>
5:13 pm - Monday April 18, 8766

ሁሌም "የተለየህ ህዝብ ነህ!"  እያላችሁ የተለያየ መከራ እንዳመጣችሁበት ነው ...!!! (አንዱአለም ቦኪቶ)

ሁሌም “የተለየህ ህዝብ ነህ!”  እያላችሁ የተለያየ መከራ እንዳመጣችሁበት ነው …!!!

አንዱአለም ቦኪቶ 

..”ህዝብን በጉልበት ማንበርከክ አይቻልም በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብን!” 
ዶ/ር ደብረጽዮን
10 ሺ ማርከናል አይነት ቀደዳዎችን እንተዋቸውና አንደኛው ንግግሩ  ላይ ብቻ  ላተኩር …”ህዝብን በጉልበት ማንበርከክ አይቻልም በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብን!” ያላት ነገር!
ይቺ ከላይ ስትታይ ተራ እውነት የምትመስል በትምክህት የታጀለች አ.ነገር ..ህወሃት  አሁን ላይ ለሚገኝበት አዘቅት ዋንኛ መንስኤ ትመስለኛለች!
በርግጥ እውነት ነው ህዝብን በጉልበት ማንበርከክ አይቻልም!
በተለይ የኦሮሞን ህዝብ :በተለይ የአማራን ህዝብ: በተለይ የሲዳማን ህዝብ :በተለይ የሶማሌን :በተለይ የወላይታን በተለይ የጋምቤላን…ወዘተ
ወንድሜ የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ የሚለይበት አንዳችም የተለየ ነገር የለም!
የራሱን ጨምሮ የጥቂት ጓዶቹን ኢጎ ለመጠበቅ ዋንኛ አላማው ሰርቶ ማደር ለሆነው ምስኪን ደሃ እና ጎስቋላ ህዝብ :የልጆቹን መማሪያ ቤት ዳስ ያላለበሰለትን ገበሬ: አንድ እንስራ ንጹህ ውሃ እንደ ውስኪ ቅንጦት ለሆነባት የትግራይ እናት…አንቺ ልዩ ፍጥረት ነሽ:አንተ እንደሌላው ኢትዮጵያ አይደለህም በሚል የትምክህት ተረት ተረት አጅለው ዳግም ለጥይት አረር ዳርገውታል!!
ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ሁሌም ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር እንደምናያቸው አይነት የጦርነቱ ሰለባዎች የመቀሌን እና የአክሱምን ጎዳናዎች የሚያዥ ቁስላቸውን በፋሻ ጠቅልለው ምናልባትም በክራንች እና ዊልቼር እየተረዱ  ያጥለቀልቁታል(በተቀሩት የኢትዮጵያ ከተሞችም እንደዛው)..እናቶች እንደተለመደው ልጆቻቸውን ቀብረው በሰቀቀን ግድግዳ ላይ የተሰቀለ ፎቶ እያዩ እህህህ ይላሉ!
“አንተ ልዩ ህዝብ ነህ !”  ባዬቹ እንደ  እነ  አሉላ ሰለሞን አይነቶቹ የማሰቢያ አድማሳቸው  ከአፍንጫቸው እስከ ሃገጫቸው የሚሰፋ  ቅልቦች ደግሞ  በአውሮፓና በአሜሪካ ጎዳናዎች ቅንጡ መኪናዎቻቸውን እየነዱ በስልኮቻቸው ላይ  የአካል ጉዳተኞቹን ፎቶ ስክሪን ሴቨር አድርገው ‘ሪሃብሊቴሽን…’  ምናምን የሚል አጀንዳ ነድፈው ኪሳቸውን በጎፈንድ ሚ  እየሞሉ  ህይወታቸውን በተለመደ መልኩ ይቀጥላሉ!
  ይህ ነገ የምናየው ነው!
 ህወሃት በደላላ አፈላልጋ ያገኘችው ይህ ጦርነት በየትኛውም  ሎጂክ  የትግራይን  ደሃ ማህበረሰብ የሚጠቅምበትን  ጎን ልታሳየን አትችልም!
ሌሎቻችሁም ተጋሩ ሁላ…. ቆም ብላችሁ ብታስቡ ዛሬ ጎሽ ጎሽ እያላችሁ በምታሟሙቁት ጦርነት ለዚህ “ያልተለየ”  ህዝብ “የተለየ”  መከራ እንዳመጣችሁለት ይገባችሁ ነበር!
መልካም ቀን
Filed in: Amharic