>

"ይሕ ፍፁም ከሩዋንዳው ኢንተርሐምዌ የወጣቶች አደረጃጀትና ተግባር ጋር የሚመሳሰል ተግባር ነው!" (ዶክተር ዳንኤል በቀለ...) 

“ይሕ ፍፁም ከሩዋንዳው ኢንተርሐምዌ የወጣቶች አደረጃጀትና ተግባር ጋር የሚመሳሰል ተግባር ነው!”

..(ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለፋና ከሰጡት ቃለ-ምልልስ የተወሰደ ነው)
.
ትሕነግ በማይካድራ ማንነትን መሠረት አድርጎ ከ600 በላይ ንፁሓንን ጨፍጭፏል 
* የማይካድራው  ፍጅት የመርሃ-ግብሩ ቅደም ተከተልና ቅድመ ዝግጅት  
.
* ጭፍጨፋው ……., ዝግጅት ተደርጎበታል ።
* ጥቃቱ ተግባራዊ የሆነው በታጣቂዎች ጥበቃና ከለላ እየተደረገለት ይንቀሳቀስ ከነበረው  ” ሳምሪ ” እየተባለ የሚጠራው የአካባቢው የወጣቶች አደረጃጀት ነው ።
* ወጣቶቹ …. በአካባቢውም የሚታወቁ ናቸው ።
* ጥቃቱንም ሲፈፅሙ በሚሊሻና በፖሊስ እየታጀቡና ከቤት ቤት እየዞሩ ነው ።
* ጭፍጨፋውና ግድያው በዱላ ፣ በስለት ፣ በጩቤ ፣ በፋስ ፣ በመጥረቢያ ግማሾቹ ደግሞ በገመድ አንገታቸው እየታነቀ ነው ።
* ቡድኑ በተለይም የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ትኩረት አድርጎ ነው ጭፍጨፋውን ያከናወነው ።
* ቀደም ሲል ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ መመሪያ ተላልፎላቸውል ።
* ገዳይ ወጣቶቹ በከተማው መውጫና መግቢያ ቦታዎች ከአካባቢው ሚሊሻና ፖሊስ ጋ በመቀናጀት ኬላ አቋቁመው ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ ሲቆጣጠሩ የነበር ።
* ሰዎች ማንነታቸውን ለመለየት በመታወቂያቸው ጭምር የመለየት ስራ ተከናውኗል ።
* የሱዳን ሲም ካርድ ያላቸው ሰዎች ስም ካርዳቸው ተወስዶ እንዲሰባበር ተደርጓል ፣
* ከዚህ በሗላ ጥቅምት 30 መንገድ የመዝጋቱ ሒደት በከፍተኛ ደረጃ ተጠናቀቀ ።
* በተጠቀሰው ቀን 5 ሰአት ላይ ተጨማሪ የማንነት ማጣራት ተግባር ተከናወነ ።
* ከሰአት በሗላ 9 ሰአት ላይ የመጀመሪያው ጥቃት ተፈፀመ ።
* ቀጥሎ ለሊቱን ሙሉ ሲካሄድ አነጋ ።
* ሊያመልጡ የሞከሩ በጥይት ተመተው ተገለዋል ።
* በጥቃቱ ሊስት ውስጥ የሌሉ ግን ደግሞ ተጠቂዎችን ለማዳን የሞከሩ  የግድያው ሰለባ ሆነዋል ።
* ጠዋት ጥቃቱን ሲፈፅሙ ያነጉት ቡድኖች (ሳምሪዎች )  ፣ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ከተማውን ለቀው ወጥተዋል ።
Filed in: Amharic