>
5:13 pm - Sunday April 19, 7299

ኦነግን ለማሸነፍ ከባድ የሆነበት ምክንያት ኦነግ ኦህዴድ ውስጥ ስላለ ነው !!! (ግርማ ካሳ)

ኦነግን ለማሸነፍ ከባድ የሆነበት ምክንያት ኦነግ ኦህዴድ ውስጥ ስላለ ነው !!!

ግርማ ካሳ

ባይገርማችሁ በኦሮሞ  አፓርታይዳዊ ክልል አቶ ለማ መገርሳ የክልሉ መስተዳደር  ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ  በሺመለስ አብዲሳ ቀጥሎ ከ31 ዙር በላይ የኦሮሞ ክልል፣  ኦሮሞዎችን ብቻ ያቀፈ ብዙዎችም ኦነግ የነበሩ የተካተቱበት፣ የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል አደራጅቷል፣ አስመርቋል። በአስር ሺሆች የሚቆጠር። ምን አልባት መቶ ሺህ ሊደርስ የሚችል።
ሆኖም ግን ያ ሁሉ ሕግን አስከብራለሁ የሚል ሰራዊት እያለ  በዚህ ክልል እጅግ አሰቃቂ የዘር ማጥፋትና  የዘር ማጽዳት ወንጀሎች ተፈጽመዋል። እየተፈጸሙም ነው። በዚህ ክልል ኦሮምኛ ተናጋሪ ወይንም ኦሮሞ ያልሆኑ፣  በተለይ አማራዎችና አማራ ባይሆኑ አማራ ተብለው የሚታሰቡ፣ ወይም በአንዳንድ ቦታዎች ኦርቶዶስክ የሆኑ ኦሮሞዎች በስጋት ላይ ነው ያሉት።
ብዙ የክልሉ ልዩ ኃይላት በኦነጎች እየተገደሉ እንደሆነ እናውቃለሁ። ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ይኸው ከአንድ አመት ተኩል በላይ አንዳንድ ቦታ የፌዴራል መከላከያ ገብቶበት ዉጊያ እየተደረገ ነው። ኦነጎችን ለምን መደምሰስ አልተቻለም ? ችግሩ ምንድን ነው ??  ለችግሮቹ ሁለት ምክንያቶች ማቅረብ ይቻላል፡
አንደኛው፣ የክልሉና የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ አመራሩ ውስጥ ኦነጎች፣ ጃዋራዊያን በብዛት ስላሉ ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልን በተገቢ ሁኔታ ማሰማራት አልተቻለም። ለምሳሌ በሻሸመኔ ችግር እንደነበረ የክልሉ መሪ ሺመለስ አብዲሳ ሲነገረው፣  ለልዩ ኃይሉ እርምጃዎች እንዲወሰድ  ትእዛዝ ለመስጠት አልፈለገም ነበር።
ሁለተኛ ልዩ ኃይሉ ወይንም መከላከያ  በሚሰማራባት ጊዜ ፣ ኦነጎች አስቀድመው መረጃዎች ይደርሳቸዋል። ከስድስት ወራት ነው አንድ አመት በፊት አንድ ሰው የነገረኝን ላካፍላችሁ። ኦነጎች ባስ አቃጠሉ። ወዲያም መከላከያና የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል አጥፊዎችን ለመያዝ ወደዚያ ተሰማሩ። ሆኖም ኦነጎች ተሰውረው ጫቃ ገቡ። ወታደሮችና ልዩ ኃይሎች እንደሚመጡ አስቀድሞ ስለተነገራቸው ሸሹ።
ሌለ በቅርቡ የሆነ ሕዝብ የሚያውቀው ምሳሌ ልጥቀስ። በወለጋ ጉሊሶ መከላከያ ተሰማርቶ ነበር። በድንገት መከላከያ ከዚያ አካባቢ ይነሳል። ነዋሪዎቹ እንዲቆይ ቢለምኑም፣ ታዘናል በሚል። የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይሎች ተክተው እንዲመጡ ታስቦ እንደሆነ በኋላ ተነገረ። በመሐከሉ የአንድ ቀን ክፍተት ተፈጠረ። ሳይታሰብ ኦነጎች መጡ። ከ200 በላይ ዜጎች አማራዎችን በአንድ አዳራሽ ሰብስበው ጨፈጨፉ።
ሰዎቹ ፈረንጆች እንደሚሉት cowards ናቸው። ፈሪ ናቸው። ያልታጠቀ ሰላማዊ ሰው ላይ እንጂ የታጠቀን ሰራዊት አይገጥሙም። ልክ የታጠቁ መከላከያዎች ሲሄዱ፣ ሕጻናትና አሮጊቶችን ገደሉ።
እንግዲህ ትልቁ ጥያቄዬ መከላከያ መነሳቱን  የክልሉ ልዩ ኃይልም ገና አለመምጣቱን ኦነጎች እንዴት አወቁ ???? መልሱ መረጃው አስቀድሞ ስለተነገራቸው ነበር የሚል ነው።
እንግዲህ ያለው ሁኔታ ይሄ ነው። ኦነግ ፣ ኦነግ ሸኔ ምናምን እንላለን እንጂ ኦነግ  የኦሮሞ ክልል መንግስት መዋቅር ውስጥ፣ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ውስጥ አለ !!!! በብዛት !! በተለይም አቶ ለማ መገርሳ በሺሆች የሚቆጠሩትን ያኔ ኦህዴድና ኦዴፓ አሁን ብልጽግና ውስጥ አስገበተዋል።
Filed in: Amharic