>

ኮሎኔል ማራኪዋ  ጀግና ኢትዮጵያዊት ም/አስር አለቃ ገባያነሽ ደባል !!! (ሄቨን ዮሀንስ)

ኮሎኔል ማራኪዋ  ጀግና ኢትዮጵያዊት ም/አስር አለቃ ገባያነሽ ደባል !!!

ሄቨን ዮሀንስ

 

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም።
 የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።
ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።
በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።
ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ወደ ኤርትራ በመሸሽ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።
በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ይካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።
ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችሁ እንዲህ ታጫውተናለች ።
“… ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደመፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ካሃዲው አዛዥ ተብየ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድየ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል…”
“… በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ ።”
ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።
ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !
ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባል
Filed in: Amharic