>

በመከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ አላማ ያለው ነው!!! (ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ)

በመከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ አላማ ያለው ነው!!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
————————————————-
በሰሜን ኢትዮጵያ በመከላከያ ሠራዊት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ፡ የተወሰነ እና ሊደረስበት የሚችል ዓላማ ያለው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ማክሰኞ ሕወሓት ትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት እርምጃ መውሰድ መጀመሩን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፣ “በፌዴራል መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግልጽ፣ የተገደበ እና ግቡን የሚመታ ዓላማ ያለው ነው፤ ይህም የሕግ የበላይነትን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስከበር እንዲሁም የኢትዮጵያውያንን መብት በማስጠበቅ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሰላማቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ለማድረግ ነው።” ብለዋል።
መንግሥት ከሕወሓት አመራሮች ጋር ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ በውይይት እና በሽምግልና ለመፍታት ለበርካታ ወራት በትዕግሥት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይሁን እንጂ በወንጀለኛው የሕወሓት ቡድን ሁሉም የሰላም ጥረት ውድቅ ሆኗል ብለዋል።
በመጨረሻም ሕወሓት በትግራይ በሚገኘው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ገልጸዋል።
ዋልታ ኢንፎርሜሽን
Filed in: Amharic