>
5:14 pm - Friday April 20, 4992

ወደ ሱዳን ለተሰደዱት ወገኖች የአጣዳፊ ድጋፍ አስፈላጊነት ለነገ የሚባል አይደለም! (ዘ .ተስፋዬ)

ወደ ሱዳን ለተሰደዱት ወገኖች የአጣዳፊ ድጋፍ አስፈላጊነት ለነገ የሚባል አይደለም!

 

.ተስፋዬ


የህወሃት አመራር በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የከፈተውን ድንገተኛ ጦርነትና የክህደት ጥቃት ለመከላከል ቡድኑ የከፋ ጥፋት እንዳያደርስና ይሄን የጦር ዘመቻውን ወደሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እወስደዋለው የሚለውን ፉከራውን ለማምከን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ላለፉት ሁለት ሳምንታት እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል።

ወትሮም ጦርነት ሲቀሰቀስና ሲካሄድ ከቀጥታ ተፋላሚዎቹ በተጨማሪ ትልቁን ገፈት የሚቀምሰው ሰፊው ሰላማዊ ህዝብ እንደሆነ ይታወቃል፣በዚህ ግጭት ሳቢያም እየሆነ ያለው ይሄው ነው።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከግጭቱ ለመሸሽና ቀድሞ በተነዛው ፕሮፓጋንዳ ፍራቻ ጭምርም 20ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችን፣ ሽማግሌ አሮጊት ሀጻናትና ወጣቶችን ጨምሮ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ተገደዋል።

ይህ ልብ የሚነካ የወገኖቻችን ስደት በፍጹም መሆን ያልነበረበት ቢሆንም ሆኗልና ባሉበት ቦታ አጣዳፊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ለሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ተማጽኖ ከማሰማት በተጨማሪ ሁላችንም የአቅማችንን ልንረዳቸው ይገባልና፣ ከዚህ ቀደም ለወገን ደራሽ የነበሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በአጣዳፊ በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ሊያስተባብሩ ይገባል

የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱና አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ቢገልጽም፣ ጦርነቱ እስካልተቋጨና ለመሰደድ ገፊ ምክንያት የነበረው ፍራቻ እስካለተቃለለ ድረስ የመመለስ እድላቸው ውሱን በመሆኑ፣ ባሉበት ስፍራ የሚረዱበትን መንገድ መፈለግ ይኖርበታል። ከዚህም በተጨማሪ ግጭት የተካሄደባቸው አካባቢ ዜጎች እንዳይሰጉና ስደትን እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዳያዩ አስፈላጊውን መረጋጋትና ሰላም ማስፈን የመንግስት ኃላፊነት ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያ ህዝብ 

 

 

Filed in: Amharic