>

ያብይ አህመድ ሁለት ነብሮች (መስፍን አረጋ)

ያብይ አህመድ ሁለት ነብሮች

 

መስፍን አረጋ


ወያኔ የጦቢያና ያማራ ገዳይ ጠላት (mortal enemy) ነው ማለት ግልጹን መግለጽ ነው፡፡   ከወያኔ እጅግ የከፋው የጦቢያና ያማራ ገዳይ ጠላት ግን በዐብይ አህመድ የሚመራው ኦሮሙማ ነው፡፡  ዐብይ አህመድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተቀናብሮ፣ በተመስገን ጥሩነህ ጉዳይ እስፈጻሚነት አማራና ትግሬን የሚያጨራርሰው፣ ሁለቱም ሲዳከሙለት ያለምንም ተቀናቀኝ የኦሮሙማ አጀንዳውን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ብቻና ብቻ ነው፡፡  

 

አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ

ርስበርስ ተዳምተህ በምክኒያት ተልካሻ

ስትዳከምለት በስተመጨረሻ፣

ሥጋህን በጫጭቆ የኦነጉ ውሻ

ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡፡

 

ዐብይ አህመድ እየተገበረ ያለው ቻይኖች የሁለት ነብሮች ፍልሚያ (when two tigers fight) የሚሉትን ጠላትን በጠላት የመርቻ ዘዴ ነው፡፡  ሁለት ነብሮች ከተፋለሙ፣ ፈፍልሚያው የሚጠናቀቀው አንዱ ሙቶ ሌላኛው ለመሞት ሲያጣጥር ነው፡፡  ፍልሚያውን ከዳር ሁና የምታቀጣጥለው ብልጣብልጥ ቀበሮ ደግሞ የሞተውን ነብር ሬሳ ተራምዳ፣ የሚያጣጥረውን ነብር ሲጥ አድርጋ፣ በነብሮቹ ግዛት ላይ አዛዥና ናዛዥ ትሆናለች፡፡ 

 

በእኔ ነግስ እኔ ነግስ ውጊያ በመቀስቀስ

አንበሳና አንበሳ ተፋልመው እርስ በርስ

አንደኛው ድል ሆኖ የሞት ጽዋ ሲቀምስ

ሌላኛው ሲያጣጥር ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ፣

የሞተን ተራምዶ የቆሰለን ገድሎ ጅቦ ሆነ ንጉስ፡፡ 

 

 ዐብይ አህመድ ጦርነቱን የከፈተው ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ነው የሚሉ ወገኖች ደግሞ ኦነጋውያን ያሳመኗቸው (convince) ወይም ያምታቷቸው (confuse) ተላሎች፣ ወይም ደግሞ በጥቅም የደለሏቸው ጥቅማደሮች ናቸው፡፡  ወያኔን ለማጥፋት ጦርነት ሳያስፈልግ፣ ሕገ መንግሥቱን ቀይሮ በብሔር መደራጀትን መከልከል ብቻ በቂ ነው፡፡  ለዐብይ አህመድ ግን በሕገ መንግሥቱ መጡበት ማለት በብሌኑ መጡበት ማለት ነው፣ ያለሱ የኦሮሙማ ሕልሙን ማወን (realize) አይችልምና፡፡ 

ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

አንዴ ቢያታልለን የሱ ነው ኀፍረቱ

ሁለቴ ቢደግም የኛ ነው ጥፋቱ፡፡ 

 

ያማራና የትግሬ ነብሮች ሆይ፡፡  ቢያንስ አንድኛችሁ ተርፋችሁ አብናቶቻችሁ (አባቶቻችሁና እናቶቻችሁ) በደም ባጥንታቸው ያስከበሩላችሁ ሀገር፣ ባህልና ሐይማኖት በስማችሁ ይጠራ ዘንድ፣  ርስበርስ ከመጠፋፋታችሁ በፊት የሁለታችሁም ጠላት የሆነችውን የኦነግን ቀበሮ አጥፏት፡፡  

 

ያገርህ፣ የምነትህ፣ ያንተነትህ ዳራ       

ባንድኛችሁ እንኳ እንዲኖር ሲጠራ

ሳትጋደል በፊት ከወንድምህ ጋራ

የጋራ ጠላትህ መሞቱን አጣራ፡፡

 

ቀበሮዋን ካጠፋችኋት በኋላ ደግሞ፣ ከጉያችሁ ሥር ወደተሸጎጡት፣ በቀጥታና በተዛዋሪ የቀበሮዋ አጋሮች ወደሆኑት፣ የነበር ደበሎ ወደለበሱት አነሮች ፊታችሁን አዙሩ፡፡ 

 

ይቅር ተባብለው ለትናንቱ ዛሬ 

ድርና ማግ ሁነው አማራና ትግሬ

ድነው እንዲያድኑ ጦቢያን ከኬኛ አውሬ፣

የሁለቱም ባንዶች ብአዴን ወያኔ

ባስቸኳይ ይመቱ ባስፈላጊ አዳፍኔ፡፡ 

 

 EMAIL   መስፍን አረጋ    :- mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic