ ዐማራ። አይ ኤጭ አሁንስ አበዙት አለልሃ ዐማራ ተራራው። ክላሹን ወልውሎ ባለ መትረየስና ስናይፐር የጫነውን ሱዳንን ገጠመው። ገጠመውና ገጥቦ፣ ገጥቦ ለቀቀው። እንድድሮው ከኋላ የሚወጋው መንግሥትም ወታደርም ስላልነበረ ዐማራ ተራራው ሱዳንን አስነጥሶ፣ አስነጥሶ በሃንጢሾ ብቻ ድንብርብሩን አውጥቶ በፍርጠጣ ካርቱም አስገባው።
… የሞተው ሞቶ፣ የፈረጠጠውም ኮፍያውንም፣ ልብሱንም ጥሎ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈርጥጦ ድራሽ አባቱ ጠፋ። ዐማራ ተራራውም የማረካቸውን ሁሉ ከትጥቅ እና ስንቅ ተሽከርካሪና የጦር መሣሪያ አንስቶ ራሳቸውን ከነነፍሳቸው ማርኮ፣ የቆሰለውንም በሞተር ሳይክል አሳፍሮ፣ ጭኖ አምጥቶ ለመንግሥት አስረክክቦ አሁን ቀጣይ ተረኛ ግባ፣ ማነህ ባለ ሳምንት መግጠም ያማረህ የራበህ ሞት በማለት ቀጣይ ቀባጭ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
… ዐማራው ቀስተኛው አራጅን እኮ አይደለም እረፍ እያለ ያለው። ያኛውን ነው። ያኛውን ቀስተኛውን የሚልከውን። እሱን ነው ዐማራው የሚፈልገው። ወንድ ከሆንክ ከጫካም ሆነህ፣ ከፈለግክ ሜዳም ላይ ወጥተህ ዐማራውን ግጠመው። በእሳት ውስጥ ማለፍ ለዐማራው አዲሱ አይደለም። አይደለም አርደህ እየበላኸው ደርድረህ ልፍጅህ ብትለውም አትጨርሰው። ልፋ ቢልህ ነው። ወዳጄ ከወልቃይትና ከጠገዴ፣ ከራያም መማር ነው የሚሻለው የሚበጀው።
… ሂዊን ለማናፈጥ ፋኖንና ኤርትራን የተጠቀመው ዐቢይ አሕመድ፤ አሁን ደግሞ ዐማራውን ለማንበርከክ ሱዳንን እየገፋ ወደ እሳት ውስጥ እየጨመራት ይመስለኛል። ሱዳን ለሙሉ ጦርነት ዝግጁ መሆኗን እያሳየች ነው። ኦነግ በወለጋ እየወበራ ነው። ታዬ ደንደአ ዳግማዊ ጌታቸው ረዳም እየፎገራ ነው። ቤኒሻንጉልም ቀስቷን ወድራ ተዘጋጅታለች። እንዲያውም ዛሬ ይባስ ብላ ጌታዋን ተማምና ላቷን ከደጅ ማሳደር የጀመረችዋ ቤኑ ሁለት የዐማራ ልዩ ኃይል ወታደሮችን መግደሏ ተሰምቷል። ይሄ ሁሉ መንፈራገጥ ዐማራን ጎትቶ ወደ ጦርነቱ ለማስገባት ይመስላል።   የመጨረሻው ቀን እንደሁ መምጣቱ አይቀርም። ያ አባቶች ያሉት ቀን መምጣቱ የሚቀርም አይመስልም። “ በረኀኞቹን አስታውሱ ”
… ወጥር ዐማራ  !! … እንደ አንበሳም እንደ ንስር ሁን !! … ጸሎትህንም አትርሳ !! ቀዳሽም…  አራሽም … ተኳሽም … ሁን።
ሻሎም !   ሰላም !
 ነኝ።
Filed in: Amharic