>

የተ. መ. ድ በኢትዮጵያ "መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ እንደሆነ" አስጠነቀቀ...!!! ዶችዌሌ

የተ. መ. ድ በኢትዮጵያ “መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ እንደሆነ” አስጠነቀቀ…!!!

ዶችዌሌ

* እስከ ዛሬ ማክሰኞ ሕዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ብቻ 27,000 ሰዎች ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን አስታውቋል
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ባባር ባሎች እንዳሉት በቀን ወደ አራት ሺሕ ገደማ ሰዎች ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን እየተሰደዱ ነው።
ባሎች “ውጊያ የሚሸሹ ስደተኞች ከረዥም የእግር ጉዞ በኋላ ተዳክመው ጥቂት ንብረቶቻቸውን እንደያዙ እየደረሱ ነው” ሲሉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
“በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚካሔደውን ውጊያ በመሸሽ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን እየተሰደዱ በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን መሆኑን ያስጠነቅቃል” ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ባባር ባሎች ተናግረዋል።
Filed in: Amharic